ሾተላዮቹ!
መምህር ዘመድኩን በቀለ
“ርዕሰ አንቀጽ”
“…ሾተላይ ክፉ ነው። ጽንስ ያጨናግፋል። በኢትዮጵያ ቦለጢቃም ነፍ የትየለሌ ሾተላዮች አሉ። ነፍ ናቸው። የዝሆን ቆዳ የታደሉ። መስሚያቸው ጥጥ የሆነ፣ ነውራቸው በክብራቸው የሆነ ነውር ጌጡዎች፣ ፈጣጣ፣ ሼምለሶች፣ ይልኝታ ቢሶች ነፍ ናቸው። የዛሬው ርዕሰ አንቀጼ እነዚህን ሾተላይ ፕላን C ዎችን እንጠንቀቃቸው የሚል ነው። ፕላን C ዎች አደገኞች ናቸው። ፕላን C ዎች ሃይማኖት የላቸውም። አፈ ቅቤ ሆደ ጩቤዎች ናቸው። የእስስት ባህሪ ነው ያላቸው። የድል አጥቢያ አርበኞች ናቸው። ፕላን C ዎች ክፉ አደገኛ ሾተላዮች ናቸው። የደረጀ፣ የጎመራ፣ ለፍሬም የደረሰ ትግል ደርሰው አጨናጋፊዎች ናቸው። መርዝ፣ ደፋር፣ እናቱን ለመሸጥ፣ ሚስቱን ለመካድ ቅሽሽ የማይለው ነው ፕላ C። የአፍ ጅዶ፣ የምላስ ካራቲስቶች ናቸው። እሳቱ ደመራውን በልቶ ሲጨርሰው የደመራውን የመውደቂያ አቅጣጫ የዘመመበትን አይተው ደመራውን መውደቂያ ነቢይ ሆነን ተንብየን እንንገራችሁ፣ እንተንትንላችሁ ባዮች ናቸው ፕላን C ዎች።
“…ሁላቸውም ገሌ ነበሩ። እንየው፣ እንሞክረው፣ እንምከረው፣ እንታገሰው በሚል ተልካሻ ምክንያት የሕዝብ የትግል ስሜት ላይ ውኃ የቸለሱ። ያን በማድረጋቸውም ምንም ዓይነት ፀፀት ዐማራ ሲታረድ፣ ሲፈናቀል፣ ሲገደል፣ ሲጨፈጨፍ ዝም ብለው፣ ከጨፍጫፊው ጋር አንሶላ ሲጋፈፉ፣ ሲሸረሙጡ፣ ሲገለሙቱ ከርመው ዐማራው ለመብቱ መታገል ሲጀምር ሲያሾፉበት ቆይተው የዐማራው ትግል ባሩድ ማጨስ ሲጀምር ደርሰው እንደ ቅቤ በአናት ላይ መጥተው ልጣድ፣ ልዘፍዘፍ ማለት ይወዳሉ። በሰው ድግስ ላይ ዕለቱን መጥተው አስተናጋጅ እንሁን ማለት ትክክል አይደለም።
“…የዐማራው ትግል መመራት ያለበት ለዐማራው ዋጋ በከፈሉ ሰዎች ነው። አንዳቸውም ገሌዎች በዚህ ትግል ላይ አያገባቸውም። ገሌ ትግሉን መደገፍ እንጂ ትግሉን መምራት አይገባውም። ገሌዎች አይታመኑም። ሃይማኖትም ሆነ ሥነ ምግባር የላቸውም። የፖለቲካ ሾተላይ ይሁዳዎች ናቸው። በቀደመ ሥራቸው መመዘን የለባቸውም። በለበሱት ልብስ፣ ባላቸው ኔትወርክ አማካኝነት በሚያገኙት የሚዲያ መድረክ ሁሉ ስለሚበጠረቁ ትግሉን ሊመሩት አይገባም። እነዚህ የትግል ጠላፊ ነጋዴዎች ትግሉን መምራት የለባቸውም።
