>
5:13 pm - Monday April 19, 5920

ወርቁን በመዳብ....!!! (ሸንቁጥ አየለ)

ወርቁን በመዳብ….!!!

ሸንቁጥ አየለ


1. መአዛ መሀመድን ለእስራት ያበቃት እውነት ነው።ይሄም ከሁለት ቀን በፊት በመንግስት መራሹ ኦነግ ሸኔ በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ እየተፈፀመ ያለው የዘር ጭፍጨፋ የወለጋ እልቂትን በሮሃ ሚዲያ ማስተላለፏ እና ለንፁሀን ድምፅ መሆኗ ነው።

2. ጎበዜ ሲሳይን ለእስራት ያበቃው እውነት ነው። ብልፅግና ከህወሀት ለውጥ የለውም አንድ ናቸው፣ህዝቡ ጦርነቱ መሮት ለመዝመት አልፈቀደም ምክንያቱም ወያኔ እንድትጠፋ ብልፅግና አይፈልግም የሚሉ እውነቶችን ለህዝብ ስለነገረ ለእስር ተዳርጓል።

3፡ በርካታ የህዝብ ድምጾች /እነ ተመስገን ደሳለኝን ጭምር/ በርካታ ፖለቲከኞች /እነ ስንታዬሁን ጭምር እንዲሁም / 15 ሽህ በላይ ፋኖዎች በእስር ቤት ያጎረዉ ብልጽግና ጠዋት ማታ የሚሯሯጠዉ የህዝብን እዉነት ያነሱትን ሁሉ ለመጨፍለቅ ነዉ፥፥

4፡ እነዚህ ወደ እስር ቤት የተጣሉት በሙሉ እነማናቸዉ ያልክ እንደሆነ ደግሞ ከነገደ አማራ ወገን ናቸዉ፥፥ ኦነግ ሸኔ ህዝብን በጅምላ  ሲጨፈጭፍ እና ከወያኔ ጋር በአደባባይ ቀለበት ሲያደርግ የባለጊዜዉ ኦህዴድ ከለላ አለዉና እንኳን ወደ እስር ሊጣል ቀርቶ ግልምጫ አይደርስበትም፥፥

የብልጽግና ባለጊዜዎቻና እና የኦነግ ሸኔዎችን የዘር ፍጅት ተከላካይ ባለስልጣኖች ግን ሀሰት ፈብርከዉ የሚቃወሟቸዉን ሁሉ ለማሸማቀቅ መአዛና ጎበዜ ከወያኔ ጋር ሲገናኙ ያዝናቸዉ ብለዉ ክስ መስርተዋል፥፥

እዉነትን በሀሰት ፥ ወርቁን በመዳብ የሚለዉጡት ባለጊዜዎች የእዉነት እንደበቶችን ሁሉ ለመዝጋት እየተሯሯጡ ነዉ፥፥

Filed in: Amharic