የአሮጌው አመት “የብልጽግና” በረከቶች….!
ወግደረስ ጤናው
~ ከ7ሺህ በላይ አማሮች በግፍ በኦነግ ኦሮምያ(ወለጋ) በሚባለው አካባቢ የታረዱበት እና ከ500 ሺህ በላይ ንፁሃን ከቤታቸው ተፈናቅለው ጎዳና የሚገኙበት፣
~ በኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫ ከ20 ሚሊየን በላይ ንፁሃን ከሞቀ ቤታቸው ተፈናቅለው ዛሬ ላይ በመጠለያ ጣቢያዎች በዕርዳታ ስንዴ አዲስ ዓመትን የተቀበሉበት፣
~”ሁለተኛው እና ሦስተኛው ምዕራፍ” እየተባለ በሰሜን ኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት ሺዎች ያለቁበት፣ሚሊየኖች የተፈናቀሉበት፣ሺዎች የቆሰሉበት፣በኢትዮጵያ ገንዘብ የማይተመን የሀገር ሃብት የወደመበት፣
~ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ፣አማራ ደግሞ አንደ ህዝብ የመጥፋት አደጋ በግልፅ የታየበት፣የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝብ በጎሳ ተከፋፍሎ እርስ በርስ የተጨራረሰበት፣
~ በኢትዮጵያ በተለይም የአማራ ህዝብ ጭፍጨፉ ተለምዶ “ስንት ሞተ?” እየተባለ ቁጥር ብቻ የሆነበት፤ሰው የረከሰበት፣ሞት የረከሰበት፣ስደት እና መፈናቀል የበዛበት፣
~ አድር ባይነት፣ፍራቻ፣ነውር፣ስርቆት፣ማስመሰል ባህል የሆነበት፤
የሀገር ፍቅር ጠፍቶ፣የጎጥ ፍቅር ነግሶ የታየበት፣ሰዎች በእምነታቸው እና በመንፈስ ቀጭጨው በቁስ እና በስጋ ሰቀቀን የወደቁበት፣
~ አዲስ አበባ በኦህዴድ ተረኛው ስርዓት በኃይል ልትሰለቀጥ አፍ ውስጥ የገባችበት፣ህፃናት በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉበት፣
~ ከ20ሺ በላይ ጋዜጠኞች፣ጦማሮች፣ ማህበረሰብ አንቂዎች፣የዮኒቨርስቲ ሙሁራን እና ተማሪዎች፣ሀገር ጠባቂ ፋኖዎች፣የፖለቲካ ፓርቲ አመራርና አባለት በኦህዴድ ማጎሪያ ቤት ታግተው አዲስ አመትን ያሳለፉበት
~የሀገር ጠባቂ ፋኖዎች፣ለሀገር የሚቆረቆሩ፣የስርዓቱን ነውር እና ተረኝነት የሚያወግዙ ጀግኖች በሙሉ ከመኖሪያቸው የተሰደዱበት፣በየጫካው የተበተኑበት፣አባት ከልጆቹ፣ልጆች ደግሞ ከቤተቦቻቸው የተለያዩበት ዓመት፣
~ በኢትዮጵያ ህዝብን የሚመራ ሳይሆን በዘር ተቧድኖ አገር የሚዘርፍ እና የሚያፈርስ፣ድንቁርና የተጠናወተው ነውር ዐልባ ስርዓት የተጫነበት ጊዜ ነበረ።
2015 ነውረኞች ቦታቸውን አግኝተው በየጫካው ያሉ ሀቀኞች ሀገሪቱን የሚረከቡበት ዘመን ይሁን!!!
አሜን!!