>
5:31 pm - Thursday November 12, 3265

የልዩ ሃይሉ ፍርሰትና የአማራ ብሄራዊ ጦር ግንባታ (ጌጥዬ ያለው)

የልዩ ሃይሉ ፍርሰትና የአማራ ብሄራዊ ጦር ግንባታ

ጌጥዬ ያለው

በርግጥ የመሳፍንት ስርዓት በራሱ ከሥልጣን ሽኩቻ የዘለለ ክፋት አልነበረውም። የውጭ ወራሪ ሲመጣ የውስጥ ልዩነቱን ትቶ ጠላትን የሚያደባይ ክንደ ብርቱ ነበር። ዘመነ መሳፍንት  እንደ ዛሬው ዘመነ ወራሪያን ኢትዮጵያን የሚበትን ብሄራዊ ስጋት አልነበረም። ሆኖም የኢትዮጵያ በአንድ ማዕከላዊ አስተዳድር ስር መሆን ሸጋነቱ አያጠያይቅም። ስለዚህ ስለ ላቀው የኢትዮጵያ አንድነት፣ ስለ ዘመናዊት ኢትዮጵያ ካሣ ኃይሉ ጫካ ገባ፤ ታገለ። 
ታዲያ መይሰው ካሣ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጦር ሲገነባ ዳገት የሆነበት በመሳፍት ክፍፍል የተያዘው ሰራዊት ነበር። ሆኖም ጀግንነቱ፣ ቆራጥነቱ እና ሞት አይፌነቱ ሁሉንም ድል እያደረገ ርዕዩን እውን ለማድረግ አስቻለው። በመሳፍንት የተከፋፈለች ኢትዮጵያንም አንድ አደረጋት። የዚህ ወቅት የአማራ ትግልም በሕዝቡ ላይ የታወጀበትን የዘር ፍጅት አስቁሞ ህልውናውን ለማስቀጠል፣ በብሄር የተከፋፈለች ኢትዮጵያን ወደ ቀደመ አንድነቷ ለመመለስ፣ ወደ መንበረ ሥልጣን ለመውጣት የቴዎድሮስን መንገድ መከተል አለበት። ለዚህም ሰሞነኛው የአማራ ልዩ ሃይል እንቅስቃሴ አጋዥ ነው። 
ዘመነ ወራሪያን ኢትዮጵያን በብሄር ሰነጣጥቆ እየበተናት ይገኛል። ለመበተን የቆመቺበትን ምሰሶ መንቀል ማለትም አማራን ማጥፋት ደግሞ የሁሉም ወራሪዎች የጋራ ቀዳሚ አጀንዳ ነው። ለዚህም አማራውን ያለ ተከላካይ ለመደለቅና ለማጥፋት የአማራ ልዩ ፖሊስን ትጥቅ ማስፈታት ብሎም ከነአካቴው መበተን አስፈላጊ ሆኗል። ይህንን ተቀብሎ የጠላትን ትዕዛዝ መፈፀም ለአማራው ራስን ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ እንደመወርወር ይቆጠራል። ምርጫው ሁለት ነው፤ ወደ ገደሉ መግባት ወይም ወደ ተራራው መውጣት።
ወደ ተራራው ለመውጣት አሻፈረኝ ማለትና የአማራን ብሄራዊ ጦር ግንባታ ማጠናከር ተገቢ ነው። እያንዳዱ የአማራ ልዩ ሃይል አባል የያዘውን ጠመንጃ ለአፍታም ቢሆን ከእጁ መነጠል የለበትም።  ጠላቶቻችን ምላጭ ለመሳብ ዝግጁ ናቸው፤ እየሳቡም ነው። ስለዚህ አይደለም ትጥቅ መፍታት፤ ጥብቅ መዝጋት አይገባም። 
የአማራ ልዩ ሃይል የብአዴን የግል ንብረት አይደለም። ብአዴን ፈቀደም/ከለከለም፣ ኦነጋውያን ፈለጉም/አልፈለጉም አንድም ጓድ ሳይነጠል መቀጠል አለበት። የአማራ ሕዝብ ተቋምነቱን ማስመስከር ይገባዋል። ወትሮም የወታደር ወጉ ይህ ነው። በአንድ ስርዓት ጭብጨባ የሚለመልም፤ በጥቂት ወራሪዎች ርግማን የሚኮሰምን ሰራዊት ሕዝባዊ ሊሆን አይችልም። ይህ ሰራዊት ከእነሙሉ ትጥቁ ከአገዛዙ መዋቅር ለመውጣት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ መቀጠል አለበት። እንቅስቃሴውም የአማራ ብሄራዊ ጦር ግንባታ አካል ይሆናል። ለጦሩ ግንባታ የሚከተሉት ተግባራት በጥይት ፍጥነት ሊፈፀሙ ይገባል፦ 
1. የአርበኛ ዘመነ ካሤን ጥሪ ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ በአስቸኳይ ጊዜያዊ ወታደራዊ ካምፖችን ማቋቋምና እየተበተነ ያለውን ሰራዊት መሰብሰብ2. በጊዜያዊ ካምፖች የተሰበሰበውን ሰራዊት በበረሃና በከተማ ካለው የፋኖ መዋቅር ጋር ማዋሃድ3. የአማራ መደበኛ ፖሊስ እና የአማራ ሚሊሻ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ውህድ ሰራዊቱን እንዲቀላቀሉ ማድረግ4. በሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ በፌዴራል ፖሊስ፣ በአዲስ አበባ ፖሊስ፣ በእስር ቤቶች ፖሊስ እና በሌሎችም ወታደራዊ ዘርፎች ውስጥ ያሉ አማሮች ውህድ ሰራዊቱን ማለትም የአማራን ብሄራዊ ጦር እንዲቀላቀሉ ማድረግ5. የአማራ ሕዝብ በስንቅና ተጨማሪ ትጥቅ ሰራዊቱን እንዲያገለግል ዕድል መስጠት፣ ብሄራዊ የውዴታ ግዴታ መጣል6. በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ የሚኖሩ አማራ የፖለቲካ ልሂቃን በተለይም የውትድርና፣ የመረጃ ጥናት እና የካርታ ዝግጅት ሙያ ያላቸው ምሁራን በሀገር ውስጥ ሆነው የእንቅስቃሴው አካል እንዲሆኑ ብሄራዊ የውዴታ ግዴታ መጣል7. ከላይ የተጠቀሱት ስድስት ተግባራት ከተፈፀሙ በኋላ፤ ሁሉን አቀፍ ጊዜያዊ የአማራ መስተዳድርን ማቋቋም                                                                                                            

