>

ሰብአዊ እርህራሄ ወይስ ፖለቲካ? (ያሬድ ሀይለማርያም)

ሰብአዊ እርህራሄ ወይስ ፖለቲካ?

ያሬድ ሀይለማርያም


አገር በማፍረስ፣ ጦሩ ላይ አሰቃቂ ድርጊት በመፈጸም፣ ሀገርን በመክዳት እና በሌሎች ከባድ ወንጀሎች ተጠርጥረው ታሰረው የነበሩትን አቦይ ስብሀትን የእድሜ ባለጠጋና ህመምተኛ በሚል አመክኒዮ በምህረቷ የጎበኘች በጎ መንፈስ በተመሳሳይ እድሜ እና የጤና ሁኔታ ላይ ለሚገኙት፣ በእንድም ሰው ሕይወት ላይ ጉዳት ባላደረሱት እና ሃሳባቸውን በብዕርና በንግግር ብቻ ሲገልጹ ጥላቻን እና የቅስቀሳ ንግግሮችን አርገዋል በሚል የታሰሩትን እና አዛውንት ጋዜጠኛና ደራሲ ታዲዬስ ታንቱን በምህረቷ ለመጎብኘት ለምን ሰነፈች? እድሜና የጤና መታወክ የመንግስትን ልብ አራርቶ በከባድ ወንጀል እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መጠየቅ የሚገባውን ሰው ነጻ ካደረገ፤ ይሄው አሰራር እጅግ ቀላል በሆነ ወንጀል ተከሰው ግን በተመሳሳይ ሁኔታ ለሚገኙ አዛውንቶች የማይሰራበት ምን ምክንያት ይኖራል?

በሰብአዊ እርህራሄ መልቀቁ ቢቀር ፍርድ ቤት የክሱን ቅለት መዝኖ የአቶ ታዲዬስ ታንቱን በዋስትና የመለቀቅ መብታቸውን ሲያከብር ያንንስ መቀበል ለከሳሹ አካል ለምን ከበደው? በመንግስት አሠራር ውስጥ እንደ ተቋም ወጥ የሆነ አሰራር አለመኖር የፍትህ ተቋማቱን የሹሞች የፖለቲካ መሣሪያ ሆኖ እንዲቀጥል አያደርገውም ወይ?

Filed in: Amharic