>

ሁሌም ማምለጫችሁን "ኦሮሞ ፊቢያ" ያደረጋችሁ የፖለቲካ ቁማርተኞችና አወናባጆች - አታምታቱን ...!  ( ግርማ ካሳ)

ሁሌም ማምለጫችሁን “ኦሮሞ ፊቢያ” ያደረጋችሁ የፖለቲካ ቁማርተኞችና አወናባጆች – አታምታቱን …! 

( ግርማ ካሳ)


እውነቱ ሲነገር “ኦሮሞፎቢያ” እያሉ ይጮሃሉ፡፡ አንዳንዶች፡፡ ኦሮሞን መጥላት ወይም መፍራት ማለታቸው ነው፡፡

እየተጠየቀ ያለው በኦሮሞ ክልል ኦሮሞ ያልሆኑትን ሌሎች ማህበረሰባትን መጤ ሰፋሪ እያሉ መጨፍጨፍ ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጻዳት ወንጀሎች መፈጸም ይቁሙ ነው፤፡

እየተጠየቀ ያለው ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ አማራ ሳይባል፣ የዘር ልዩነት ሳይኖር ሁሉም ዜጋ በሁሉም አገሪቷ ክፍል እኩል ይሁን ፣ በሰላም ወጥቶ ይግባ የሚል ነው፡፡

እየተጠየቀ ያለው አገርን እያፈረሰ ያለ፣ በተለይም ኦሮሞን ያቆረቆዘው ፣ ለኦሮሞ ችግር፣ ጦርነት፣ ከሌላው ጋር መቃቃር፣ ድህነት እንጂ አምስት ሳንቲም ጥሩ ነገር ያልፈየደው የጎሳና የዘር፣ የጥላቻና የመከፍፈል ፖለቲካ፣ ህገ መንግስትና የፌዴራል አወቃቀር ይቀየር ነው፡፡

እየተጠየቀ ያለው የአዲስ አበባ ሕዝብ የራሱን እድል በራሱ ይወስን፣ ራሱን በራሱ ያስተዳድር፣ የሚፈልገውን ባንዲራ፣ የሚፈልገውን ህዝብ መዝሙር፣ እርሱም የኢትዮጵያን ብቻ፣ ያውለብልብ፣ ይዘምር ነው፡፡

እየተጠየቀ ያለው በኦሮሞ ክልል ውስጥ ያሉ ኦሮሞ ያልሆኑ በብዛት ባሉባቸው አካባቢዎች በአማርኛ መንግስታዊ አጋልግሎት ይሰጣቸው፣ የራሳቸውን እድል በራሳቸው በዞን ይሁን በወረዳ ደረጃ ያስከብሩ ነው፡፡ ለምሳሌ የናዚርተ ከተማ ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ ይከበርለት፣ የራሱን ከንቲባ ይምረጥ፣ ህዝቡ በሚፈልገው ቋንቋ ይተዳደር፣ በሚፈልገው ቋንቋ አገለግሎት ይሰጠው ነው የተባለው፡፡

Filed in: Amharic