>

ጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችሎት ነፃ ቢላቸውም እስካሁን ከእስር አልተፈቱም ...!!!

ጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችሎት ነፃ ቢላቸውም እስካሁን ከእስር አልተፈቱም …!!!

 

የባልደራስ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ እና የፓርቲው ስራ አስፋፃሚ አባል የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ ጠቅላይ ሰበር ይግባኝ ሰሚ ችሎት ቀርበዋል።

መሰረታዊ የህግ ክፍተት የሚመለከተው ጠቅላይ ሰበር ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ ዛሬም መርማሪ ፖሊስ በአቶ ስንታየሁ ቸኮል ላይ ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የስር ፍ/ቤቱን ውሳኔ አፅንቶታል።

በውሳኔው መሰረት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ መፈታት ሲኖርባቸው እስካሁን ድረስ አለመለቀቃቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ወዴ ስንቄ ግልፀዋል።

አቶ ስንታየሁ ቸኮል እስካሁን ድረስ ከ4 ወራት በላይ በስር የቆዩ ሲሆን ለዋስትና ብቻ ከ140 ሺህ ብር በላይ ከፍለዋል።

አቶ ስንታየሁ ቸኮል የሶስት ሴት ልጆች አባት ሲሆኑ በቅርቡ በተረኛው ሥርዓት ለ 1 ዓመት ከ6 ወር ታስረው መለቀቃቸው ይታወሳል።

አቶ ስንታየሁ እስካሁን ያልተፈቱት “ለሌላ ጉዳይ እንፈልጋቸዋልን”ተብሎ እንደሆነ ሰምተናል። የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን  ግፍ ሊያወግዝ ይገባል።

በተመሳሳይ ዛሬ ፍ/ቤት የቀረቡት ጋዜጠኛ  ታዲዎስ ታንቱ ለጥቅምት 14/2015 ዓ.ም የተቀጠሩ ሲሆን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ደግሞ ለጥቅምት 10/2015 ዓ.ም ተቀጥረዋል።

Filed in: Amharic