“…ዐማራ የለም ሲል የነበረ ሁላ ዛሬ ዐማራን ከየት አግኝቶት ነው ልምራው የሚለው። ዐማራ ተጎዳ ብሎ የማያውቅ ጭምብላም ሁላ ዛሬ ደርሶ የሚመራው ዐማራ ከየት አባቱ አመጣ። ምድረ ዲቃላ ሁላ ከመሬት ተነሥቶ ትግሉን መጥለፍ የለበትም። ኢሳት ከነ ሠራተኞቹ፣ ኢ ኤም ኤስ ከነ ግብርአበሮቹ፣ የጎፈንድሚ ቀበኛው ግሎባል አልያንስ ከነ ኮተቶቹ፣ የግንቦት 7 ቫይረስ የነካው በሙሉ፣ የብርሃኑ ነጋ ካድሬ ሲሆኑ ከርመው አሁን በቃን በሚል ስሜት ከኢዜማ የለቀቁ ሆዳሞች በሙሉ፣ ትግሉን መደገፍ ይችላሉ። ትግሉን ለመጥለፍ፣ ለመምራት ግን መሞከር የለባቸውም ባይ ነኝ። በቃ ትግሉ ከዜሮ ተነሥቶ፣ እየተፍጨረጨረ ከዚህ ደርሷል። እነዚህ ጨቡዴዎች በመጨረሻ መጥተው ባለቀ ቤት፣ በተደረደረ ምግብ ፊት ተጥደው እጃቸውን ታጥበው ከርሳቸው እያሰቡ መግተልተል የለባቸውም። ጥፋ ከዚህ ሆዳም ሁላ።
“…የህወሓቱ ኢህአዴግ ፕላን B ነበረው። ያም ብልፅግና ነበር። ብልፅግና የህወሓት ኢህአዴግ ፕላን B ው ነበር። ብልጽግናም ከላይ እንደ አባቱ ህወሓት ኢህአዴግ ሁለት ፕላኖች አሉት። ፕላን B እና ፕላን C። የብልፄ ፕላን C ው እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ሾተላይ ሰው መሳይ በሸንጎ የትግል አጨናጋፊዎች በሙሉ ናቸው። ምድር ሁሉ በዐማራ ሞት ሲያለቅስ እነርሱ ሌላ ዓለም ውስጥ ነበሩ። ከአራጅ ጋር ሲሸረሙጡ፣ ሲገለሙቱ ነበር። ዜጎች እንጂ ዐማራ አልሞተም ባዮችም ነበሩ። አሁን ደርሰው ከላይ ልጣድ ማለት በፍፁም የለባቸውም። እዚያው በጸበላቸው።
“…ዐማራ አሁን በፀረ ዐማራው በእስስቱ መሳይ መኮንን ምላስ መሸወድ የለበትም። አክባሪው ነኝ ነገር ግን በደረጀ ሀብተወልድም ምላስ ዐማራው መጠለፍ የለበትም። በታዬ ቦጋለ ኦህዴድ ሆኖ ወያኔ ብአዴን አድርጎ ያሰለጠነውን በቀጣፊው በአቢይ ጆሮ ጠቢ በብልፄ ሰላዩን ኮተት ዐማራው መጠለፍ የለበትም። ትግሬን በመሳደብ ብቻ ዐቢይን በማይተቸው በፕሮፌሰር ትንግርቱ፣ በኖሞር ጠላፊዋ በፕሮፌሰር ሐረገወይን ወዘተረፈ ትግሉ መጠለፍ የለበትም። አቢይን ንፁሕ አድርጎ ትግሬዋን ሕወሓትን በመስደብ ብቻ በአራድነት ትግል መጥለፍ አይቻልም። ዐማሮች ይሄንን በደንብ መስመር ማስያዝ አለባችሁ።
