>

የአማራ ገበሬዎች አመፅ (ጌጥዬ ያለው)

የአማራ ገበሬዎች አመፅ

ጌጥዬ ያለው

ሰው ሰራሽ ርሃብ፥ ደም አልባው የአማራ ፍጅት 

“የሰውን ነፍስ እንደ መውሰድ ነውና ወፍጮ ወይም መጅ ስለመያዣ ማንም አይውሰድ” ይላል መፅሐፍ ቅዱስ በኦሪት ዘ ዳግም ምዕራፍ 24 ካሰፈራቸው ሕግጋት መካከል። ሰዎች ንብረት ተውሰው መመለስ ባይችሉ፣ ገንዘብ ተበድረው በጊዜው ባይመልሱ ወይም ሌላ ማናቸውም ዕዳ ቢኖርባቸው ቀን ወጥቶ እስኪከፍሉ በአበዳሪው ወይም በሦስተኛ ወገን እጅ የሚቆይ ንብረት እንደ ኤግዚቢት አስይዞ መቆየት የተለመደ ነው። በተለይም እንደ ዛሬው ዘመናዊ የገንዘብ ዝውውር ተቋማት ሳይስፋፉ በአራጣ አበዳሪዎችና ተበዳረዎች መካከል መያዦ የየዕለት ጉዳይ ነበር። ታዲያ ታላቁ መፅሐፍ በእንደዚህ አይነቱ ማህበራዊ ግንኙነት ውስጥ የሰው ሕይዎት እንዳይጠፋ የተጨነቀ መሆኑን ከላይ የሰፈረው ሕግ በግልፅ ያሳያል። ወፍጮ ሰዎች የዕለት ጉርሳቸውን ከክተው የሚበሉበት ስለሆነ ከእነ መጁ መያዦ እንዳይሆን ከልክሏል። ይህም ሰው በርሃብ እንዳይሞት ከሚል እሳቤ ነው።
ይህ አይነቱ የነፍስ አድን እሳቤ በዘመነኛው ዓለማዊ የሕግ ድንጋጌና አተረጓጎም ውስጥም ከፍተኛውን ድርሻ ይዞ ይገኛል። ለዚህም ነው ወህኒ ቤቶች ምግብ አብስለው እስረኞችን የሚቀልቡት።
አረመኔነትን ከዘር ሃረጉ የወረሰው የኦሮሞ የወረራ አገዛዝ ግን ከዚህ በተቃራኒው መንፈሳዊ፣ ዓለማዊ እና ሞራላዊ ሕጎችን ሁሉ በመጣስ በአማራ ብሄር ላይ የጭካኔውን ጥግ እያሳየ ይገኛል።
. . . በአፋር በረሃ በግዞት የታሰሩ ፋኖዎች ምግብ እንዳያገኙ ተከልክለው በርሃብ ሞቱ። በሕይዎት ያሉትም በቀን ድንች የምታክል አነስተኛ ዳቦ እየተሰጠቻቸው ጠኔ ይዟቸዋል። በቀን ውስጥ ፈፅሞ ምግብ የማያገኙም አሉ. . .
የሚል ዜና ተደጋግሞ ብንሰማም ነገሩ የደነቀው የለም። ምክንያቱም ስርዓቱ አጋንታዊ ባህርያቱን ካሳየን ውሎ አድሯል። ለይስሙላ የተቋቋሙ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ቢኖሩም አንድም የአጋንቱ ከዳሚ ናቸው፤ ሁለትም ወገቡን እንደተመታ እባብ ልፍስፍሶች ናቸው። ለይስሙላ የተቋቋመ እንባ ጠባቂ ተቋም ቢኖርም፤ የሌላውን እንባ ሊያብስ ቀርቶ ለራሱም አልቃሻ ነው። የሕግና ፍትሕ ተቋማትም የትንንሽ አጋንቶች መስፈሪያ ከሆኑ ቆይተዋል። ልብ ወለድ ተደርሶ የሚተወንባቸው ቴአትር ቤቶች ናቸው ማለት ይቻላል። ጉዱ ብዙ ነው፤ ወደ ርዕሰ ጉዳዩ እንመለስ፦

