>
1:19 pm - Friday March 24, 2023

በነገራችን መሃል…!! (ዘመድኩን በቀለ)

በነገራችን መሃል…!!

ዘመድኩን በቀለ

“…ብዙዎቻችሁ የራያው ልጅ ጎበዜ ሲሳይ በድጋሚ ታሰረ የሚል ዜና በመስማታችሁ በውስጥ መስመር እዬዬ ስትሉብኝ አርፍዳችኋል። እና ምን ይጠበስ ነው የምትሉት? ሲጀመር ጥፋተኛው እኮ እርሱ ራሱ ጋዜጠኛው ነው።

“…መጀመሪያ ነገር ቀድሞውኑ እርሱም ናትናኤል መኮንንም አባል ከሆኑበት ከግንቦት 7 ፓርቲ ለምን ወጣ? እና ዐማራ ሆኖ ከግንቦት 7 ሲለቅ እነ ብርሃኑና እነ አንዳርጋቸው ጽጌ ዝም ብለው የሚያዩት ይመስላችኋል?

ሁለተኛ፦ ከፓርቲውስ እሺ ይልቀቅ እንዴት ከፓርቲው ልሣን ከኢሳት ውሸት በቃኝ ብሎ ለቅቆ ይወጣል? ይሄም ትልቅ ድፍረት ነው። ለግንቦቴዎች።

“…ሦስተኛው ነገር ጋዜጠኛው እንዲህ ግንባር ድረስ እየሄደ፣ በተልእኮ የሚዘግቡትን የወሎ ፈረሶችን፣ የኢዜማ ካድሬዎችን፣ የብልጽግና አቃጣሪዎችን የሐሰት ዘገባ ላይ ዐመድ፣ አፈር እየደፋ፣ ሬንጅ እየለቀለቀ፣ ነጭ ነጯን እየተናገረ ሊለቁት ኖሯል? ዥል ሁላ…!

“…በዚያ ላይ ዐማራ ሆኖ፣ ያውም ናትናኤል መኮንን ዝቶበት ላይታሠር ኖሯል? ፓትርያርኩን በትግሬነታቸው ከፍ ዝቅ የሚያደርጉት፣ የሚያዋርዱት፣ አንተ እያሉ የሚሳደቡት እነ ናቲ ዝተው እናስ ላይታሰር ነው? ሶዬው እኮ ዐማራ ነው። ያውም የራያ ዐማራ። ዐማራን እንደ በግ እየነዱ ማሰርስ ብርቅ ነው እንዴ? 12ሺ ፋኖ እየተነዳ ሲታሰር ምንም ያላላችሁ የአንዱ ዐማራ የራየው ልጅ እስር እንዳንገበገባችሁማ አታስመስሉኣ? ኣ?

“…ናትናኤል ዛተ። እከሰዋለሁ ይሄን “ቆሻሻ” ዐማራ አለ። እነ ብሬ፣ እነ አንዲ ተባበሩት ጎበዜ ሲሳይ ታሰረ። በቃ አታክብዱ። አሁን የኦህዴድ ዳንኤል ብርሃኔዎች ጀንበራቸው እስክትጨልም ድረስ ዝም ብሎ መታዘብ ነው። ይህን በማለቴ ቅር የሚልህ ካለህ በአናትህ ተተከል።

“…ዛሬ ቀኑ የክበረ ክህነት ቀን ነው። ላስታውሳችሁ ብዬ ነው።

“…ዐማሮችዬ እየታሰራችሁ…!!

Filed in: Amharic