>
5:13 pm - Friday April 18, 6098

"የአብይ አህመድ በሽታ 10 መገለጫ ፀባዮች አሉት...!!! (ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ )

“የአብይ አህመድ በሽታ 10 መገለጫ ፀባዮች አሉት…!!!

– ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ

* … ዋንኛዎቹ አስመሳይነት እና ራስን ብቻ ከመውደድ የሚመነጩ በሽታዎች ናቸው”

የአማራ ልሂቃን ዝምታ አማራን ጎድቶታል። በግሌ አብዛኛውን ህይወቴን የኖርኩት በኢትዮጵያዊነት ነበር።

አሁንም አረፈደም፣ ቀሪ ህይወቴን ከአማራ ጎን ለመቆም አውለዋለሁ። አማራ በሁለት አደገኛ ጠላቶቹ እንደ ሳንዱች ተጣብቋልና።

በመሆኑም ከአብይ አህመድ የተሻለ ነገር የሚጠብቁ አማሮች በጊዜ ተስፋ ቢቆርጡ መልካም ነው። አብይ በሽታ አለበት።

የአብይ አህመድ በሽታ 10 መገለጫ ፀባዮች አሉት።

እነሱም ከአስመሳይነት እና ከራስን ብቻ መውደድ የሚመነጩ በሽታዎች ናቸው።

1. በእየ ሄደበት ራሱን የሚታወቅ እና የሚወደድ ሰው አድርጎ ማሰብ። ከሱ በስተቀር ሌላ ታዋቂም፣ ተወዳጅም እንደሌለ ማለም።

2. አንድ ሁኔታ ሲፈጠር ያንን ሁኔታ በቁጥጥር ስር የማውለው እኔ ብቻ ነኝ። ሌላ ሰው አይችለውም ብሎ ማሰብ።

3. ሁልጊዜ ውጤማ እንደሆነ ማሰብ። ስልጣን አለኝ፣ ለሰዎች በስልጣኔ ምን ላደርግ እንደምችል አሳያቸዋለሁ። ስልጣኔንና ውጤታማነቴን ሰዎች እንዲውቁለት መፈለግ። በግድ ህዝቡ እንዲያውቅ ማድረግ። ያሰብኩትን የማሳካ ሰው ነኝ ብሎ ማሰብ።

4. በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ ባለ ታሪክ መሪ እሱ ብቻ እንደሆነ ማሰብ።

5. ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ነገር ትምስ ይፈጠር፣ ሞት ይኑር በሃላፊነት ሳልጠየቅ እንደምንም ብዬ ከዚህ ችግር እወጣለሁ። በንግግር ብቻ ሰውን አደንዝዠ ስልጣኔንም አስጠብቄ እወጣለሁ ብሎ ማሰብ። ወንጀል ሰርቶ፣ በወንጀሉ መጠየቁ ቀርቶ በንግግር ብቻ ጀግና መስሎ መውጣትን ማሰብ።

6. የራሴ ግብና አላማ ለመድረስ ህዝቦችን እጠቀምባቸዋለሁ። ህዝቡን መጠበቅና ማስተዳደር ሳይሆን፣ ህዝቡን የእሱ ግብ ማሳኪያ መሳሪያ አድርጎ መጠቀም። ተጠቅሞ መጣልን እንደ ስኬት መውሰድ።

7. ህግ ለሌላው ሰው እንጅ ለእኔ አይሰራም። እኔ ከህግ በላይ ነኝ ብሎ ማሰብ።

8. የሌላ ሰው ችግር ጉዳዬ አይደለም። የሌላ ሰው ሞት አይመለከተኝም። የሀዘን ስሜት አለመኖር። ጭካኔን እንደ ጥበብ መቁጠር።

9. እኔ ከሰው ፍጡር በላይ ነኝ። እንደ ሰው አትቁጠሩኝ። እኔን እንደ ፈጣሪ ተመልከቱኝ፣ ዝም ብላችሁ እመኑኝ። እኔ እውነት ነኝ። እመኑኝ፣ እመኑኝ፣ እመኑኝ … የእውነት መንገድ እኔ ነኝ ብሎ ማሰብ።

9. የምፈልገውን ግብ ለማግኘት ማናቸውንም ነገር አደርጋለሁ። ከፈለኩ እገድላለሁ፣ አስራለሁ፣ ህዝብን አጠፋለሁ እያለ ማሰብ።

  ፈለግ ግዮን

Filed in: Amharic