 ወላዲ አመፅ 

በአማራ ብሄር ላይ የታወጀው የዘር ማጥፋት እንቅስቃሴ ትልም (Strategy) እና ስልቶች (Tactics) ተዘጋጅተውለት እየተፈፀመ ይገኛል። ከማስፈፀሚያ ስልቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
ሀ. መንግሥት ደገፍ ሽብርተኛ ቡድን ፈጥሮ በጦር ሃይል ማስጨፍጨፍ
ለ. ‘ሕግ ማስከበር’ በሚል የሽፋን ዘመቻ በራሱ በአገዛዙ ሰራዊት መጨፍጨፍ
ሐ. የአማራን ታሪክና ባህል በሀሰተኛ ትርክት መደምሰስ (በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል መሰረዙን ያስታውሷል)
መ. የተፈጥሮ መስህቦቹን ማጥፋት (በጣና ሐይቅ ላይ የተሰራጨውን የእንቦጭ አረም ልብ ይሏል)
ሠ. ቅርሶቹን፣ ገዳማቱንና አብያተ ክርስቲያናቱም በፀሀይም ሆነ በጨረቃ ማውደም
ረ. አማርኛን ማጥፋትና በፍጥነት በኦሮምኛ መተካት (ሰሞኑን በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ትምህርት ክፍል መሰረዙን ልብ ይሏል)
ሰ. አማራ ሰብሰቢ ድርጅት እንዳይኖረው ተቋማቱንና መሪዎቹን ማጥፋት
ሸ. በጋራ እንዳይቆም በውስጡ እየገቡ መበታተን
ቀ. ማህፀን ማድረቅ (ወደ አረብ የሚላኩ የቤት ሠረተኞችን ጉዳይ ያስታውሷል። በየከተማው የሚገኙት የሜሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ቢሮዎች ከብልፅግና ፅህፈት ቤቶች ያላነሰ የአማራ መፍጃዎች ናቸው)
በ. ማሕበራዊ ረፍት መንሳት
ተ. ሰው ሰራሽ ርሃብ . . .
ለጊዜው ሌሎችን አቆይተን በመጨረሻ የተጠቀሰውን የጅምላ ጭፍጨፋ ማስፈፀሚያ ስልት እናፍታታው፦ ስርዓቱ ሰው ሰራሽ ርሃብን በማንበር አማራን በጅምላ በርሃብ ለመፍጀትና ዘሩን ለማጥፋት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። የአማራ ገበሬዎች በብሄራቸው ብቻ ተለይተው ምርጥ ዘርና የአፈር ማዳበሪያ ማለትም ዳፕ እና ዩሪያ ገዝተው እንዳይዘሩ ተከልክለዋል። የአመፃው መነሻም ይኸው ነው። ወትሮውንም ሙሉ በሙሉ ከግል ነጋዴዎች ንክኪ ርቆ በስርዓቱ ቸርቻሪነት በውድ ዋጋም ቢሆን ለገበሬው ይደርስ የነበረው ዘርና ማዳበሪያ ከግንቦት ጀምሮ ቢጠበቅም ይኸው እስከ ሀምሌ ሊገኝ አልቻለም።
በአንፃሩ የኦሮሞ ገበሬዎች ‘እንኳንስ መሬቱን ከቻላችሁ ሰማዩንም፤ እንኳንስ የብሱን ባሕሩንም እረሱ እንጂ እጃችን አይታጠፍም’ ተብለዋል። በቅርቡ ከሩሲያ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጭ የመጣውን ማዳበሪያም በብቸኝነት እንዲወስዱ ተደርገዋል። በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሞ ገበሬዎችማ ደግዳጋ በሬውን የሚያንኳትት፣ ቀንበር ያልለመደ ወይፈኑን የሚኮለኩል አማራ ጎረቤታቸውን እንቁልልጭ እያሉ በትራክተር ማረስ ከጀመሩ ሦስት ዓመታት ተቆጠሩ። እድሜያቸውን በእረኝነት ሲገፉ የኖሩ የኦሮሞ ከብት አርቢዎች ከኦጋዴን ተነስተው አዲስ አበባ ሲሰፍሩም ከትራክተር በተጨማሪ ዘመናዊ የቪላ መኖሪያ መንደር