አባቶች ተክደዋል፣ ልጆቻቸውን አብይ እያሰረ፣ ከስራ እያባረረ ነው…!
ግርማ ካሳ
በቤተ ክርስቲያን ላይ፣ በኦህዴድ/ኦነጎች የተከፈተውን ጥርነት ተክትሎ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ባቀረበው ጥሪ መሰረት፣ ህዝበ ክርስቲያኑ እንዲሁም የኦርቶዶስክ ቤተ ክርስቲያን ወዳጆች ድምጻቸውን ማሰማታቸው ይታወሳል፡፡ በነነዌ ጾም ወቅት ጥቁር በመልበስና ቤተ ክርስቲያናትን በመጠበቅ፡፡ በርካታ የሜዲያ ሰዎችን ፣ የሶሻል ሜኢድያ አክቲቪስቶች ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጎን ቆመዋል፡፡ እውነትን በማቅረብና በመዘገብ፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከአብይ አህመድ ጋር ተቀምጠው፣ ስምምነት እንደተደረገና፣ ሌላ ሲኖዶስ ለመፍጠር የተነሱ ከድርጊቶቻቸው እንደተቆጠሩቡ፣ እንደተመለሱ አሳውቀውናል፡፡ ከአብይ አህመድ ጋር የተረደረገውን 10 ነጥብ ያለበት ስምምነት አሰነብበዉናል፡፡
ከዚያ በኋላ ቅዱስ ሲኖዶስ አገር ሰላም ብሎ የተቀመጠ ይመስላል፡፡ ቁጥራቸው እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ ወገኖች ታስረው፣ አሁንም እየታሰሩ ባለበት፣ ብዙዎች ጥቁር ለበሳችሁ ተብለው ከስራ የተባረሩና እየተባረሩ ያሉ ባለበት፡፡
አባቶች የሚያደርጉት የሚያወቁ ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ እስካእአሁን ለነበራቸው ላሳዩት አስደማሚ አምራር፣ ብልህነትቸው፣ አስተዋይነታቸው የሚደነቅ ነው፡፡ ሆኖም ግን የነርሱ ዝምታ ምችት አልሰጠኝም፡፡
አብይ አህመድ፣ በዚህ ስምምነት አድርገባል እያለና አባቱንች በተራቃላት እየሸረደደ፣ በጀርባ ግን ሰይጣናዊ ተግባራቶችን ከአዳነች አበቤና ሺመለስ አብዲሳ ጋር ሆኖ እየሰራ ነው፡፡ ስምምነት ተደረገ ከተባለ በኋላ ብዙዎች እየታሰሩ ነው፡፡ ብዙዎች ከስራቸው እየተባረሩ ነው፡፡ የበቀል እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው፡፡ ታዲያ አባቶች ለዚህ ምንድን ነርው ምላሻቸው ? “ክብሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ” ያሉት በዚህ ልክ ክህደት ሲፈጽምባቸው ?
የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከአብይ ጋር የተስማሙበት አስር ነጥብ ላይ፣ አብይ አህመድ የታሰሩትን እንደሚፈታ፣ ከሞቱት ካሳ እንደሚከፍል መቀመጥ ነበረበት፡፡ ግን ባይቀመጥም፣ ቢያንስ በቃል ተስፋ እንደገባላቸው መፈጸም ነበረበት፡፡ ያ አልሆነም፡፡ እነርሱም ለዚያ ተጠያቂ አላደረጉትም፡፡ ይሄ ትልቅ ስህተት ነው፡፡
ነገ ቅዱስ ሲኖዶሱ ላያ ሌላ አደጋ ሲፈጸም፣ እነ አብይ እስካሉ ድረስ መፈጸሙ አይቀርማን፣ ሌላ ጥሪ ቢያቀርቡ፣ “ትንሽ ቆይተው ደግሞ ይስማሙና ለኛ ግድ አይሰጣቸውም” የሚል አመለካከት ሊኖር ስለሚችል ፣ ብዙ ድጋፍ ላያገኙ ይችላሉ፡፡ የነ አብይ አህመድም አላማ ይሄው ነው፡፡ ህዝቡ እንደዚያ እንዲያስብ፣ በህዝቡና በሲኖዶሱ መካከል ክፍተት እንዲኖር ያደርጉና፣ ሲኖዶሱን ከህዝብ ነጥሎ፣ ለብቻቸው ሲያገኛቸው አሁን ያልተሳካላቸውን ያኔ በቀላሉ ያሳካሉ፡፡