ርዕሰ አንቀጽ
መምህር ዘመድኩን በቀለ
“…3 ሺ አመስገኝ ሞልተናል። አሁን በቀጥታ ዛሬ ማታ በኢትዮ ቤተሰብ፣ እና በእኔም ቲክቶክ ለሁለተኛ ጊዜ የጀመርነውን የሻሸመኔ ክርስቲያኖች ርዳታ የማሰባሰብ መርሀ ግብር እስክንጀምር ድረስ በዚያው ዙሪያ ስንወያይ እንውላለን።
“…የጀመርኩትን ከግብ እስካደርስ ድረስ ስለሰውበሰው ተጫነ አላወራም። የኦሮሞ ገዢዎች የሲዳማን ገበሬዎች ለስብሰባ ጠርተው ስለመረሸናቸውም አላወራም። ገና መች ጀመረውና ኦነግ ሲዳማን በቀጣይ እንደጉድ ያርደዋል። ታዲያ ሲዳማን ከደቡብ የነጠለው ለምን ሆነና? ሃኣ…? አሁን ሌላው ደቡቤ ሲዳማን ኦሮሞ ሲበላው “የትአባቱ ይበለው” እንጂ ትንፍሽ አይላትም። ሊረዳውም አይሞክርም። መጨረሻ ላይ የኦሮሞው ወራሪ ሁሉንም እንደሚበላቸው አላወቁምና አሁን ነጣጥሎ ያስቀመጣቸው ለጌጥ ስለሚመስላቸው አይተነፍሱም። እናም ሲዳማ ከነእግሩ ከነ አንጀት ሆድ አዋሳ ከተማው ገና በኦሮሞ ይዋጣታል። ግን እኔ አሁን ስለእሱም አያገባኝም። ሃሳብም አልሰጥም።
“…በዘር ዐማራን ማሳነስ ያልቻለው የኦሮሞ ብልፅግና ዐማራን በሃይማኖት ገብቶበት እያመሰው ነው። ታርጌት የተደረገው ደግሞ ጎጃም ነው። ከጎጃምም ምሥራቅ ጎጃም። የሊቃውንት ሃገሩ ምሥራቅ ጎጃም አሁን በፀጋ፣ በቅባት እና የዓለም ብርሃን በሚባል አዲስ ሃይማኖት ተወጥሯል። ጎጃምን አሳንሶ የመበረዙ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የዓለም ብርሃን የሚባለው እና ቤዙን ሱሉልታና እስራኤል፣ አዲግራትም አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የምጽአት ቀን ናፋቂ ቡድን ብልፅግናው መንግሥት የጦር መሣሪያ ድጋፍ ሁላ እየተደረገለት እና ለጦርነት እየተዘጋጀ እንደሚገኝ መረጃው ቢደርሰኝም አሁን ስለ እሱ አልተነፍስም።
“…ይሄም ብቻ አይደለም ያለው መከራ አልበቃ ብሎ ህወሓት በመርፌ ዘሩን ያመከነችው ዐማራ አሁን ደግሞ ብልፅግና ሌላ ዙር ዘር ማምከኛ ዕቅዱን ዘርግቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ሆን ብሎ የዐማራ ክልል ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲ እንዳይገቡ ካደረገ በኋላ በሀገሯ ወሃቢያ እንዳይኖር በሕግ ደንግጋ ወሀቢያን ለአፍሪካ ኤክስፖርት ከምታደርገው ሳዑዲ አረቢያ ጋር ተነጋግሮ ሥራ አጡ የተማረ ወጣት ፋኖ እንዳይሆኑበትና መንግሥቱን እንዳይገዳደረው በማሰብ የተማረውንና ፊደል የቆጠረውን የዐማራን ወጣት ኃይል በተለይ ደግሞ ሴት ዐማሮችን ዘራቸውን በመበረዝ እስላምም በማድረግ የዐማራ ወጣት ሴቶች በግርድና ስም ስለታቀደው ፕሮጀክትም አላወራም።
