>

"…አሸበርቲዎቹ…!! (ዘመድኩን በቀለ)

“…አሸበርቲዎቹ…!!

ዘመድኩን በቀለ

“…የኢትዮጵያ ፌደራል ፎሊስ ነፍሴ መምህር ምሕረተአብ አሰፋንና የነገረ መለኮት ምሩቋን መምህርት ፌቨን ዘሪሁንን ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ በሚል ከባድ ወንጀል ከሷቸዋል።

የችሎት ውሎ…!!

መምህር ምህረተአብ አሰፋና

• መምህርት ፌቨን ዘሪሁን (ቲዮሎጂ ምሩቅ ናት) ሕገመንግሥቱን በኃይል ለመናድ ተባሉላችሁ። እልልል በሉ ምእማናን። አሸበርቲ ተባሉላችሁ። እንደ አልሸባብ፣ እንደ አልቃይዳ ማለት ነው። አሸበርቲ ተባሉላችሁ። ወይ አሸበርቲ…? 

“…ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ላይ በተፈጠረ ችግር ምክንያት ለአስር የተዳረጉት የእምነቱ ተከታይ ምእመናን እና መምህራን በሁለት ተከፍለው ልደታ ምድብ ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጊዜ ቀጠሮ ከ5 በላይ ከሆኑ ጠበቆቻቸው ጋር ቀርበው ነበር። 

1. የመጀመሪው ተጠርጣሪዎች መዝገብ የተከፈተባቸው በእነ ፌቨን ሰም ነበር ይኸውም፦  

1. ፌቨን ዘሪሁን  

2. ብሩክታዊት ነብዩ  

3. መሳይ ተፈራ  

4. ተካልኝ ኢቲቻ 

5. ወንደሰን ንጉሴ 

6. ረ/ሳጅን ሰራዊት ጸጋ  

7. ፋሲል አግደው 

2. በሁለተኛው ተጠርጣሪዎች መዝገብ የተከፈተባቸው በእነ መምህር ምህረተኣብ አሰፋ ሲሆን እነሱም፦ 

1. መምህር ምህረተአብ አሰፋ 

2. አማኑኤል አያሌው 

3. ኪሩቤል አሰፋ 

4. ሰይፉ አለማየሁ 

5. ኮንስታብል እጅጋየሁ ዳርጌ ናቸው 

ፍ/ቤቱም በጠበቆቹ እና በፖሊስ የተደረገወን ክርክር ከሰማ በኋላ፦  

1. ፌቨን ዘሪሁን  

2. ብሩክታዊት ነብዩ 

3. ፋሲል አግደው 

4. መምህር ምህረተአብ አሰፋ 

5. አማኑኤል አያሌው 

6. ኪሩቤል አሰፋ … በእነዚህ ላይ ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀን ውስጥ ተጨማሪ ምርመራ 8 ቀን ፈቅዶ…

1. መሳይ ተፈራ  

2. ተካልኝ ኢቲቻ  

3. ወንደሰን ንጉሤ 

4. ረ/ሳጅን ሠራዊት ጸጋ 

5. ኮንስታብል እጅጋየሁ ዳርጌ የተባሉትን ተከሳሾች ደግሞ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ ምርመራ አያስፈልግም በማለት እያንዳንዳቸው በ15 ሺ ብር ዋስ እንዲወጡ ፈቅዷል። 

6ኛ ተጠርጣሪ 4. ሰይፉ አለማየሁ በ30 ሺ ብር ዋስ እንዲወጣ ፈቅዷል፡፡ ብላኝ ነገር ግን ዘመዴ ከ1 እስከ 5 የተዘረዘሩት 15 ሺ ብር የመክፈል አቅም የላቸውም ብላኛለች ርግቤ።

“…በተለይ ጠበቆቹንም ዳኞቹንም ታዳሚዎችንም ፈገግ ካስባለውና ያስገረማቸው ደግሞ በእነ ምህረተአብ መዝገብ ከተዘረዘሩት ተከሳሾች በ4 ኛው ተራ ቁጥር ላይ የተጠቀሰው አቶ ሰይፉ አለማየሁ ማስረሻ የተባሉት እስረኛ የኮመርሽያል ተቋም ማናጀር ሲሆን በፖሊስ ተጠርጥሮ የተያዘው የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ እና አንዳንድ ነገሮች በፌስ ቡክ ላይ ሼር አድርገሃል ተብሎ መሆኑን። 

“…በተራ ቁጥር 5 ላይ የተከሰሰችው ኮንስታብል እጅጋየሁ ዳርጌ አዲስ የተባለችው የፖሊስ አባልም በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለችው የፖሊስ ደንብ ለብሳ እኔም ለሃይማኖቴ በማለት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ፎቶዋን ለጥፋለች ተብላ ነው። አሁን 15 ሺ ብር ዋስትና ተብላ ከየት ታምጣ?

ዝርዝሩን ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ያንብቡት።

http:///ZemedkunBekeleZ

Filed in: Amharic