>

የአማራ ትግልና የሚዲያ አስፈላጊነት (ጌጥዬ ያለው)

የአማራ ትግልና የሚዲያ አስፈላጊነት

ጌጥዬ ያለው

የጠላት ህልም ይህ ነው፦ በቅድሚያ አማራን መሪ አልባ ማድረግ፣ መታገያ ድርጅቶቹን እያደነ ማጥፋት ወይም ባሉበት ወደ ፀረ አማራነት መቀየር፣ ቀጥሎ እንደ ደቡብ ኢትዮጵያ የአማራ መስተዳድርን ግዛተ መሬት ሰነጣጥቆ ከቁጥር አብላጫነት ወደ አናሳነት መቀየር፣ ከዚያም የራሱ ግዛተ መሬት የሌለው የተበተነ ሕዝብ ማድረግ፣ በመጨረሻም ከያለበት እየለቀሙ መግደል!

ለዚህ ትግሬም፣ ሻንቅላም፣ አገው ሸንጎም ከኦሮሞ ጋር ይተባበራሉ። የኦሮሞ የወረራ አገዛዝ መሪ፤ የአብይ አሕመድ የሕይዎት ዘመን እቅድ ይሄን ማሳካት ነው። ፈረንጆች ይህንን ነው ኔክሮ ፖለቲካ የሚሉት፥ በአንድ ሀገር ላይ ከፊሎች እንዲኖሩ ገሚሶችን ማጥፋት።

የ1960ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ “አዞዎቹ” የተባለ ህቡዕ ቡድን ነበራቸው። የኢትዮጵያ በጥባጮች ጥንስስ ይህ ቡድን ነው። አዞው ዛሬ ጥርሶቹን አግጦ አማራን በመንከስ ላይ ነው። ፈፅሞ ሳይውጠን ጥርሱን መስበር ይገባል። አማራ ያለው አማራጭ ጠላቶቹን በመጡበት አግባብ መመለስ ነው! ለዚህ ደግሞ ሚዲያ ያስፈልጋል። እነኝህ ጥቁር ጣልያኖችም ጥርሶቻቸውን ያሰሉት “ታገል” በተባለ ጋዜጣቸው ነበር።

የሚዲያ አስፈላጊነት ሲባል ጉዳዩን ቀለል አድርጎ የሚረዳው ሰው ጥቂት አይመስለኝም። ምክንያቱም ስነ ልቦናችን ሚዲያን ከመዝናኛነት ጋር ያቆራኘ ስለሆነ ነው። በገጠር በብዙ ሰው ቤት ውስጥ ራዲዮ የሚከፈተው ቤቱ ፀጥታ እንዳይሰፍንበት (በእነርሱ አባባል እንዳይቀዘቅዝ) ነው። በተመሳሳይ በከተማ በብዙዎች ቤት ቴሌቪዥን የሚገዛው ለሳሎን ጌጥ ከሶፋ ወንበር ተነጥሎ እንዳይቀር እንጂ ዜና ለማዳመጥ አይደለም።

የትግል መገናኛ ብዙሃን መኖራቸው ይህንን ክፍተት ይሸፍነዋል። የራሳቸው ጉዳይ ከተነሳበት እና እውነት ከተነገረበት አማሮች ሚዲያን እንደመዝናኛ ሳይሆን እንደ ሥራ በቀጠሮ ማየታቸውን ይቀጥላሉ። ስለዚህ አስፈላጊነቱንም ቢያንስ የቴሌቪዥን መስቀያውን ያህል ከፍ አድርጎ ማየት ተገቢ ነው። እኛ ሚዲያን የምንፈልገው ከዘር ፍጅት ለመትረፍ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ለበርካታ እንቅስቃሴዎቻችን ያስፈልገናል። ከፊሎችን በዝርዝር እንመልከታቸው፦