“…በተለይ ከሰሜን ሸዋና ከምሥራቅ ጎጃም በብዛት ለማጋዝ የተጀመረው ፕሮጀክት ወደፊት በዚያውም የኦሮሞ ወራሪ ኃይል በኋላ ወደ ጎንደር ለሚደረገው ወረራ ከሸዋና ከጎጃም ሊገጥመው የሚችለውን ተግዳሮት ለመቀነስ በማሰብ ነው ሴቱን ሁሉ እስላም በማድረግ ለግርድና ሊሸጠው የተዘጋጀው ብዬም አሁን ትንፍሽ አልላትም። አፄ ኃይለሥላሴ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የጀርመን መንግሥት ኢትዮጵያውያን በብዛት ገብተው በጀርመን መልሶ ግንባታ ላይ ይሳተፉ ዘንድ በዚያውም ዜግነትም ከፈለጉ ጀርመናዊ ሆነው ይኖሩ ዘንድ ቢጠየቁ “በፍጹም አይደረግም” በማለት መከልከላቸውንና ለዳግም ሌላ ቀኝአዙር ቅኝአገዛዝ ሕዝቤን አልዳርግም ማለታቸውና ከኢትዮጵያ ምላሽ ያጣችው ጀርመን ለቱርክ ጥያቄ አቅርባ ቱርክም በደስታ ተቀብላ በጦርነት መግባት ያልቻለችው አውሮጳ በቀንሠራተኝነት በወዛደርነት ገብታ ዛሬ ጀርመን ቱርክ ኢስታንቡል መስላ እንድትታይ ሆኗል። ዐማራን ፊደል የቆጠረ ገረድ ለማድረግ እየተሠራ ስላለው ፕሮጀክትም አልናገርም።
“…እኔ ዛሬም ነገም ተነገወዲያም የማወራው በኦሮሞ ፅንፈኛ እስላሞችና በኦሮሞና በደቡብ ፅንፈኛ የጴንጤ በለሃብቶች እና ባለ ሥልጣናት አማካኝነት በሻሸመኔ ከተማ በግልፅ የተፈጸመውን የኦርቶዶክሳውያን የዘር የማጥፋት ወንጀል እያጋለጥኩ በዚያውም ለኦርቶዶክሳዊያን ሕጻናት ይሄን ክፉ የጽንፈኞች ድርጊት በምስል እና በቪድዮ እያዩ ለወደፊት ዘራቸው እንዳይጠፋ ከወዲሁ መፍትሄ እየፈለጉ እንዲያድጉ እየመከርኩ፣ ለቆሰሉት እና እስከአሁን በፅንፈኛ እስላሞቹና በአክራሪ ኦርቶዶክስ ጠል ጴንጤዎቹ የተጎዱትን ወገኖቻችንን አለሁላችሁ ስል ነው የምውለው።
“…አንድ ቀን ሳይሞላን በ2 ሰዓት ገለጻ ብቻ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገባው ብር ሳይቆጠር በጎፈንድሚ ብቻ 45,242 ዶላር ደርሰናል። ዛሬም መወትወቴን እቀጥላለሁ። ዐውቃለሁ ሱማሌ ተርቧል፣ ቦረናም ተርቧል። ደቡብም ተርቧል። ዐማራም፣ ትግሬም ተርቧል። ዐውቃለሁ ብዙ ወጪ በዝቶባችኋል። ሰሞኑን እንኳ ፍጻሜውን ያሳምርለት እንጂ በአይበገሬውና በጠንካራው ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አማካኝነት ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል ግንባታ ለሚሠራው ህንፃ በርና መስኮት ማሠሪያ ስታዋጡ ነው የከረማችሁት። ያረፋችሁበት ጊዜና ሰዓትም የለም። እንግዲህ ምን ይደረግ? መፍትሄው እርስ በእርሳችን በመረዳዳት እና ይሄን ራሳችን ጨካኝ ያደረግነውን ዘመን በጥበብ ማለፍ ብቻ ነው። ለጊዜው ሌላ አማራጭ የለም። ቆይቼ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ። እስከዚያው ድረስ…
•ይሄ የንግድ ባንኩ ነው። 1000525914619
• ይሄ
• እየለገሳችሁ…!