ጭምር ተገንብቶ ነበር የጠበቃቸው። እንዲህ አይነቱ የገበሬዎች የመንደር ግንባታ በአውሮፓና አሜሪካ ካልሆነ በቀር በአፍሪካ ገበሬዎች ታሪክ ታይቶ ለመታወቁ እጠራጠራለሁ። ቤቶቹ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ሳይሆኑ አጫጭር ቪላዎች መሆናቸውን፣ በመስታዎትና ብልጭልጭ መብራቶች አለማሸብረቃቸውን ብሎም መውጫና መግቢያቸው በከብቶች እግር መቆሸሻቸውን አይተን ‘በከበርቴው ዓለም ከሚገኙ መንደሮች አይመሳሰሉም’ ብንል እንኳን፤ በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአሜሪካ፤ ቦሰተን ከነበረ የብዙ መርከበኛ ነጮችና የጥቁር አሜሪካውያን መንደር ጋር ማዛመዳችን አይቀርም።
በታከለ ኡማ ክንትብና ጊዜ  በቂሊንጦ የሚኖሩ ኦሮሞዎች ጥያቄ ‘ሞፈርና ቀንበር ተሸክመን የኮንዶሚኒየም ደረጃ መውጣትና መውረድ ተቸግረናል። በተለይ በሬዎቻችን አልቻሉትም’ የሚል ነበር። በአዳነች አቤቤ ክንትብና በሬ መንዳት፣ ሞፈርና ቀንበር መሸከም አላስፈለጋቸውም። ትራክተራቸውን አሽከርክረው ያርሳሉ፤ ከጋራ መኖሪያ ቤቱ ግርጌም ከከተማዋ ኗሪዎች ቪትዝና ያሪስ ጋር ተጋፍተው ያቆማሉ። የበረት ጥያቄያቸው የፓርኪንግ ምላሽ አገኘ። የዛሬ ጥያቄያቸው “አንዱ ሲበላሽ በሌላው እንድናርስ ትራክተር ይጨመርልን” የሚል ነው። ስርዓቱ የእነርሱ ነውና ቢችል የትራክተር ፋብሪካ ያቆምላቸዋል።
ኦሮሞን ወሃ በሬ! ብሎ አርሶ መብላትን ያስተማረው ጠቢቡ አማራ ግን በሬውን ከላሞች ጋር ቀላቅሎ መስክ ያውላል። ራሱም ጅራፉን አጥፎ በየከተማው በመዞር ግብር የተቀበለውን መንግሥት ተብየ ዘርና ማዳበሪያ እንዲያቀርብለት በመጠየቅ ላይ ነው። ከጎጃም እና ከጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች ገበሬዎች ባሕር ዳር ድረስ ሄደው የአማራ መስተዳድርን ግብርና ቢሮ ጠይቀዋል። ጥያቄው ከመንግሥት ተብየው አልፎ ለሰፊው ሕዝብም ቀርቧል። ሰሞነኛው የገበሬዎች አመፅ ትርጓሜ ይህ ነው። የሰኔ ዘራቸው ጉዳይ ግን መፍትሔ አላገኘም።
ከቀበሌና ወረዳቸው መጥተው የማያውቁ ገበሬዎች የሰኔ ጉዳይ ሆነባቸውና ባሕር ዳር ድረስ ተንከራተቱ። በሸዋና በወሎ ተመሳሳይ ጥያቄዎች እየቀረቡ ቢሆንም ጆሮ ዳባ ልበስ እንደተባሉ ናቸው። ጅራፋቸው እንደ አቶሚክ ቦምብ ያስፈራው ስርዓቱ የመርሀቤቴ ገበሬዎችን “ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱን በሃይል ልትንዱ ነው” ሲል በፍርድ ቤት ከሷቸዋል። ከአማራ ለኦሮሞ ‘ክልል’ ከተሰጡ በኋላ እንደገና ለፌዴራል ፖሊስ ተላልፈው በመሰጠት በግፍ እስር ላይ ይገኛሉ። በአንደበታቸው ለችሎቱ ያቅርቡት ወይም በአርምሞ ይለፉት ባይታወቅም በክርክሩ ጊዜ የገበሬዎቹ ቀዳሚ ጥያቄ ‘ሕገ መንግሥት ምንድን ነው? ሕገ መንግሥታዊ ስርዓትስ?’ የሚል እንደሚሆን አልጠራጠርም። በታሪክ የገበሬዎች አመፅ ለማዕከላዊ መንግሥት ስጋት እስከ መሆን የደረሰ ቢሆንም፤ ዶሴ ከፍቶ፣ ነገር አወሳስቦ ገበሬን በሽብር መክሰስ እምብዛም አልተስተዋለም።

