>
5:21 pm - Wednesday July 20, 1588

በቅድሚያ ብአዴንን ማጥፋት አላማው የማያደርግ የአማራ ተጋድሎ የውሸት ትግል ነው...!

በቅድሚያ ብአዴንን ማጥፋት አላማው የማያደርግ የአማራ ተጋድሎ የውሸት ትግል ነው…!

አቻምየለህ ታምሩ


በየዩኒቨርሲቲው የምትገኙ የአማራ ወጣቶች በወለጋ ምድር በናዚ ኦነግና በኦሮሞ ልዩ ኃይል በጅምላ ለሚጨፈጨፉት የአማራ እንቦቀቅላዎች፣ ሴቶች፣ አዛውንትና አቅመ ደካሞች የስናፍጭ ቅንጣት ያህል ወገናዊ ስሜት ካላችኹ ብአዴን የሚባለውን የአማራ ግንባር ቀደም ባለደም በጉያችሁ ታቅፋችሁ አማራን እየጨፈጨፉ የሚገኙ ሌሎች ገዳዮችን ፍለጋ ሩቅ ቦታ መባዘን የለባችኹም። የአማራ ሕዝብ እውነተኛ ተጋድሎ የሚጀምረው ከሚገኝበት የቁም መቃብር ውስጥ መግነዙን ቀዳዶና በጣጥሶ የተጫነበትን የመቃብር ድንጋይና አፈር ፈነቃቅሎ እንዳይወጣ መቃብር ጠባቂ ይሆን ዘንድ የተፈጠረውን ብአዴን የሚባለውን የፋሽስት ወያኔ ነውረኛ ድርጀትና የናዚ ኦነግ ጉዳይ አስፈጻሚ በቅድሚያ በማስወገድ ነው።

ብአዴን የሚባለውን የአማራ ነቀርሳ በቅድሚያ ማጥፋትን አላማው የማያደርግ የአማራ ተጋድሎ የውሸት ትግል ነው። ስለዚህ በየዕለቱ በሺዎች የሚጨፈጨፈው የአማራ ነፍስ ከዶሮ ነፍስ ማነሱ የሚጣላ ሕሊና የፈጠረበት የአማራ ወጣት ቢኖር በቅድሚያ ተጋድሎውን ብአዴን የሚባለውን የአማራ ነቀርሳ በማጥፋት ይጀምር። ፋሽስት ወያኔን የተጋፈጡ ከአስር ሺህ በላይ የሚሆኑ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች በግፍ የታሰሩበትንና በርካቶች በጭካኔ የተገደሉበትን የኦሮሙማ ኦፕሬሽን የመራውን ይልቃል ከፋለ የሚባልን የአማራ ገዳይ ታቅፈህ፤ “አማራን መግደል ሕገ ወጥ ተግባር አይደለም” ያለውን ግርማ የሺጥላ የሚባል ጨካኝ አውሬን በጉያህ ይዘህ ሌላ ጠላት ፍለጋ መባዘን ጅልነት ነው።

Filed in: Amharic