>
5:26 pm - Saturday September 15, 2959

አገዛዙ በኢትዮዽያ ሀሰተኛ የታሪክ ትርክት የማንበር ስራውን የመማሪያ መጻህፍትን በመበረዝ እያሳለጠው ነው! (ጌጥዬ ያለው)

አገዛዙ  በኢትዮዽያ ሀሰተኛ የታሪክ ትርክት የማንበር ስራውን የመማሪያ መጻህፍትን በመበረዝ እያሳለጠው ነው !

ጌጥዬ ያለው

በአዲስ አበባ ትምህርት ይቋረጥ!

ወራሪው ኦህዴድ፣ ብልፅግና አባቶች ቁጥር ፈጥረው እና ቀመር ቀምረው በሰጡት የዘመን ሰሎ እንቁጣጣሽን ሲያከብር ሰንብቶ ህፃናትን ደግሞ . . .የግዕዝ ቁጥር ከግሪክ መጣ. . . እያለ ውሸት ያስተምራል። ይህ ብቻ አይደለም፤ በርካታ ሸፍጦች እየተሠሩ ነው። ልጆችን ወደ  ትምሀርት ቤት ለመላክ በአገዛዙ እና በህዝብ መካከል መተማመን መኖር አለበት። አዲስ አበባን እየወረረ ያለው  ኦነጋዊ አገዛዝ ሕዝቡን በጠላትነት የፈረጀ ነው። የበቀል በትሩንም በህፃናቱ ላይ እያሳረፈ ይገኛል። ኗሪዎች ተኝተው ሲነቁ ቤታቸው ከሁለት ተገምሶ፤ ሳሎኑ ኦሮሚያ፣ ጓዳው አዲስ አበባ ሆኖ የመቆየት ያህል ተቸግረውል።

በዚህ ሁኔታ ሲገቡና ሲወጡ የሚሳሙ ህፃናትን ለሚዋጉ ወራሪዎች አሳልፎ መስጠት በመጭው ትውልድ ላይ መጨከን ነው። ባይማሩ ይሻላል፤ የስርዓት ለውጥ እስኪመጣ በተለይ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች፤ ትምህርት መቋረጥ አለበት።

ወራሪው የኦሮሞ አገዛዝ ቀዳሚ አላማው በኢትዮዽያ ሀሰተኛ የታሪክ ትርክት ማንበር ብሎም የታሪክ፣ የባህል፣ የቋንቋ፣ የመሬት፣ የሃይማኖት ወዘተ ወረራ መፈፀም ነው። ታሪክና ትውፊት ስርቆትም መገለጫው ነው። ይህንን በአደባባይ የሚተቹት ጥቂት ሊቃውንት ናቸው። አንዳዱ ነውሩን በስሙ ጠርቶ ማጋለጥ በራሱ የሚያስነውር እየመሰለው፣ ከፊሉም ለፖለቲካ አካታችነት (Political correctness) ሲል፣  ሌላውም የአገዛዙን ጡንቻ እንደ እንኩሽ በመፍራት በአርምሞ እያየው ይገኛል።

በሀገር ውስጥ በልኩ የሚተቹት ሀቀኛው ጋዜጠኛ እና የታሪክ ፀሀፊ ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ  ናቸው። ኮሽ ባለ ቁጥር  የሚያስራቸውም ለዚህ ነው። እሳቸውን አስሮ ግዕዝ አይደለም የግሪክ ነው፤ የገዳ ነው ቢልም ደፍሮ አስደንጋጭ የለውም ማለት ይቻላል።

Filed in: Amharic