“…ዐውቃለሁ፣ ይገባኛል ብዙ ሰው የአዝማሪ ወዳጅ ዓይነት ጠባይ ያለው ነው። አዝማሪ የተሰጠውን ግጥም በዜማ ያቀርባል፣ አልያም ራሱ ዜማ ፈጥሮ ይገጥማል። የአዝማሪ ወዳጅ የአዝማሪ ሱሰኛ ደግሞ ከማኅበረሰቡ ያጣውን ሙገሳ፣ ውዳሴ፣ ክብር አዝማሪ ቤት ሄዶ ብሩን በሽልማት መልክ በመበተን በምላሹ አዝማሪው የሚያጎርፍለትን ግጥም እያጣጣመ ራሱን በራሱ እያረካ ይኖራል። አዝማሪ ደግሞ ብር ከሸለምከው ጣጣ የለበትም። ፉንጋውን የአፈር ገንፎ የመሰለውን ሁላ የሌለ የዓለም ቆንጆ ሞናሊዛ ነህ ይለዋል። ኩርማኑን የእኔ መለሎ፣ ጎራዳዋን ሰልካካ፣ ኪንኪ ፀጉሯን የእኔ ዞማ፣ የዓባይ ዳር ጠምበለል ቄጤማ፣ ሽንታሙን፣ ፈሪውን፣ ደካማውን ደግሞ የሌለ አፄ ቴዎድሮስ፣ አፄ ሚንልክ በላይ ዘለቀ፣ የዓለም አንደኛ ነህ ይለዋል። ያኔ የአዝማሪ ወዳጅ ይሞቀዋል።
“…አንዳንድ ዐማሮችም እንደዚያው ናቸው። በዮኒ ማኛ የእብድ የቀውስ ፖለቲካ ሲበሳጩና ደግሞም ሲረኩ የሚውሉ ይበዛሉ። አንዴ ፈትነውት የወደቀ አይደለም 10 ግዜ ፈትነውት የወደቀን ገዳያቸውን እግሩ ስር ተወሽቀው ማለቃቀስ ይወዳሉ። የትግሬና የዐማራ የኦሮሞም ቀሽም ጀማሪ ቦለጢቀኞችም፣ ጎምቱዎቹም እንደዚያው አንድ ዓይነት ናቸው። ዮኒ ማኛ ትናንት ጥንብ እርኩሳቸውን አውጥቶ፣ አራክሶ ሰድቦ ሲያስለቅሳቸው ይውልና ዛሬ ተመልሶ ይቅርታ ካላቸው በቃ ነገ ጥንብ ርኩሳቸውን እስኪያወጣቸው ድረስ በሰላም ይገረዱለታል። የዮኒ ማኛ ስድብ የዐማራን ትግል የሚያነሣ፣ የሚጥልም የሚመስለው ድንገቴ በቀቀናም የትየለሌ ነው። የዐማራ ጀማሪ ቦለጢቀኞችም የዚህ ሰለባ ናቸው። መወደስ፣ መሞገስን እንደ አዝማሪ ግጥም ይወዳሉ። ይሄን ባሕል መተው አለብህ። ኮምጠጥ በል። ሚሪንዳ አትሁን።
“…ይሄ የፕላን C ቡድን እኮ እስክንድር ነጋ ታስሮ በነበረ ጊዜ ፎቶውን ጨረታ እየሸጠ ሲነግድበት፣ ሲሸቅልበት፣ ሲበላ፣ ሲጠጣበት ከሴት ጋር አንሶላ ሲጋፈፍበት የነበረ ከርሳም ቡድን ነው። እስክንድር ዋጋ ከፍሎ ባመጣው ለውጥ ነው እነሱ ከአቢይ ጋር የሸረሞጡት፣ እስክንድርን እብድ ሲሉ የነበሩ ሸርሙጣ ጋለሞቶች ዛሬ ደርሰው ደመራው ሊወድቅ ነው ብለው ባሰቡ ጊዜ ትግሉን ለማጨናገፍ ከፊት መምጣት የለባቸውም። ትግሉን መደገፍ ይችላሉ። መብታቸውም ነው። ትግሉን መጥለፍ ግን የለባቸውም። አለቀ።
