>

አባ ሠረቀ ብርሃን በሽተኛ እንጅ በሽታ አይደሉም (መስፍን አረጋ)

አባ ሠረቀ ብርሃን በሽተኛ እንጅ በሽታ አይደሉም  

መስፍን አረጋ

የሐይማኖት አባት ናቸው ተብለው አባ የሚባሉት አባ ሠረቀ ብርሃን፣ በሐይማኖት አባትነታችው ፍቅርን መስበክ ሲገባቸው ጥላቻን ይነዛሉ።  ይህን የሚያደርጉት ግን በሽተኛ እንጅ በሽታ ስለሆኑ አይደለም።  በሽታቸው ደግሞ ወያኔ የሚባል በቀላሉ የሚተላለፍ (የሚዛመት) ወረርሽኝ ነው።  

በተመሳሳይ መንገድ ካማራ ጋር አትጋቡ ከተጋባችሁም ተፋቱ እያሉ ለመንጋቸው ትዛዝ የሚሰጡት የትግሬ ልሂቆችና፣ አማራን ጥፍራም፣ ፎጣ ለባሽ እያሉ የሚዘልፉት፣ አማራ ናቸው የሚባሉ የሐይማኖት አባቶችን ደግሞ ወያኔን ስለተቃወሙ ብቻ ሚሊሻ ምናምን እያሉ ፀያፍ ስድብ የሚሳደቡት፣ አፋቸው ለከት የሌለው፣ ስድ አፍ የሚዲያ ሰወች ወያኔ በሚባለው ተዛማች ወረርሽኝ የታመሙ በሽተኞች እንጅ በሽቶች አይደሉም።  

አሮሞን በተመለከተ ደግሞ ጭራቅ አሕመድ፣ ጃዋር ሙሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሽመልስ አበዲሳ፣ ለማ መገርሳ፣ አባዱላ ገመዳና የመሳሰሉት ሰወች ኦነግ በሚባል ተዛማች ወረርሽኝ የታመሙ የወረርሽኝ በሽተኞች እንጅ በሽቶች አይደሉም።   

ስለዚህም ወያኔ በሚባለው ወረርሽኝ የሚሰቃዩ በሽተኞች ከበሽታቸው የሚድኑት በሽታቸውን ወያኔን በማጥፋት ሲሆን፣ ኦነግ በሚባለው ወረርሽኝ የሚሰቃዩ በሽተኞችም ከበሽታቸው የሚድኑትን በሽታቸውን ኦነግን በማጥፋት ነው።  ወያኔና ኦነግ ተዛማች ወረርሽኞች ስለሆኑ ደግሞ፣ እነዚህን በሽታወች ማጥፋት የሚቻለው በሁለት ደረጃወች ነው፡፡  የመጀመርያው ደረጃ ወረርሽኙ እጅግ የጠናባቸውን አሉላ ሰለሞንና በቀለ ገርባን የመሳሰሉትን በሽተኞች እየለቀሙ መቀሰግ፣ ማለትም ቀሳ (quarantine) ማስገባት ነው፡፡  ሁለተኛው ደረጃ ደግሞ ለጎጠኝነት ወረረሽኝ ፍቱን መድሐኒት መፍጠር፣ የተፈጠረም ካለ መጠቀም ነው።

እንደመታደል ሁኖ በጦቢያ ውስጥ ለተዛመቱት ወያኔና ኦነግ ለሚባሉት ወረርሽኞች ፍቱን መድሐኒት አለ፡፡  እሱም የጎጠኝነት ፀር የሆነውን ያማራ ሕዝብ ትግል ማጠናከር ነው።  ያማራ ሕዝብ ደግሞ ለሱ ለራሱ ሕልውና ሲል፣ መነሻው አማራ መድረሻው ጦቢያ የሆነውን፣ የፀረ ወያኔና ኦነግ ትግሉን እንደ ሰደድ እሳት እያስፋፋው ይገኛል።  የትግሉ ዐላማ ደግሞ ያማራንና የጦቢያን ሕልውና ለዘላለም ማረጋገጥ ነው፡፡  ይህን ማድረግ የሚቻለው ደግሞ ያማራና የጦቢያ የሕልውና ጠላቶች የሆኑት ወያኔና ኦነግ ሙተው ተቀብረው ለዘላለም ሲወገዱ ብቻ ነው።  ወያኔና ኦነግ የሚባሉት፣ ዘር ጨፍጫፊ፣ አገር አጥፊ ወረርሽኞች (ልክ እንደ ፈንጣጣ ወረረሽኝ) ከምድረገፅ ከጠፉ ደግሞ፣ በወረርሽኞቹ የሚያዙ አባ ሠረቀ ብርሃንን የመሰሉ በሽተኞች አይኖሩም፡፡    

 መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic