>

መንግስት በታጣቂዎች የሚደርሱ ጥቃቶችን የማስቆም ሃላፊነቱን በበቂ ሁኔታ እየተወጣ አይደለም ....!!!  (ኢሰመጉ)

መንግስት በታጣቂዎች የሚደርሱ ጥቃቶችን የማስቆም ሃላፊነቱን በበቂ ሁኔታ እየተወጣ አይደለም ….!!! 

ኢሰመጉ


አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ከኤፍራታና ግድም ወረዳና አዋሳኝ ከሆነው የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በኩል በመጡ

ታጣቂዎች በ04/11/14 ዓ.ም በተፈጸመ ጥቃት በርካታ የጸጥታ አካላትና የቀበሌው አርሶ አደሮች ላይ ግድያ እና የአካል ጉዳት

መፈጸሙን፣ በኤፍራታና ግድም ወረዳ ስር የሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች ውስጥ ያሉ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውንና በአካባቢው የሚኖሩ

ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው መፈናቀላቸውን ኢሰመጉ ከአካባቢው ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡ በተጨማሪም ይህ

ጥቃት የጀመረው በ3/11/14 ዓ.ም ምሽት እንደሆነ እና እስከ 05/11/14 ዓ.ም ድረስ በአካባቢው ተኩስ እንደነበረ፣ ይህንንም ጥቃት

ተከትሎ በኤፍራታና ግድም ወረዳ መጤ ቀበሌና ዘንቦ ቀበሌ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ እንደነበር ኢሰመጉ

ከአካባቢው ካሰባሰባቸወ መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡

ተያያዥ የህግ ግዴታዎች፡

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ አንቀጽ 3 “እያንዳንዱ ሰው በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነቱ የመጠበቅ መብት” እንዳለው

ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለችው የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል-ኪዳንም በአንቀጽ 6 (1) እና 9 (1) ላይ

ይህንኑ መብት በማረጋገጥ፣ መንግሥታት በቃል-ኪዳኑ የተረጋገጡትን መብቶች በግዛታቸው የማክበር፣ የማስከበርና የማሟላት

ግዴታ እንዳለባቸውም በአንቀጽ 2 (1) እና 2(2) ይደነግጋል። የአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር አንቀጽ 4 ማንኛውም

ግለሰብ በሕይወት የመኖር መብቱና የአካሉ ደህንነት ሊከበርለትና ሊጠበቅለት እንደሚገባና እነዚህን መብቶቹን በዘፈቀደ ሊነፈግ

እንደማይችል ተመላክቷል። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 14 “ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ

በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና የነጻነት መብት አለው” ሲል ይደነግጋል። በተመሳሳይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 15

ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት እንዳለውና በሕግ ከተደነገገው ውጪ ሕይወቱን ሊያጣ እንደማይችል በግልፅ

ደንግጓል።

ከዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች እንደምንረዳው መንግስት የሰዎችን ሰብዓዊ መብቶች

ማክበር፣ ማስከበር እና የማሟላት ሀላፊነት አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ሲቀር እና በመንግስት ቸልተኝነት የዜጎች ሰብዓዊ መብቶች ሳይከበሩ

ሲቀሩ ዋነኛ ተጠያቂ ሊሆን የሚገባው መንግስት ነው፡፡

የኢሰመጉ ጥሪ፡

 መንግስት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኤፍራታና ግድም ወረዳ አጠዬ ከተማ ላይ በተደጋጋሚ በታጣቂ ቡድኖች የሚፈጸሙ

ከፍተኛ የሆኑ ጥቃቶችን በአስቸኳይ ዘላቂ መፍትሔና ጥበቃን በማበጀት ችግሩን እንዲፈታ እንዲሁም ጥቃት አድራሾችን ለፍርድ

እንዲያቀርብ፣

 የሀይማኖት አባቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የማህበረሰብ አንቂዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ሲቪል ማህበራት እና ሰብዓዊነት የሚሰማው በሙሉ

በተደጋጋሚ እየደረሱ ላሉ አሰቃቂ ጥቃቶች የፌደራል መንግስት እንዲሁም የሚመለከታቸው የክልል መንግስታት ትኩረት ሰጥተው

በመስራት የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች የማስከበር ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ በመወትወት የበኩላቸውን እንዲወጡ ኢሰመጉ ጥሪውን

እያቀረበ ከላይ በቀረቡት ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ስራን በማከናወን ሰፋ ያለ ዘገባን እንደሚያዘጋጅ ከወዲሁ ይገልጻል፡፡

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵ

Filed in: Amharic