 የገበሬዎች አመፅ በታሪክ 

በኢትዮጵያ ታሪክ የገበሬዎች አመፅ የታወቀና ለውጥም ያመጣ ነው። የ1942ቱ የጎጃም ገበሬዎች አመፅ ሰፊ ድርሻ አለው። ይህንን ተከትለው የተስፋፉት የራያ እና የባሌ ገበሬዎች አመፆችም ተጠቃሽ ናቸው። የእነዚህ አመፆች ቀጥተኛ ምክንያት የመሬት ግብር ጭማሪ ሲሆን ስርዎ ምክንቱ ደግሞ አጠቃላዩ የአካባቢ ገዥዎች ጭቆና ነበር። መንግሥቱም የገበሬዎችን ጥያቄ በመስማት ለቃዳ መሬት አንድ ብር ከሃምሳ ሳንቲም ይከፈል የነበረው ግብር ላይ ቅናሽ አድርጓል፤  ጨቋኝ የተባሉ የአካባቢ ሹመኞችን ከሥልጣን አንስቷል። የአመፁ አስተባባሪዎችንም ከማሰርና ከማሳደድ ይልቅ እንደየ ችሎታቸው የሥልጣን ተካፋይ አድርጓል። ገበሬዎቹም የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤን መንግሥት የመቀየር አላማ ስላልነበራቸው አመፁን አቁመው ወደ ርሻቸው ተመልሰዋል። ገበሬዎችን በሽብር መክሰስ ሊደረግ ቀርቶ ሊታሰብም በእጅጉ ሩቅ ነበር።
የ1968ቱ የጎጃም ገበሬዎች አመፅ የደርግን ሥርዓት ከስር መሰረቱ በመቃወም የተደረገ ነበር። አመፃው ሁለት ምክንያቶች ነበሩት፦ አንደኛው የወታደራዊው መንግሥት የርስትና ጉልት ስርዓትን ማፍረስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ፀረ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶነቱ ነበር። ግልፍተኛው ደርግ የቻለውን ያህል ገበሬዎቹን ደበደበ፤ ለጊዜው አሰረም። ሆኖም ነገረ ፈጅ አቁሞ የሽብር ድርሰት ሲያውጠነጥን እምብዛም አልታየም። ደርግ ጥያቄውን መመለስ ባይችል አመፁን በሃይል አፈነው እንጂ ገበሬዎችን የእድሜ ልክ ወይም የሞት ፍርደኛ ለማድረግ የሽብር መዝገብ አልገለጠም።
አመፆች ዘወትር ቢኖኑም ገበሬን በተወሳሰበ የሽብር ዶሴ አንደኛ ተከሳሽ ማድረግ የተለመደ አይደለም። በአባሪነት ከዋናው ተከሳሽ ቀጥለው የሚከሰሱ ይኖራሉ። ለዚህም ከፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ጋር አጣምሮ ወያኔ የከሰሳቸው የጎጃም ገበሬዎች ጉዳይ ምሳሌ ነው። ጅራፋቸው እንደ ከባድ መሳሪያ ተቆጥሮ፤ ‘ሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊ ስዓትን በሃይል በመናድ’ ሲከሰሱ የመርሀቤቴ ገበሬዎች የመጀመሪያዎቹ ሳይሆኑ አይቀሩም።
የመሬ ገበሬዎች በጠቅላላው ለአማራ ገበሬ የታቀደው የማስጨነቅ፣ ማህበራዊ ረፍት የመንሳትና ጥሪቱን የማሟጠጥ ጅምር ማሳያዎች ናቸው። ገበሬው ጭብጡ ባልገባው ክስ ግራ እንዲጋባና እንዲጨናነቅ፣ በዋስትና ገንዘብ ሰበብ ጎታውን እየጠረገ ለርሃብ እንዲጋለጥ፣ የዘርና የመኸር ወቅቶችን እስር ቤት በማሳለፍ ከሥራ ውጭ እንዲሆን እና ሕይዎቱ እንዲቃወስ ይፈለጋል። ይህም የዘር ፍጅቱ ስልት ነው።
ለመሆኑ በአማራ ላይ የታወጀው ደም አልባ የዘር ፍጅት ስልት  እንቅስቃሴ የተጀመረው መቼ ነው?