“…እነዚህ ብቻ አይደሉም ነገ ደግሞ የብአዴን ፋኖዎችንም እገልጣቸዋለሁ። ከአሁኑ እስክንድር ልኮን ነው፣ ወዘተረፈ የሚሉ ሾተላይ የጎንደር እና የጎጃም የከተማ ፋኖ፣ የብአዴን የቤት ውስጥ ውሻዎችን እገልጣቸዋለሁ። ከእስክንድር ጋር የሚሠሩ ራሱ እስክንድር በእኔው የመረጃ ቲቪ ይፋ ያወጣቸዋል። ጎንደር ባህርዳር ተቀምጦ ጃምቦ ድራፍት እየጠጡ ትግል መጥለፍ አይቻልም። በፎቶ፣ በስም ጭምር ይጋለጣሉ። አሉ ሌሎችም ጀግና ሆነው ይወጡ ዘንድ ልክ እንደ አብን ብአዴን ያሰማራቸው ትግል ጠላፊ ሾተላዮችም ። እነሱንም እንገልጣቸዋለን። አሁን በዐማራ ስም ታስረዋል ተብለው በብልፅግና አመራሮች የሚጎበኙ፣ የወኅኒ ቤት በር በፖሊስ
የወኅኒ ቤት በር በፖሊስ ተዘግቶላቸው ከእነ ዶር ሲሳይ ንጉሡ ጋር የሚመክሩ፣ የፌደራል ፖሊስ ወኅኒ ቤት ለውይይት አልተመቸንም ብለው ወደ ማዕከላዊ የዞሩ። አራዶች። ብአዴንን ለማዳን ተቃዋሚ መስለው የሌለ ዋጋ የሚከፍሉ ሾተላዮችንም አሳምረን ነው የምናውቃቸው። እነርሱንም እንታገላቸዋለን። አከተመ።
“…ወዳጄ ብርሌ ከነቃ አይሆንም ዕቃ። አለቀ። 120 ሚልየን ሕዝብ ባለበት ሃገር በተቃዋሚውም ሆነ በገዢው መደብ የሆኑ ሁልጊዜ ፊቶች ብቻ ከፊት ተጥደው መታየት የለባቸውም። እንደ ስብሃት ነጋ በዳይፐር ሊመሩ የሚፈልጉ ተቃዋሚ ነን ባዮችም ጥጋቸውን ሊይዙ ይገባል። አዲስ ሰው እንዳይመጣ፣ እንዳይገለጥ ከፊት ደንቃራ የሚሆኑ ጉደኞች በቃችሁ ሊባሉ ይገባል። እንደነሱ ሼምለስ መሆን ግድ ነው። ጥፋ ከዚህ በለው።
“…በቀደም ዕለት እኔ መሳይ መኮንን ሙቀቱን ለመለካት እንደ ጆፌ አሞራ አንዴ በስሱ ዞርኩት። መሳይን ስዞረው ግልብጥ ብሎ የመጣው ግሪሳ ግን ይገርማችኋል የብልፅግና እና የኢዜማ ግሪሳ ነበር። መሳይን ስለነካሁት የሻአቢያ ደጋፊ በማያገባው መጥቶ ተንተባተበብኝ። እናም እኔ ትክክል እንደነበርኩ ወዲያው ነው የገባኝ። መሳይ መኮንን የበግ ለምድ የለበሰ ሾተላይ ተኩላ ነው። ይሄ አዝማሪ ወዳጅ ጀማሪ ቦለጢቀኛ እንደ ዮኒ ማኛ የሙገሳ ግጥም፣ ዜማ ባዜመለት ወቅት ሁላ ወከክ እንደሚል አሁንም ጭንብሉን ለብሶ ለሻአቢያና ለግንቦቴ ሊሠራ የመጣው ሰው እግር ስር ሲንደፋደፍ ይታያል። በቀደም ሻለቃ ዳዊትን አስር ጊዜ ” የዘር ከረጢት የዘር ከረጢት ሲል የነበረው ለዚህ ነው። ግም ቦቴያም” ጥፋ ከዚህ የዐማራ ትግል ከዳር የሚደርሰው በሃቅ፣ በእውነት፣ በመሬት ላይ ባሉት ልጆቹ ትግል እንጂ በሾተላዮች አፈ ቅቢ ሆደ ጩቤዎች አይደለም።
