የኦሮሞን ህዝብ ጠበቃ አሰሯቸው!
ጌታቸው ሽፈራው
*…. ወንድሙ ኢብሳ አዳነች አቤቤን፣ ጃዋርን፣ በቀለንና ጃል ማሮን የተቃወሙባቸው ቃለመጠይቆች አሉ። በልጻጊዎቹ እነዚህን ሁሉ በየሚድያው የሚያፍን ውርጋጥ አላቸው
ወንድሙ ኢብሳ ይባላሉ። ጠበቃ ናቸው። እንደወንድሙ ኢብሳ ለህዝብ ጥብቅና የቆመ አላውቅም። በትህነግ ዘመን በርካቶች በማንነታቸው በሚታሰሩበት ወቅት ጠበቃ ለቸገራቸው የኦሮሞ ልጆች በነፃ “እኔ አለሁ” የሚሉት ወንድሙ ኢብሳ ነበሩ። ጥብቅና የሚቆሙላቸው ተከሳሾች ከመብዛታቸው የተነሳ ተከሳሾች ተራቸው ደርሶ በተጠሩ ቁጥር ወንድሙ ተነስተው “የእኔ ልጆች ናችሁ?” ብለው ይጠይቃሉ። “አዎ” ከተባሉ ከሚይዙት መአት መዝገብ መሃል ሰነዱን ያተረማምሱና ጥብቅና ብቻ ሳይሆን ትግል ይጀምራሉ። እስረኞች ተደበደብን ብለው ካመለከቱ አገር ይያዝልኝ ብለው ይሟገቱላቸዋል።
ወንድሙ ለኦሮሞ ወጣቶች ብቻ ጥብቅና አልቆሙም።”ጠበቃ አለህ?”ተብሎ ተጠይቆ “የለኝም” ለሚለው ሁሉ “እኔ አለሁ” ብለው ይነሳሉ። በነፃ! ወንድሙን የኦሮሞ ጠበቃ ያልኳቸው ያሰሯቸው ከእኛ በላይ ኦሮሞ የለም የሚሉት ስለሆኑ እንጅ ከየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ለሚመጡት ሁሉ ጠበቃ ናቸው።በአንድ ወቅት ብቻ በትንሹ ለ600 እስረኞችን በነፃ ጥብቅና ቆመውላቸዋል።
ትናንት አቶ ወንድሙ መታሰራቸውን ሰማሁ። የተወሰኑ ቃለ መጠይቅ አይቸ ነበር። ቴዲ አፍሮን አደንቀዋለሁ ያሉበትን ጨምሮ የተወሰኑትን ብቻ ለማሳያ፥
#ወንድሙ ኢብሳ አዲስ አበባ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ የኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ መሰቀል የለበትም ብለው ተቃውመዋል።
#ወንድሙ ኢብሳ አዳነች አቤቤን፣ ጃዋርን፣ በቀለንና ጃል ማሮን የተቃወሙባቸው ቃለመጠይቆች አሉ። እነዚህ ሁሉ የሚያፍን ውርጋጥ አላቸው።
#ወንድሙ ኢብሳ የአኖሌን ታሪክ አይቀበሉም። አሊያም የወገን ታሪክ ነው ብለው ያምናሉ።
ወንድሙ ኢብሳ የኦሮሚያ ባንዲራ ይሰቀል ብለው የሚበጠብጡትን “ህወሓት ባመጣው ባንዲራ ከወገኔ ጋር አልጣላም” የሚሉ ናቸው።
አሁን ስልጣን ላይ ያለው ፅንፈኛ ሁሉ ያኔ ለውጥ ለውጥ ብሏል። የለውጡ አካል ግን እነ ወንድሙ ናቸው። ታግለዋል። ስልጣን ላይ ያሉት የኦሮሞ ህዝብ ጥቅምን እናስጠብቃለን ይላሉ። ለኦሮሞ ግን ስልጣን ላይ ያሉት አሳሪ፣ ወንድሙ ጠበቃው ነበሩ። ሰሞኑን ስለ አዲስአበባ ተናገሩ ብለው፣ የኦሮሚያ ባንዲራ በየ ትምህርት ቤቱ መሰቀል የለበትም ብቻ ሳይሆን ወያኔ ባመጣው ከወገናችን ጋር አታቆራርጡን ስላሉ ሰበብ ፈልገው አሰሯቸው። መቸም አያፍሩም ወንድሙን በሚተቹት ኦነግ ሸኔ ስም ጠረጠርንህ ይሏቸው ይሆናል። ይህ ኃይል የሆነ አጋጣሚ ሲያገኝ ነገም “ለውጡ” ብሎ ለማውራት አያፍርም።