 ቀዳሚ ጉዳዮች 

አገዛዙ በ2012 ዓ.ም. የእርሻ ዘመንም ዘርና ማዳበሪያ በመከልከል ወይም በበቂ ደረጃ እንዳይዳረስ በማድረግና ሆነ ብሎ በማዘግየት የአማራ ገበሬ በሙሉ አቅም እንዳያመርት ሲያደርግ ከርሟል። በዚህም ሳቢያ በጎጃም የቢቡኝ ወረዳ ገበሬዎች ከአዲስ አበባ ~ ደብረ ማርቆስ ~ ባሕር ዳር ~ ጎንደር ብሎም ሁመራ የሚያዘልቀውን ሀገር አቋራጭ አስፋልት መንገድ ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ.ም. ለሰዓታት በመዝጋት ማመፃቸው ይታወሳል።
የዘርና ማዳበሪያ ክልከላው ሰሞኑን በአመፅ ደረጃ ተቀጣጥሎ ቢወጣም ካለፈው ግንቦት መባቻ ጀምሮ ውዝግብነቱን አላቋረጠም። ከዚያም ባለፈ በአቸፈር ዝህብስት፣ ቻባ ጊዮርጊስና አሹዳ አካባቢዎች በገበሬዎች እና በአካባቢው የአገዛዙ ካድሬዎች መካከል ውጊያ ተደርጓል። ገበሬዎቹ ጅራፍ አጥፈው ከመለማመጥ በዘለለ ጠመንጃቸውን አቀባብለው ተፋልመውታል። ጀግና ብርሌ ነው ወድቆ ይሰበራል እንዲሉ እንደ ካድሬዎች ሁሉ የጀግኖች ሕይዎትም ጠፍቷል። በዚያው በአቸፈር ከተለያዩ ቀበሌዎች የተውጣጡ ገበሬዎች በሊበን ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውም ሀቅ ነው።
በዚህ ዓመት በገበሬዎች ላይ እየተፈፀመ ያለው ደም አልባ ፍጅት ዘርና ማዳበሪያ በመከልከል ብቻ አልቆመም። ዘር እስከ መብላት የደረሰ ነው። ባለፈው ሰኔ 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በደንበጫ ከተማ ራሱን የሀገር መከላከያ ሰራዊት እያለ የሚጠራው የኦሮሙማ ወራሪ ሰራዊት የገበሬዎችን እህል ከጎተራ አውጥቶ ለመውሰድ ሞክሯል። እህሉ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማሕበር የከዘነው ሲሆን  ጎተራ ቀዶ ለመዝረፍ የተደረገው ሙራ በሕዝብ እምቢተኝነት ከሽፏል። ውጥረቱም ከደንበጫ አልፎ ወደ አጎራባች ከተሞች ማለትም ጅጋ እና ፍኖተ ሰላም በመዛመት ለቀናት የዘለቀ ሕዝባዊ ውጊያ ተደርጓል። ከተቃውሞ ባሻገር ወራሪው ሰራዊት እና ነፍጠኛው በጠመንጃ ተጫውተዋል። ከታጠቁት ፊት መቆም የተሳነው የኦሮሙማ ሰራዊት ከ15 በላይ ንፁሃን አማሮችን ገድሎ ሌሎችን ማቁሰሉ ተዘግቧል።
የስርዓቱ የአረመኔነት ጥግ ይህ ነው፥ ዘርና ማዳበሪያ የተከለከለው ገበሬ ሊጨፈጭጨፈው የመጣን ሰራዊት የሰኔ ዘሩን ቆልቶ እንዲቀልብም ተፈርዶበታል። ለጊዜው አልተሳካም! የጥይት ቆሎ ቅሞ፤ ካምፑንም ነቅሎ ሸሽቷል። ሆኖም ጠቅልሎ ከአማራ መስተዳድር አልወጣም።
የዘመቻው አላማ አንድ ነው። በመስተዳድሩ ውስጥ የሚኖረውን አማራ እንደ ወለጋ እና መተከል አማራ በቀጥታ ማረድ ስላልተቻለ እንዳያመርትና በርሃብ ተቆራምዶ እንዲሞት ማድረግ! በአማራው ላይ ኦሮሞ ሰራሽ ርሃብ መልቀቅ! በቃ ሰው ሰራሽ ርሃብን ደም አልባ የዘር ፍጅት መሳሪያቸው አድርገው መርጠውታል። ርሃቡ ገበሬውን ብቻ ሳይሆን መላው አማራን ይመለከታል። ከወዲሁ መክሸፍ አለበት። በባሕር ዳር ጎዳናዎች የአመፅ ድምፃቸውን ያሰሙ ገበሬዎችም ለዚህ ጥሪ አቅርበዋል። መላው የአማራ ሕዝብ አረመኔውን ስርዓት ከስሩ መንግሎ ለመጣል መነሳት አለበት። በተጓዳኝ የሚከተሉት አስቸኳይ የመፍትሔ ርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል፦