ለነፍስ አድን ጥሪ

ኬቨን ካርተር ይባላል። ደቡብ ፍሪካዊ የፎቶ ጋዜጠኛ ነበር። በአንድ ወቅት በሱዳን ተከስቶ የነበረውን ርሃብ በምስል ከዘገቡ ጋዜጠኞች መካከል ግንባር ቀደሙ ነው። አንዲት ሕፃን ሰውነቷ በርሃብ ደቆ፣ ለመተንፈስ እየቃተተች በሞት እና በሕይዎት መካከል ሆና ያያል፤ በካርተር ካሜራ ተቀርፆ ለዓለም የተሰራጨው ምስል ሕፃኗ የሞተች መስሎት ጆፌ አሞራ ከእነነፍሷ ሊበላት ሲጠጋት፤ ልጅቷም ላለመበላት ስትንሰፈሰፍ ያሳያል። ትዕይንቱ ዓለምን አስገረመ። ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነት ምስል ያቀረበ ጋዜጠኛ አልነበረምና ካርተር ተወደሰ።

ካርተር የርሃቡን አስከፊነት እና የፎቶ ችሎታውን በተመለከተ መግለጫ ሊሰጥ ከበርካታ ጋዜጠኞች ፊት ተሰየመ። ነገሮችን ሁሉ ሲያብራራ ከቆየ በኋላ ያልተጠበቀ ጥያቄ ተነሳ፦

ሀ. ሕፃኗ የት ነች?
ሁ. ከፎቶ በኋላ አሞራው አልበላትም ወይ?
ሂ. ምግብ ሰጠሃት ወይ?

ይህ ለካርተር ብቻ ሳይሆን በዚያ ለተሰበሰው ሁሉ አስደንጋጭ ጥያቄ ነበር። የፎቶ ጋዜጠኛው ሥራውን ከመሥራት በዘለለ የሕፃኗን ነፍስ ለማትረፍ ያደረገው አንዳች ሙከራ አልነበረም። ሙያውን በአግባቡ ቢሠራም ሰብዓዊነቱን ረስቷል። በዚህም ራሱን በሞት ፍርድ ቀጣ። ከጋዜጣዊ መግለጫው በኋላ ሕፃኗ ‘ሄዳበታለች’ ወዳለው፤ ወደ ማይቀርበት ሄደ። ይህ ታሪክ ዛሬ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ስርዓተ ትምህርት ውስጥ ተካቶ በየዩኒቨርሲቲው ጋዜጠኞች እየተማሩበት ነው።

የአማራ ሕዝብ በርሃብ ባይደክምም ዙሪያውን ከከበቡት ጅምላ ጨፍጫፊዎች ለማምለጥ ልክ እንደ ሕፃኗ ልጅ እየተንሰፈሰፈ ይገኛል። ወለጋ ላይ በቤተሰቦቿና ጎረቤቶቿ አስክሬን መሃል ቁማ ‘የዛሬን ማረኝ በድጋሜ አማራ አልሆንም’ ያለቺው ሕፃን ለዚህ አስረጂ ነች። በርግጥ አማራ ተንሰፍሳፊ ብቻ ሳይሆን ጠላቱን ደፊም ነው።

ያም ሆነ ይህ፥ የዘር ፍጅት እየተፈፀመበት ያለን ሕዝብ ከጭፍጨፋ እንዲድን በሚዲያ መቀስቀስ ከጋዜጠኝነትም በላይ ሰብዓዊነት ነው። ይህ አማራ ብቻ ሳይሆን ሰው የሆነ ሁሉ ሊያደርገው የሚገባ ነው። ጉዳዩ የነፍስ አድን ጥሪ ነው። ለራሱ ለአማራ ደግሞ ግዴታው ነው።

ለፀረ ወረራ

በአማራ ሕዝብ ላይ የታወጀው ጅምላ ጭፍጨፋ ትልሙ (Strategy) አንድ ቢሆንም የተለያዩ የማስፈፀሚያ ስልቶች (Tactics) አሉት። ከእነዚህ መካከል ሚዲያን በመጠቀም የሚደረጉ የባህል፣ የሃይማኖት፣ የታሪክ፣ የቋንቋ፣ የትውፊት ወዘተ ወረራዎች ይጠቀሳሉ። አማራ የራሱ ሚዲያ ካለው ይህ መሰል ወረራ እንዳይደረግበት መመከት ይችላል። እንቅስቃሴያቸውን ተከታትሎ ያከሽፋል።

የዋልተኝነት ሚዛንን ለማስጠበቅ

እንኳንስ እንደ እኛ እና ጠላቶቻችን የጋራ ማንነት ሳይኖረን፤ የጋራ ብሄራዊ ማንነት ባላቸው ሀገራትም የመገናኛ ብዙሃን ዋልተኝነት (Media polarization) ያለ ነው። የጋራ ብሄራዊ እሴታቸውን በሚያከብሩ ሀገራት ዋልተኝነቱ እንደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መለማመጃ ወይም ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል። በእኛ ሀገር ግን ከዚህ የተለየ ነው። የትግሬ ዋልታ ባሉት ሚዲያዎች ሁሉ አማራን ሲደበድብ ውሎ ያድራል። በኦሮሞ ዋልታም በተመሳሳይ “ነፍጠኛን ስበረው” ሲል ይከርማል። ይህን ለማለት ነገ ሌላውም ተወልዶ ይደርሳል። አማራም ይህንን ተገዳዳሪ ብቻ ሳይሆን ደምሳሽ ሚዲያ መገንባት አለበት።

ለሁለንተናዊ መሰባሰቢያነት

ሚዲያ በባህሪው መረጃ በመሰብሰብና መልሶ በማሰራጨት የማዕከላዊነት ሚና አለው። ሕዝብ ሃሳቡን የሚለዋወጥበት ዋነኛ የመገናኛ ማዕከል ነው። ስለዚህ ስነ ልቦናዊ አንድነትን ማጠናከሪያ፣ የትግል አጀንዳ ግልፀኝነትን መፍጠሪያ ማዕከል ልናደርገው ይገባል። ሚዲያ ሁለንተናዊ መሰብሰቢያችን ሲሆን ትርክትን በአግባቡ መቆጣጠርና መምራት ይቻላል።

ተሞክሮዎች

በዓለም ዙሪያ የተለያዩ የትግል እንቅስቃሴዎች ውጤታማ የሆኑት ትግላቸው በሚዲያ የታገዘ ስለነበረ ነው። ሚዲያን ሁለንተናዊ መሰባሰቢያቸው ስላደረጉ ነው። ይህ ባይሆን ኖሮ እርስ በእርስ እንኳን ለመነጋገር አስቸጋሪ ነበር። እኛም ከታሪካችን ወይም ከጎረቤቶቻችን መማር ይጠበቅብናል። ጥቂቶችን እንመልከት፦

ሀ. የጣልያን ወረራ

ከ1928-1933 ዓ.ም. ፋሽስት ጣልያን ኢትዮጵያን ሲወር አርበኞች በሀገር ቤት፤ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ደግሞ በውጭ ሀገር ሆነው በቅንጅት ታግለዋል። ከአምስት ዓመታት በኋላ ድል ለማድረግ ያበቃቸው ትግላቸው በሚዲያ የተደገፈ ስለነበረም ጭምር ነው። በወቅቱ አርበኞችና ጃንሆይ በጥምረት “New times and Ethiopian news” የተባለ ጋዜጣ እያሳተሙ ለተለያዩ ተቋማት በተለይም ለእንግሊዝ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ያሰራጩ ነበር። ከጣልያን ጋር የነበራቸው ቁርሾ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ ቢሆንም የእንግሊዝ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆም የጋዜጣው ሚና ከፍተኛ ነበር። የሽምቅ ውጊያው በሚዲያ ባይደገፍ ኖሮ ኮሎኔል ሳንፎርድ እና ጀኔራል ዊንጌት ጀግኖች አርበኞችን ለማገዝ ኢትዮጵያ ባልገቡ ነበር። በመንግሥታቱ ድርጅት ለተደረገው የዲፕሎማሲ ተጋድሎም የጋዜጣው አስተዋፅኦ በቀላሉ የይበየን አይደለም። ይህ ጋዜጣ ከድል በኋላ “አዲስ ዘመን” ተብሎ በሀገር ቤት በአማርኛ መታተም ጀመረ። ዛሬም የሀገሪቱ ብሄራዊ ጋዜጣ እንደ ሆነ ቀጥሏል። የአማራ ትግል ከጨፍጫፊዎች ልሳንነት ነፃ ያወጣዋል! ወደ ባለቤቶቹም ይመለሳል!

ለ. የአፍሪካ የነፃነት ንቅናቄ

በጃማይካዊው ማርከስ ጋርቬይ መሪነት “ወደ አፍሪካ ተመለሱ” (back to Africa) በሚል መፈክር ይደረግ የነበረው የነፃነት ንቅናቄ በዓለም አፅናፋት ሁሉ የነበሩ ጥቁሮችን ወደ አፍሪካ መመለስ የቻለው በጋዜጣ ቅስቀሳ ጭምር ነው። “the Negro world” የተባለው ጋዜጣ ጥቁሮችን ለትግል አነሳስቷል። ፖለቲካዊ ንቃታቸውን አሳድጎታል። በተመሳሳይ ጥቁር አሜሪካዊው ዊልያም ቦኢዝ ያሳትማት የነበረቺው “Criss” መፅሔት የነጭና የጥቁርን የፖለቲካ ሚዛን በመቀየር ታላቅ አስተዋፅኦ አድርጋለች። “የዓለም ችግር ቀለሜው መስመር ነው” (the problem of the world is the problem of the color line) እያለች ሰዎች በቆዳ ቀለማቸው ብቻ ተለይተው ነጭ ከፍ ጥቁር ዝቅ መደረጋቸውን ትኮንን ነበር። በርካታ ጥቁሮችንም ለትግል አነሳስታለች።

ሌሎች በርካታ አስተዋፅኦዎችም ተጨምረውበት የአፍሪካ ነፃነት እውን መሆን ችሏል።

ሐ. የጽዮናዊነት ንቅናቄ

እስራኤላውያን የጠፋች ሀገራቸውን መልሰው ለማቋቋም፣ ከ2000 ዓመታት በፊት የተወሰደ መሬታቸውን ለማስመለስ ሲታገሉ ከበራሪ ወረቀት ጀምሮ ዘመኑ የፈቀደላቸውን የሚዲያ አማራጭ ሁሉ ተጠቅመዋል። የዘመናዊ ጽዮናዊነት አባት በመባል የሚታወቀው ኦስትሪያዊው ይሁዲ ራሱ ጋዜጠኛ መሆኑንም ልብ ይሏል። ንቅናቄው በአለም የተበተኑ ይሁዲዎችን የሰበሰበው በሚዲያ እንደሆነ አያጠራጥርም። “ሰው የሌለበትን አገር፤ አገር ለሌላቸው ሰዎች” (Land with out people, for people with out land) በሚል መፈክር የጀመሩት የአገር ምስረታ ትግልም ስኬታማ ሆኖ የእስራኤልን ትንሳኤ አብስሯል።

በአጠቃላይ የአማራ ሕዝብ ትግል ሁሉን አቀፍ ነው። ይህንን አቀናጅቶ ለማስተናበር ሚዲያ በእጅጉ አስፈላጊ ነው። ያለ ሚዲያ መታገል ያለ ጠመንጃ ጦር ሜዳ እንደ መዝመት ነው።

Filed in: Amharic