>

መነበብ ያለበት የመምህር ዘመድኩን በቀለ ''ርዕሰ አንቀጽ''

“ርዕሰ አንቀጽ”

 

“…ጌታቸው ረዳና ደብረ ጽዮን ተጣሉ። እና ለምን አይባሉም አንተ ምን አገባህ? ምን ይጠበስልህ? በህወሓት ውስጥ ክፍፍል እየተፈጠረ ነው። ይፈጠራ ታዲያ አንተ ምንአገባህ? ይመለከትሃል? አይደለም የውስጥ በውጭ ለምን አይራኮቱም። አይናጩም፣ አይፈረካከሱም። ምን ጥልቅ ያደርግሃል? ህወሓት ከኤርትራ ጋር ልትዋጋ ነው። እና ምን ይጠበስልህ? አንተ ምን ቤት ነህ በቤተሰብ ጠብ መሃል ጥልቅ ብለህ የምታቦከው? ቡካቲያም…

“…አቢይ በወደብና በቀይ ባሕር ምክንያት ወደ ጦርነት ሊገባ ነው። እና ምን ይጠበስልህ? መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት። አቢይም ሆነ አክቲቪስቱ ስለዚህ ጉዳይ በኦሮሚኛ ሲያወሩ ሰምተሃል? አልሰማህም። በአማርኛ ብቻ የሚለፈልፉት ለምን ይመስልሃል? ሂድ በለው። ንካው በለው። ይልቅ አፋር ይጠንቀቅ። ከኤርትራ ጋር ጦርነት ብለው የውሸት ገጥመው ከወያኔ ጦርነት የተረፈውን አፋርን በጥቅሴ አውድመው እንደ ትግሬ በሻሻ አድርገው በዜሮ እንዳያስቀሩት ለአፋር ንገር። አቢይ አፋር መመላለስ ካበዛ ነገር አለ ብለህ ንገረው። ጨው…

“…በዐማራ ክልል የብአዴን ፌክ ፋኖዎች ተነሥተዋል። አዎ ተነሥተዋል። ምልክታቸውም መዝረፍ፣ ገበሬ ማማረር፣ ሕዝብን ማበሳጨት ነው። በዐማራ ህልውና ላይ የመጡ ጥቂት ባንዳዎች ስለሆኑ እነዚህን መደምሰሱ በጣም ቀላል ነው። እናም አንተ እዚህ ላይ ሥራ። ዳያስጶራ ነን ብለው ለፋኖ መሪዎች ዶላር እያሳዩ ትግሉን ለመጥለፍ በሚንከላወሱ ውሾች ላይም ወጥረህ ሥራ።

“…አናትህ ለ2 ይከፈልና ሁለተኛ ስለ ወያኔ መከፋፈል አታውራብኝ። የአባቴ አምላክ በመብረቅ ለምን ሺ ቦታ አይሰነጣጥቃትም። ምንአገባኝ አንተስ ምንአገባህ…? ኮተታም። አጀንዳ አትቀይር። የዐማራ ትግል መሠረት ይዟል። አንበሳው ፒኮኳን ያደቅቃል። ስለሱ አውራ። ራቡን ለማምለጥ ጸልይ።

•ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው…!

Filed in: Amharic