1. የአማራ ግብርና ባለሙያዎች ማህበር መቋቋም (ከሌለ) እና ተፈጥሯዊ የአፈር ማዳበሪያ ስልቶችን መቀየስ አለበት። ባድማቸው ድረስ እየሄደ ገበሬዎች ሊያደርጓቸው ስለሚገቡ አማራጭ የስነ ዘር ስልቶች ማማከር አለበት። ይህንን ለማድረግ ሰፊ ጊዜ ወስዶ ሰፊ አደረጃጀት ያለው ማህበር ማቋቋም አይጠበቅም። ሩጫው ከሰኔ ጋር ነው። ስለዚህ ጥቂት ባለሙያዎች ተሰባስበውም  ቢሆን የተቻላቸውን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
2. የአማራ ነጋዴዎች በተለይም ከፍተኛ ባለንብረቶች ማዳበሪያውን በግል ንግድ ለማቅረብ የማያቋርጥ ሙከራ ማድረግ አለባቸው። እያቀረቡ ያሉ ካሉም ዋጋውን ተመጣጣኝ ማድረግን እንዳይዘነጉ። በዚህ ሂደት ውስጥ የሚያከብሩት የንግድ ሕግ መኖር የለበትም። ጉዳዩ ሕግ ሳይሆን የነፍስ አድን ዘመቻ ነው።
3. በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ የሚታገሉ የአማራ ትግል መሪዎች ማዳበሪያው ከውጭ ሀገራት ተገዝቶ በጎረቤት ሀገራት በኩል የሚገባበትን ዲፕሎማሲያዊ መንገድ በአስቸኳይ ለመቀየስ መንቀሳቀስ አለባቸው። ሽያጩ ከራሳቸው ከጎረቤት ሀገራት ከተገኘም እሰየው!
4. ሰሞኑን የተጀመረው የገበሬዎች አመፅ ጊዜያዊ አስተባባሪዎች እንጂ መሪዎች የሌሉት በመሆኑ ቋሚ መሪዎች እንዲኖሩትና በትልምና የማስፈፀሚያ ስልቶች እንዲመራ ማዋቀር ግዴታ ነው። በተቻለ መጠን ቄስ ገበሬዎች የአደረጃጀቱ መሪዎች እንዲሆኑ ማድረግ ገበሬውን በአንድ መዋቅር ለመምራት ጠቃሚ ነው። ጅራፍ በማጠፍ በባሕር ዳር የተጀመረው አመፅ፤ በዋና ዋና የከተማዋ ጎዳናዎች ለረጅም ሰዓታት ጅራፍ በመግረፍ ተቀጣጥሎ መቀጠል አለበት። በከተማ የታጠረው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቁምጣ ለብሶ ገጠር እንዲወጣ መጎተት ይገባል።
በአጠቃላይ የአማራ ገበሬዎች አመፅ ከዘርና ማዳበሪያ አቅርቦት በተጨማሪ የስርዓት ለውጥ ጥያቄን ይዞ እንዲቀጥል ማድረግ ያስፈልጋል። የአቸፈር ገበሬዎችን ተሞክሮ በመውሰድ በአፈ ሙዝ መፋለም ይገባል። አማራ ነፍጠኛ የሚባለው በሰርግ፣ ለቅሶና መሰል መርሃ ግብሮች ላይ ወደ ሰማይ በመተኮስ ብቻ መሆን የለበትም። ‘የጅራፍ ቁማርተኛ’ እያለ ከሚዘባበትበት ጀምሮ በየቀበሌው የሚያንሾካሹከውን የስርዓቱን አሽከር ሁሉ ሊደፋው የተገባ ነው። በርሃብ ከመሞት ተዋግቶ መሞት ሺህ ጊዜ ይመረጣል። የእንግሊዙ ባለ ቅኔ ሸክስፔር እንደሚለውም ጀግና አንድ ጊዜ ይሞታል፤ ፈሪ ከመሞቱ በፊት ደጋግሞ ይሞታል። እግዚአብሔር ከድርብ ሞት ይሰውረን!
Filed in: Amharic