ይህ የሚቋቋመው ጊዜያዊ መስተዳድር ከወራሪዎች ጋር የምናደርገውን ጦርነት ይመራል። ብሄራዊ ጦሩም ተጠሪነቱ ለዚህ መስተዳድር ይሆናል። እዚህ ላይ የብአዴን ጉዳይ ከፍተኛ ፖለቲካዊ ውሳኔን የሚሻ ነው። ነገር ግን ከውሳኔው አስቀድሞ የሚከተሉት ጥያቄዎች መመለስ አለባቸው፦ 
1. ብአዴን በጦርነት ውስጥም የኦሮሙማ ተላላኪነቱን ይቀጥላልን?2. ከኦነግ-ብልፅግና ራሱን እንዲያገል ማስገደድ ይቻላልን? በራሱ ተነሳሽነትስ ራሱን ያገል ይሆን?3. ራሱን አክስሞ የጊዜያዊ መስተዳድሩ አካል ለመሆን ይፈልግ ይሆን? ቢሆንስ ከብአዴናውያን ጋር መሥራት ፋታ ከማይሰጠው የጦርነት ጊዜ አንፃር፣ ከፖለቲካ ትርፍና ኪሳራ አንፃር፣ ከሞራል ተጠየቅ አንፃር እንዴት ይገመገማል?4. በተቋሙ ውሰጥ ያሉ አንጃዎች ተብተው ይፈረካክሱት ይሆን? ከሆነ፤ መፈረካከሱ በጊዜያዊ መስተዳድሩ ላይ የሚፈጥረው አፀግብሮት ምንድን ነው?5. የሚቋቋመው ጊዜያዊ መስተዳድር በሥልጣን ላይ ያለውን የአማራ መስተዳድር በሃይል መደምሰስና ቢሮውን ተቆጣጥሮ መቀጠል ይችል ይሆን? ከሆነስ፤ ይህ ወራሪዎች ከሚከፍቱብን ግልፅ ጦርነት አንፃር እንዴት ይጤናል?
በእነዚህ ሂደቶች ውስጥ ሊገጥሙን የሚችሉ በርካታ ችግሮች ይኖራሉ። ነገር ግን ታላላቆቹ ችግሮች አማራው ሕዝባዊ መስመራዊ ጦርነትን እስኪጀምር ብቻ የሚቆዩ ናቸው። አማራ በጦርነት ውስጥ ድል ግብሩ ነው። ታሪክ መሥራት ተፈጥሯዊ ባህሪው ነው። ጠላት የቱንም ያህል ተዛዝሎ ቢመጣ ከፊቱ ሊቆም አይችልም። ለዚህ አድዋ ምስክር ነው። መከላከያ ሰራዊቱ የዓይን እማኝ ነው። ይህ የትግሬ ወራሪዎች መካድ ያልቻሉት ሀቅ ነው። በመሆኑም የሚገጥሙ ችግሮች ሁሉ በድል ይሸፈናሉ። ችግሮቻችን ሁሉ በዙሪያችን የሚቆዩት “ጦርነት መፍትሄ ነው” ብለን እስክናምን ነው። ከእስራኤል የምንማረው የጦርነትን መፍትሄነት ነው። 
በአጠቃላይ የአማራ ልዩ ሃይል ከአገዛዙ መዋቅር መውጣት የአማራ ብሄራዊ ጦር ግንባታ አካል ነው።

Filed in: Amharic