“…ይሄ ሾተላይ ቡድን አባቴ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስን ጭምር ጠልፎ የያዘ ነው። አቡነ ኤርሚያስ ሳያውቁ ሳይሆን ሆን ብለው በዚህ ቀሳጢ ቡድን ተጠልፈዋል። አቡነ ኤርሚያስ በግልፅ ከወደዳቸው፣ ካከበራቸው ሕዝብ ጋር ሳያስቡት መላተም ፈልገዋል። እየተቅለሰለሱ፣ ድምጻቸውን ወደ አሳዛኝ፣ ምስኪንነት እየለወጡ መሸወድ አይችሉም። ጥንቃቄ ቢያደርጉ ለእርሳቸው መልካም ነው። ሳያስቡት ብዙ ነጥብ እየጣሉ ነው። ይሄንንም ጀምሬዋለሁ ከዳር ሰላደርሰው አልመለስም። እኔም ያየሁትን አይቻለሁ እንደ ጆፌ አሞራ መዞሬን አላቆምም። በነገራችን ላይ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ተተቹ ብላችሁ የምትንጫጩ ኮተታሞች ለደንታችሁ ነው። ብፁዕነትዎ ግን እግር ባያበዙ፣ ከአንደበትዎም ቢቆጠቡ፣ እዩኝ እዩኝ ባያበዙ መልካም ነው። ከግንቦቴዎችና ከኢዜማዎች ይልቅ የእኔ የታዛዥ ልጅዎ ምክር ይሻልዎታል። አይ ካሉ ግን ምን ገዶኝ። ሃኣ የበሰበሰ ዝናብ ይፈራል እንዴ?
“…እደግመዋለሁ ትግሉ መመራት ያለበት ኢትዮጵያን ለማፍረስ መሠረት በተጣለ ጊዜ ድጅኖና ዶማ ባላቀረቡ ንፁሐን ኃይሎች ነው። ፈንጂና ድማሚት ባላቀረቡ ፅኑአን ኃይሎች ነው። ቫይረሱ ያለባቸውን በሙሉ ሰገራ እንደነካው እንጨት ተጸየፏአቸው። እንደ ጾም ዕቃም ለብቻቸው አድርጓቸው። ልብ በሉ እኔ ትግሉን አይደግፉ አላልኩም። ትግሉ ቅዱስ ስለሆነ የሰይጣንን ድጋፍ አይፈልግም እንጂ ሰይጣንም እንኳ ትግሉን ልደግፍ ቢል ይከልከል ባይ አይደለሁም። እነዚህ ከሃዲ ይሁዳ ሾተላዮችም ትግሉን እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ተጸጽተው መደገፍ ይችላሉ። እንደ እስክንድር ነጋ፣ እንደ ጋሽ አሰግድን እና ጋሽ መሳፍንትን ግን ትግሉን መምራት አይደለም አክት ማድረግ አይችሉም። የዐማራ ትግል አሁን እፉ ነው፣ ካካካ ነው። አከተመ።
“…የዐማራ ትግል ሱናሚ ነው። ቁጣ ነው። መዓት ነው። ታግሶ፣ ታግሶ የገነፈለ ነው። የማንም ልጋጋም አፉን ሲከፍትበት፣ ለሃጩን ሲያዝረበርብበት የተከበረ ሕዝብ አምጦ የወለደው ነው። በበቀል የተሞላ፣ ዘሩን ከጥፋት ለመታደግ የተወለደ መብረቅ የሆነ ትግል ነው። ይሄን ትግል በተለመደው መልክ መጥለፍ አይቻልም። አይሞከርም። ብርሃኑ ነጋንና ሱሳይ አጌናን፣ በለጠ ሞላንና ጋሻው መርሻን ያላስገባሁትም ስለማይጠቅሙ ነው። ኤክስፓየርድ ስላደረጉ ማለት ነው። ክርስቲያን ታደለ፣ ዶር ደሳለኝ ጫኔ በአፍ ከዐማራው ጋር ናቸው። ልባቸውን እንጃ። መድፈር አለባችሁ። ደፍራችሁ ካልተናገራችሁ መድኃኒቱ ይርቃል። ዐውቀዋለሁ፣ ስለ ዐማራ አሁን ጥሩ ይናገራል ወዘተ አይሠራም። ሚናህን ለይ በሉት። አንዳንዱ ደግሞ አለ ከውስጥ ሆኖ ሥራ የሚሠራ። እርሱ ይበረታታል።
