>
5:21 pm - Sunday July 21, 0424

የግፍ እስረኛው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ላይ ፖሊስ በድጋሚ ይግባኝ ጠየቀባቸው!!! (ባልደራስ)

የግፍ እስረኛው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ላይ ፖሊስ በድጋሚ ይግባኝ ጠየቀባቸው!!!

ባልደራስ

በትላንትናው እለት አራዳ ምድብ የግዜ ወንጀል ችሎት በሀሰት ክስ የታሰሩትን አቶ ስንታየሁን ዋስ ቢላቸውም ፓሊስ ግን ይግባኝ እንደጠየቀባቸው ይታውሳል።

በዛሬው እለት ማለትም ነሀሴ 24/2014 ዓ.ም የይግባኝ ሰሚ ችሎት የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አፅንቶታል። ሆኖም ግን ለዋስትና የተጠየቀው ብር ከተከፈለ በኋላ  ፖሊስ በድጋሚ ይግባኝ ለማለት ጉዳዩን ወደ ሰበር ሰሚ ችሎት ወስዶታል። በዚህም ምክንያት አቶ ስንታየሁን ፖሊስ ሳይፈታቸው ቀርቷል።

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ እና የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ስንታየሁ ከዚህ ቀደም በባህርዳር እና በፌደራል ፓሊስ ወንጀል ምርመራ ታስረው የነበሩና ሁለት ግዜ (የ30ሺህ እና የ100 ሺህ ብር) ዋስ ተፈቅዶላቸው የከፈሉ ቢሆንም ሳይፈቱ መቅረታቸው ይታወሳል። የአሁኑ ዋስትና ለሶስተኛ ግዜ የተፈቀደ ነው።

ፍትህ ለአቶ ስንታየሁ ቸኮል

Filed in: Amharic