“…ሥልጣን ላይ በነበረ ጊዜ ለዐማራ ምንም ያልሠራ ዮሐንስ ቧ ያለው በካልቹ በእርግጫ ተብሎ ሲባረር መጥቶ ጓ ስላለ አልሰማውም። ትናንት ዐማራ እንዳይደራጅ ዐቢይን ለማስደሰት ሲገረድ የከረመው ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ ድራሽ አባትህ ይጥፋ ሲባል ሩጦ ዐማራ፣ ዐማራ፣ ፋኖ ፋኖ ቢል አልሰማውም፣ እንደ መስቀል ወፍ እንደ ዳዊት ጠጠር የብአዴን ብልጽግና ሰዎችን ለመምታት መሃይሙ አቢይ አሕመድ የሚወረውረው አቶ ፀጋ አራጌን ከተኛበት ከርሞ ድንገት መጥቶ ዐማራ ዐማራ ስላለ እሽኮኮ ብሎ መዞር አግባብ አይመስለኝም። ብአዴን ሆኖ ለሕዝብ ሳይሠራ ከርሞ እንደ ኮንዶም ከተጣለ በኋላ ግማት ይዞ መዞር ዐማራ ማቆም አለበት። አዲስ ኃይል፣ አዲስ ጉልበት፣ አዲስ ዐማራዊ አመራር ወደፊት መምጣት አለበት። የትግሬ ወንድሙንና የኦሮሞ፣ የዐፋር፣ የሱማሌ፣ የጉራጌ፣ ወላይታ፣ ሲዳማ ከንባታ ወንድሞቹን ሳያስደነገጥ አቅፎ እንደ ንሥር የሚመነጠቅ አዲስ የዐማራ ትውልድ ወደፊት መውጣት አለበት። አሮጌዎቹ ተደበቁ። ሌባ ሁላ…!
“…ይልቅ ዐማራው ተዘጋጅ። ክረምቱ መጥቷል። ደም በፈሰሰበት ደሙን ዝናብ ሳይጠርገው መዋጋት የማትችለው የሱዳን አጋንንት አምላኪዋ ወያኔ፣ ያለ ጦርነት ሕይወት የሌላት ወያኔ፣ ክረምቱን ጠብቃ አሁን መምጣቷ አይቀርም። ይሄ በቴሌቭዥን መከላከያ ተረከበው የሚባለው መሣሪያ ለወያኔ መንግሥትና ሌሎች የሚያስታጥቋት የጦር መሣሪያ ነው። አሁን ውጊያው ከሁለት ግምባር ነው። ከመንግሥታዊው ሸኔ እና ከወያኔ ጋር። ጠላት በጊዜ መለየቱ መልካም ነው። እንዳይወጣ አድርገህ መክተው። ለማንኛውም ተዘጋጅ ነው የምልህ። ደም የለመደው የወያኔ ሰይጣን በወልቃይት፣ በፀገዴ፣ በራያና በዋግኽምራ መንደፋደፉ አይቀርምና ተዘጋጅ፣ በሸዋ፣ እና በወለጋ፣ ጎጃምና ወሎም ኦነግን ከብራኑ ጁላ ሠራዊት ጋር ተጠንቀቁት።
“…ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው።