>

የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት በአበዳሪዎች የዕዳ ወጥመድ ተይዟል!

የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት በአበዳሪዎች የዕዳ ወጥመድ ተይዟል!

 ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢትኢኮኖሚ /ET- ECONOMY) ጥናታዊ ፁሁፍ

 

በ2016ዓ/ም የኢትዮጵያ ባንኮች ኪሳራ ያውጃሉ (Banking crisis in Ethiopia) የኢትዮጵያ የብር የመግዛት አቅምን ማዳከም  የኮነሬል አብይ አህመድ ፣ ከባንኮች የተበደረውን አንድ ነጥብ ሰባት ትሪሊዮን ብር መክፈል ስለማይችል ባንኮች ይከስራሉ እንዲሁም የኢትዮጵያ የብር የመግዛት አቅም ማዳከም ማለትም አንድ ዶላር በሕጋዊው የውጭ ምንዛሪ ተመን 55.5 (ሃምሳ አምስት ነጥብ አምስት) ብር የደረሰ ሲሆን፣ በጥቁር ገበያው ግን አንድ ዶላር እስከ 110 (አንድ መቶ አስር) ብር እየተመነዘረ ይገኛል፡፡ አይ ኤም ኤፍ የኢትዮጵያ ሕጋዊ የብር መግዛት አቅም በጥቁር ገበያ ተመን እንዲመነዘር ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሚሊዮን ብር ባንክ ያስቀመጠ ሰው አስራስምንት ሽህ ዶላር ይኖረዋል፡፡ የብር የመግዛት አቅም በ110 ብር ከተዳከመ አንድ ሚሊዮን ብር ባንክ ያስቀመጠ ሰው ዘጠኝ ሽህ ዶላር ይኖረዋል፡፡ ገንዘብ አስቀማጩ ሃብት በግማሽ ቀንሶል ማለት ነው፡፡ አይኤም ኤፍ የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት፣ የባንክ ዘርፉን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት እንዲያደርግ መመሪያ ሠጥተዋል፡፡ የኦህዴድ ብልጽግና የጦርነት ኢኮኖሚ  የብር ኖት እያተመ በኢኮኖሚው ውስጥ ያሰራጫል ይበትናል፡፡

የኢትዮጵያ የብር የመግዛት አቅምን ማዳከም  (Devaluation) የአለም ባንክና የዓለም ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ)  የኢትዮጵያ የብድር ጫና ክምችት፣ የዕዳ የወለድ ምጣኔ መጨመር፣ የውጪ ንግድ ገቢ መቀነስ፣ የውጪ ምንዛሪ ክምችት መመናመን የተነሳ፤ ኢትዮጵያ  የብርን የመግዛት አቅም 95 (ዘጠና አምስት) በመቶ ማዳከም ይጠበቅባታል፡፡  ይህን ካደረገችም የሁለት ቢሊዮን ዶላር ብድር እንደሚፈቀድላት ገልጸዋል፡፡ በዚህ መሠረት የአይ ኤም ኤፍ ምክረ ሃሳብ መሠረት የውጪ ምንዛሬው በነፃ ገበያ ማለትም በጥቁር ገበያው መቶ አስር ብር   እንዲመነዘር አዘዋል፡፡ በዚህ መልክ የብር መርከስ ውጤቱ ኢትዮጵያ በውጪ ንግድ የምትልከው ምርትና ሸቀጥ ዋጋቸው በእጥፍ ይረክሳሉ፡፡ በኢትዮጵያ የውጪ ባንኮችም ገብተው በነጻው ገበያ እንዲወዳደሩና እንዲሠሩ  ኮነሬል አብይ አህመድ ትእዛዝ ወርዶላቸዋል፡፡ In 2023, the Government of Ethiopia is in ongoing discussions with the IMF on a potential USD 2 billion lending programme to stabilize the macroeconomy. Discussions revolve around exchange rate reform, appropriate fiscal and monetary policy, and external debt restructuring.

በፊች ምደባ፣የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ደረጃ ሲሲሲ ኔጌቲቭ ወደ ሲሲ ኔጌቲቨ አሽቆልቁሎል! በዚህም የተነሳ አዲስ ብድር አግኝቶ ወለድ ለመክፈል በኢትዮጵያ ‹የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶች› በሚቀጥሉት ሁለት አመታት ውስጥ በፕራይቬታይዤሽን ከ25 በመቶ እስከ 55 በመቶ ድርሻ የሚሸጡት ካንፓኒዎች ለዓለም አቀፍ ንግድ ጨረታ ይቀርባሉ፣ በምዕራባዊያን የእዳ ወጥመድ ውስጥ የብልፅግና መንግሥት ተጠምዶ ገብቶል፡፡

Fitch Ratings – Hong Kong – 02 Nov 2023: Fitch Ratings has downgraded Ethiopia’s Long-Term Foreign-Currency (LTFC) Issuer Default Rating (IDR) to ‘CC’ from ‘CCC-‘ and affirmed the Long-Term Local-Currency IDR (LTLC) at ‘CCC-‘. ……………………………(1)

{1} የኢትዮጵያ የውጪ ብድርና የብድር ወለድ አገልግሎት ክፍያ (External debt servicing payments) ዘጠኝ ቢሊዮን ዶላር ከ2023 እስከ 2025እኤአ የውጪ ብድርና ወለድ እንደሚሆን ተተንብዮል፡፡  የዩሮ ቦንድ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር በዲሴንበር 2024 እኤአ ያበቃል፡፡ External debt servicing payments of USD 9 billion in 2023-2025 presents liquidity challenges. A USD 1 billion Eurobond is due in December 2024.

ከጁን 30 ቀን 2022 እኤአ ድረስ፣ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ ዕዳ 2.642 (ሁለት ነጥብ ስድስት አርባ ሁለት) ትሪሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የአገር ውስጥ ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.7 (አንድ ነጥብ ሰባት) ትሪሊዮን 242 ቢሊዮን ብር  እንዲሁም የውጭ አገር ውዝፍ ዕዳ መጠን 1.29 (አንድ ነጥብ ሃያ ዘጠኝ) ትሪሊዮን ብር ይገመታል፡፡  የሃገር ውስጥ ዕዳ  1.7 ትሪሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን የአበዳሪዎቾ ባንኮች ያበደሩትን ገንዘብ ከኮነሬል አብይ አህመድ የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት የማግኘት እድላቸው ‹‹ላም አለኝ በሰማይ ወተቶንም አላይ›› ነው፡፡ ባንኮች ከሰሩ ማለት የባንክ ደንበኞች ገንዘብ አስቀማጩ ህዝብ ከሰረ ማለት ነው፡፡ ኮነሬሉ ከሰማይ ውኃ ሳይሆን ብር አዝንል፡፡ 

በ2016ዓ/ም በኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት ኪሳራ የሚያውጁት የኢትዮጵያ ባንኮች ስብጥር ውስጥ፡-  

  • {1} የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 833 (ስምንት መቶ ሠላሳ ሦስት) ቢሊዮን ብር ያበደረ ሲሆን ይህውም ከጠቅላላ ብድሩ  49 (አርባ ዘጠኝ) በመቶ ይሆናል፡፡ 
  • {2} የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 527 (አምስት መቶ ሃያ ሰባት) ቢሊዮን ብር ያበደረ ሲሆን ይህውም  ከጠቅላላ ብድሩ 31 (ሠላሳ አንድ) በመቶ ይሆናል፡፡ 
  • {3} የኢትዮጵያ ጡረታ ፈንድ 289 (ሁለት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ) ቢሊዮን ብር ያበደረ ሲሆን ይህውም ከጠቅላላ ብድሩ 17 (አስራ ሰባት) በመቶ ይሆናል፡፡ ጡረተኞች ያስቀመጡትን የቱረታ ገንዘብ አያገኙትም፡፡
  • {4} የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 51 (ሃምሳ አንድ) ቢሊዮን ብር ያበደረ ሲሆን ይህውም  ከጠቅላላ ብድሩ 3 (ሦስት) በመቶ ይሆናል፡፡ በኦሕዴድ / ብልፅግና ዘመን መንግሥት የጦርነት ኢኮኖሚ የሃገሪቱን በጀት አጠቃሎ ለመከላከያ ሠራዊቱ የመሣሪያ ትጥቅና ተተኮሽ ግዥ፣ ደሞዝ፣ ምግብ፣ ዩኒፎርም፣ የትራንስፖርት ወጪ፣ የቀን አበል፣ ወዘተ ወጪዎች በመጠቀም ሁለት አመት ከስድስት ወራት የፈጀ ጦርነት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ መንግሥት የበጀት ጉድለቱን ለማሟላት፣  በከፍተኛ ደረጃ ብር የማተም የገንዘብ ፖሊሲ  ሥራ ላይ ተጠምዶል፡፡

የዋጋ ንረት (Inflation)፡- የሸቀጣ ሸቀጦችና ምርቶች ዋጋ ከአመት ወደ አመት እየጨመረ በመሄድ በአፕሪል 2023እኤአ 33.5 በመቶ ሲገመት የምግብ ነክ የዋጋ ግሽበት 31.8 በመቶ ሲገመት፣ የምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች የዋጋ ግሽበት 36.1 በመቶ እንደሆነ ተገልፆል፡፡ የዋጋ ንረቱ ዋና መንስኤ በሃገር ውስጥ የመንግሥት ወጪ ከፍተኛ መሆን ሲሆን ከውጪ ተገዝቶ የሚገባው የነዳጂ ወጪና የምግብ ፍጆታ ግዢ እየጨመረ መሄድ የዋጋ ንረቱን አባብሶታል፡፡ በኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት የምግብ ነክ የዋጋ ግሽበት 45 በመቶ ሲገመት፣ የምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች የዋጋ ግሽበት 40 በመቶ እንደሆነ ይገመታል፡፡ Inflation continues to be stubbornly high in 2023. Year-on-year headline inflation in April 2023 stood at 33.5% while food and non-food inflations remain high at 31.8% and 36.1%, respectively. The drivers of inflation are both domestic (government spending) and external (inflation from fuel and food imports)……………………………….………(2) 

የንግድ ሚዛን (Balance of Payment)፡- በ2023 እኤአ የንግድ ሚዛን ኪሳራ አንድ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ዶላር እንደሚገመት ዩኤንዲፒ ተንብዮል፡፡ Balance of Payment: Overall, the BOP deficit in 2023 is projected by UNDP to be close to USD 1.6 billion.

{2} የውጭ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችት መቀነስ (International reserves) በ2022እኤአ የኢትዮጵያ የውጭ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችት 1.5 (አንድ ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ዶላር አሽቆልቁሎል፡፡ የገንዘብ ክምችቱ የአንድ ወር የገቢ ንግድ ውጪን ብቻ ሊሸፍን ቢችል ነው፡፡ Ethiopia’s FX reserves have fallen to USD 1.5 billion, enough just to cover less than a month’s import bills but insufficient to satisfy debt commitments. According to Fitch’s latest outlook, published on December 20, 2022, the current account deficit will remain unchanged until 2023.Dec 24, 2022. International reserves declined to about 1 month of import cover in 2022 from 2.2 months in 2021…… Foreign exchange: Foreign exchange reserves are estimated in May 2023 at USD 0.8 billion covering less than three weeks of imports. በ2021 እኤአ ለሁለት ነጥብ ሁለት ወራት፣ ለ2022እኤአ አንድ ወር እንዲሁም በ2023እኤአ የዓለም አቀፍ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችት ስምንት መቶ ሚሊዮን ዶላር ሲሆን ለሦስት ሳምንት በታች ከውጪ እቃዎች ሊያስመጣ ይችላል፡፡  የውጭ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችት ከተመናመነ ለመንግሥት ለህዝብ መድሓኒት መግዣ  እንን አይኖረውም!  

{3} ከውጪ የተላከ ገንዘብ (Remittance) ገቢ ቀን፡- በባህር ማዶ የሚኖረው ኢትዮጵያዊያን በሚልኩት ገንዘብ የሚያስተዳድሩት ህዝብ ሢሶ መንግስትነታቸውን ዛሬም አረጋግጠዋል፡፡ ከ1981 እኤአ እስከ 2018 እኤአ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከውጪ የተላከ ገንዘብ (Remittance) ድርሻ 6.9 በመቶ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት gross domestic product (GDP) እንደነበር ይታወቃል፡፡  Remittance accounted for 6.9% of Ethiopia’s GDP on average from 1981 to 2018 (WDI, 2020), and remittance is an extremely important source of foreign exchange for Ethiopia, perhaps larger than the export earnings of the country in its foreign exchange generation capacity.Jun 8, 2021 ከውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች  የወያኔን የግፍ አገዛዝ በመቃወምና የአብይን መንግሥት በመደገፍ በተግባር ወደ ሃገር ቤት የላኩትን ገንዘብ በመጨመር በ2013 ዓ/ም 4.3 (አራት ነጥብ ሦስት) ቢሊዮን ዶላር፣በ2014 ዓ/ም 5.6 (አምስት ነጥብ ስድስት) ቢሊዮን ዶላር በመላክና ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በማዋጣት ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ኮነሬል አብይ መንግሥት ከኢትዮጵያዊነት ወደ ኦነግነት የዘር ፖለቲካ ጆንያ ውስጥ በገቡ ጊዜ ዲያስፖራው ተቃወማቸው፣ ሸሻቸው እንዲሁም ድጋፉን ነሳቸው፡፡ ዲያስፖራው ከውጪ የሚልከው ገንዘብ ሰባ በመቶ እንደቀነሰና ወደ መንግሥት ካዝና እንዳይገባ በማድረግ የኢኮኖሚ እቀባ መንግሥት ላይ ቀጠለ፡፡ በዚህም መሠረት በ2015ዓ/ም ስድስት ወራት ውስጥ 1.72 (አንድ ነጥብ ሰባ ሁለት) ቢሊዮን ዶላር ብቻ እንደተገኘና በሚቀጥሉት ወራቶች እየነጠፈ እንደሚሄድ የተቃዋሚ አስተባባሪዎቹ ገልፀዋል፡፡ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በ2015 ዓ/ም ከውጪ በግለሰቦች የተላከ ሃዋላ 4.6 ቢሊዮን ዶላር ብለው ለፓርላማ ያቀረቡት የውሸት ሪፖርት መሆኑ ይታወቃል፡፡  ዲያስፖራው ወገናችን ወደ ሀገር ቤት የሚልከው ገንዘብ ሃገራችን ከውጪ ንግድ ገቢ (ኤክስፖርት) እንደሚበልጥ ይታወቃል፡፡ እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ሆኖ አገልግሎል፡፡ ለዚህ ነው ዲያስፖራው ወገናችን ሢሦ መንግስት የሚባለው ለአንድ ሦስተኛው ህዝብ ቀለብ በመሸመት፣ ሸማ ገዝቶ በማልበስ፣ ወገኖቹን በማሳከምና በማስተማርና በሃገር ውስጥ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት በማድረግ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ወደ ሀገር ቤት በማሸጋገር ወዘተ  ከመንግሥት ተብዬው የተሸለ ስብዓዊ ልማት በማፋጠን ለሃገር ኢከኖሚ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረጋቸው በሃገራቸው ጉዳይ ከማንም በላይ ያገባቸዋል እንላለን፡፡   

{4} ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ቀንሶል (Foreign Direct Investment) በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ያላቸውን አስተዋፅኦ በካፒታል፣ በሙያ ክህሎት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ  ወዘተ  ያበረከቱትን ድርሻ  ከፍተኛ ነው፡፡ political stability and government policy commitment are the most important factors. Moreover economic factors such as labour, trade connection, size of the export sector, external debt, and market size of the countries are found to be significant determinants of FDI flows to African countries.

በኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት በ2018 አኤአ $3.36B (ሦስት ነጥብ ሠላሳ ስድስት) ቢሊዮን ዶላር፣ በ2019 አኤአ $2.55B (ሁለት ነጥብ ሃምሳ አምስት) ቢሊዮን ዶላር፣በ2020 አኤአ $2.40B (ሁለት ነጥብ አርባ)ቢሊዮን ዶላር፣በ2021 አኤአ $4.26B (አራት ነጥብ ሃያ ስድስት)ቢሊዮን ዶላር፣ በባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ወደ ኢትዮጵያ ካፒታላቸውን በማስገባት ኢንቨስት አድርገዋል፡፡ በ2022 አኤአ (2015ዓ/ም) $3.4B (ሦት አራት ነጥብ አራ)ቢሊዮን ዶላር፣እንደነበር የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ እየቀነሰ እንደመጣ ገልጸዋል፡፡

በ2023 እኤአ ዘጠኝ ወራት ሪፖርት መሠረት ሃገሪቱ 2.67 (ሁለት ነጥብ ስልሳ ሰባት) ቢሊዮን ዶላር ወይም 59 በመቶ  ቀጥተኛ የውጪ ካፒታል ኢንቨስትመንት ዝቅ እያለና እየወረደ ሄዶል፡፡ በቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት  ለማግኘት ታቅዶ የነበረው 4.5 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡  In the nine-months of FY23, the country attracted USD 2.67 billion worth of capital investment out of a target of USD 4.5 billion. 

በኢትዮጵያ የፖለቲካ አለመረጋጋትና የደህንነት ስጋቶች የተነሳ የተከሰቱ የዘር ተኮር ግጭቶች በተለይም በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተው ጦርነት ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ቀንሶታል፡፡የውጭ ኢንቨስተሮች ሰላም ከሌለ፣ ገንዘባቸውን ስጋት ባለበት አካባቢዎች ኢንቨስት አያደርጉም፡፡ የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት አማራ ክልልን በጦርነት ለማጥቃትና የፋኖ አርበኞችን የህልውና ትግል ለማጨናገፍ ያላገላበጠው ድንጋይ የለም፡፡ የኮነሬል አብይ ኦህዴድ ብልፅግና ከትግራይ ጦርነት የሚሊዮኖች እልቂትና የሃያ ስምንት ቢሊዮን ዶላር የኢኮኖሚ ውድመት  ምንም አልተማረም፡፡  በአማራ የህልውና ጦርነትም በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ወቶአደሮች የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ከአገር መውጣት ይጀምራሉ ኢኮኖሚው ይወድቃል፡፡ Insecurity and political instability associated with various ethnic conflicts – particularly the conflict in northern Ethiopia – have negatively impacted the investment climate and dissuaded foreign direct investment (FDI).Jul 29, 2022

በኢትዮጵያ ህይወታቸውን አጥተወል፣ ንብረት ወደሞል፡፡ በዚህም የተነሳ ኢንቨስተሮች ከሃገር ወጥተዋል፣  ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት በጦርነቱ ምክንያት ከ4.26 B ወደ 2.67 B ቢሊዮን ዶላር በመውረድ ተሸመድምዶል፡፡ 

  • ኢትዮጵያ ኢንደስትሪያል ፓርክ፣(Ethiopian Industrial Park) 51(ኃምሳ አንድ) የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ከኢንደስትሪል ፓርክ ጥለው ወጥተዋል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት  ኃምሳ አንድ ኢንቨስተሮች ከኢንደስትሪል ፓርክ ጥለው ወጥተዋል፣ ምክንያታቸውም በመሰረቃቸውና በቢሮክራሲያዊ አሰራር በመማረር ማለትም በብልሹ መልካም አስተዳደር  የተነሳ ነው፡፡  The Ethiopian Investment Commission has indicated to Parliament in May 2023 that 51 investors have left the industrial parks due to theft and bureaucratic bottlenecks. 
  • ኢትዮሊዝ (Ethio Lease):- በኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ኢትዮሊዝ የአሜሪካ የግል ኮርፖሬሽን ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ልዩ ልዩ የመሠረተ-ልማት መሣሪያዎች(ካፒታል ጉድስ) በድርጅቱ የውጭ ምንዛሪ ገዝቶ ወደ ሃገር ውስጥ አስገብቶ በማከራየት  አገልግሎት የሚሰጥ ካንፓኒ ከኢትዮጵያ ለቆ ወጥቶል፡፡ Ethio Lease is part of the AAFC group of companies. AAFC is a privately owned US corporation, with its main office in New York. Ethio Lease is also the first foreign-owned company with a license to operate in a corner of the Ethiopian Financial Services sector. ……If the equipment needs to be imported, Ethio Lease will buy the equipment abroad, using foreign currency from its parent company, AAFC. Ethio Lease customers can pay the lease fee in Ethiopian Birr. While leasing comes in many forms and shapes, for now the only form of leasing that the NBE will allow is a capital lease (aka “financial lease” or “full pay-out” lease)………………………………….(3) 
  • ኢትዮቴሌኮም (Ethiotelecom):- ኢትዮቴሌኮም ሶስተኛ ዓለም አቀፍ ጫረታ ተሠረዘ፡- በሃገሪቱ ባለ  ጦርነት የተነሳ ዘለቄታዊ ልማት ማስፋፋት ስለማይቻል ብዙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሳይሳተፉ ቀርተዋል፡፡ ኮነሬል አብይ ኢትዮቴሌኮም ድርሻ በከፊል በመሸጥ ዶላር ለማግኘት ቢቆምጥም፣ በጫረታው የውጪ ድርጅቶች አልተሳተፉም፣ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ጦርነት ባለበት አገር ገብተው መስራት አይፈልጉም፡፡ ለአንድ አገር ለዘለቄታዊ  የኢኮኖሚ እድገት የኢንቨስትመንት ፍስት ቀጣይነት ዋናው ሠላምና መረጋጋት ነው፡፡ Ethiopia cancels process for offering third telecoms licence …The Ethiopian government has confirmed its cancellation of a process offering the country’s third licence, after receiving low bids, ……( https://www.telecompaper.com › news › ethiopia-cancels…)
  • ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ (Moha Soft Drinks factory)፡- ሞሃ ፋብሪካ ፔፕሲኮላ፣ ሚሪንዳ፣ሰበን አፕ፣ ኩል ውሓ በማምረት ይታወቃል፡፡ ሞሃ ፋብሪካ ከባሀር ማዶ ለፋብሪካው ግብዓት የሚሆኑ ኬሚካሎችና ማሽነሪዎች፣ ጠርሙሶች፣ለማሰገባት የውጪ ምንዛሪ በማጣት ስራውን ለማቆም ተገዶል፡፡ ሞሃ ፋብሪካ በሃገሪቱ ለሠላሳ አመታት በመስራት ስምንት ማምረቻ በሃገሪቱ በመገንባት ለስምንት ሽህ ሠራተኞች የሥራ ዕድል የፈጠረ ድርጅት ነበር፡፡ Recent reports from local sources have indicated that some foreign investors are quitting operations in Ethiopia due to chronic foreign currency shortage in the country to import products. A company owned by Ethiopian-born Saudi Billionaire, Mohammed Alamudi, is among those affected by the problem.  Moha Soft Drinks factory is moving in the direction of closing down all its operations in Ethiopia, according to a report by The Ethiopian Reporter Published on November 25, 2023……….. The main problem the company has been facing was foreign currency needed for importing materials for its operation including bottles , ingredients needed for soft drinks and machineries. Moha Soft Drinks Industry Share company has been producing Pepsi Cola Products and Mineral water for nearly thirty years since 1996 and the number of plants in the country reached eight. The source cited its informant to report that “More than 8,000 employees have lost or resigned from their jobs at Moha over the past year.” ……………………………………..(4) 
  • የኢትዮጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን ስር የሚገኙ ፍብሪካዎችን ለአገር ውስጥና ለባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ለመሸጥ ጨረታ ወጥቶ ምንም ገዥ አልተገኘም፡፡
  • የኢትዮጵያ ዓየር መንገድና የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ሠላሳ በመቶ ድርሻ ለኤርትራ ሠጥቶ የአሰብን ወደብ የመውስድ ምኞት፡፡ ኮነሬል አብይ አህመድ  እብደት የቀይ ባህር ኬኛ፣ አሰብ ኬኛ፣ አዲስ አበባ ኬኛ 

{5} የባህር ማዶ እርዳታና ኦፊሽያል ዲቨሎፕመንት አሲስታንስ ድጋፍ  መቆረጥ (Foreign Aid and Official Development Assistance received)፡-እርዳታው ከአምስት ቢሊዮን ዶላር ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር ወርዶል፡፡በኢትዮጵያ የባህር ማዶ እርዳታ ከጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት (GDP) ድርሻ 9.3 በመቶ በ1982 እኤአ የነበረ ሲሆን በ2019 እኤአ ደግሞ 42.9 በመቶ እያደገ እንደሄደ በጥናት ተረጋግጦል፡፡ ኢትዮጵያ በየአመቱ ከሦስት እስከ አራት ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ታገኝ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በዚህም መሠረት እንደ ናሙና በ2015 (3.239 ቢሊዮን ዶላር)፣ በ2016 (4.084 ቢሊዮን ዶላር)፣በ2017 (4.125 ቢሊዮን ዶላር)፣ በ2018 (4.941 ቢሊዮን ዶላር)፣ በ2019 (4.810 ቢሊዮን ዶላር)የባህር ማዶ እርዳታ አግኝታለች፡፡ (The Global Economy.com) ድረ-ገፅ መረጃ ይገልጻል፡፡ How much of Ethiopia’s GDP is aid? It is clearly observe from the figure 2 on average the share of foreign aid to GDP showed increasing trend from 9.3% in 1982 to 42.9% in 2019; on the other hand there is slight fluctuation in GDP per capital growth rate over time, it is also evident that there is a rising trend from 0.9% in the year 1981 to 5.6% in …Jul 20, 2022. ከኢትዮጵያ የሰሜኑ ጦርነት በኃላ  የባህር ማዶ እርዳታና ኦፊሽያል ዲቨሎፕመንት አሲስታንስ ድጋፍ በመአቀብ ተመታ፡፡ ኢትዮጵያ ጦርነቱን ካላቆመች የሚላስ የሚቀመስ ዶላር እንደማታገኝ ተፈረደባት፡፡ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በ2015 ዓ/ም አንድ ቢሊዮን ዶላር እርዳታ እንዳገኘች ገልጸዋል፡፡ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት በ2023ዕኤአ 331 ሚሊዮን ዶላር ለስብዓዊ እርዳታ አበረከተ፣ ከሦስትና አራት ቢሊዮን ዶላር ወደ ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እንደ ተሸቆለቆለ መረጃው ይጠቁማል፡፡ የጦርነት መዘዙ ይሄ ነው አሁንም የፈረንጅ እርዳት ለማግኘት ካሻን ከጦርነት መታቀብ ግድ ይላል እንላለን፡፡ የኮነሬል አብይ መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ የሚያካሂደውን ጦርነት በአስቸይ እንዲያቆምና በሠላማዊ መንገድ እንዲፈታ፡፡ 

{6} ካፒታል ኩብለላ 44 ቢሊዮን ዶላር (Capital flight)፡- ከሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ የሚወጣ የውጪ ምንዛሪ ካፒታል ኩብለላ Capital flight 2 እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር በአመት እንደሚደርስ የአፍሪካው ልጅ  ታቡ ኢንቤኪ አጋልጠዋል፡፡ በኦህዴድ/ብልፅግና መንግሥት አምስት ዓመት አገዛዝ ዘመን የውጭ ምንዛሪ ኩብለላ ዋና ተዋናዬች ከፍተኛ የመንግስት ሹማምንቶች የሚከወን ሲሆን በሃገሪቱ በሚስተዋለው ህዝባዊ እንቢተኛነትና አመጽ ፍራቻ የተነሳ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በሃገሪቱ የብር የመግዛት አቅመ ከጊዜ ወደ ጊዜ መውደቅ የተነሳና በብሔራዊ ባንክ የብር የማርከስ ሂደት፣ በእቃዎች ዋጋ እየጨመረ መሄድ የኑሮ ውድነት እየተባባሰ የሚሄደው ሃያ  በቢሊዮን  ዶላር ከሀገር ውስጥ መኮብለል የተነሳ ሁኔታውን አባብሶታል፡፡ Results also show, for trade with only advanced countries, trade misinvoicing has cost Ethiopia $6-35 billion between 2008 and 2016; for trade with emerging economies (including China and India), Ethiopia has lost $15 -78 billion to trade mis-invoicing during the same period. If we just take the sum of the lowest estimates of trade mis-invoicing, Ethiopia had lost over $20 billion due to trade mis-invoicing with all its trading partners during the study period.………………….(5) 

በህወኃት/ኢህአዲግ መንግስት ዘመን 1991 እስከ 2018እኤአ የካፒታል ኩብለላ በአማካኝ በየአመቱ አንድ ቢሊዮን ዶላር ከአገር ይወጣል:: በህወኃት/ኢህአዲግ በህገወጥ መንገድ ከሃገር ውስጥ የወጣ ካፒታልና የንዋይ ኩብለላ 27 (ሃያ ሰባት) ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር ከኢትዬጵያ ረሃብተኛ ህዝብ ተሰርቆ ወደ ተለያዩ ባህር ማዶ አገራት ተቀምጦል፡፡ 

የማክሮ ኢኮኖሚ ተንታኝና የጥናት ተመራማሪ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ በሃገሪቱ ወደ ውጪ ሃገር የኮበለለው  ኃብት ካለፈው አርባ አራት አመታት ከነበረው  የኃብት ዝርፍያ፣ ባለንበት በዚህ አስር አመት ውስጥ ከሃገሪቱ የተዘረፈው 44 (አርባ አራት)ቢሊዮን ዶላር  ኃብት አስር እጥፍ ይበልጣል፡፡  የኮነሬል አብይ አህመድ ዘመን ስድስት አመታት ወደ ባህር ማዶ የኮበለለ ገንዘብ የትየለሌ መሆኑን በህወኃት/ኢህአዲግ ዘመን ጋር በማወዳደር መገንዘብ ይቻላል፡፡ 

Apr 4, 2023 — Capital flight has cost Ethiopia 44 billion USD over the last ten years … Macroeconomic analyst and researcher Professor Alemayehu Geda claims  that the amount of wealth purported to have left the country in the previous 10 years is 10 times more than it was 44 years ago. The lecturer, Alemayehu Geda, claimed to have fled the country. According to recent estimates, more foreign currency has been printed in the last ten years than in the 44 before. The sudden increase in riches is said to be very frightening. Several sources claim that the main causes of this capital flight or money movement are a lack of security in the country and lax government regulation. The researcher told us that in order to stop the government from continuing to lose billions of dollars, problems must be found and holes must be filled. It was also believed that strengthening mining regions based on the dollar trade system, emphasising Kela oversight, and strict legislation and monitoring are required.”…………..(6) 

{7} ኢትዮጵያ  ወታደራዊ ወጪ ( Ethiopia Military expenditure-) አንድ ቢሊዮን ዶላር  እንደ ስቶክሆልም ኢንተርናሽናል ፒስ ሪሰርች  ኢንስቲቲውሽን ጥናት መሠረት፣ ዓለም አቀፍና የሃገራት ወታደራዊ ወጪ አፕሪል 24 ቀን 2023 እኤአ ባወጣው መረጃ መሠረት ኢትዮጵያ  ወታደራዊ ወጪ አንድ ቢሊዮን ዶላር (ሃምሳአራት ቢሊዮን ብር )2022እኤአ እንደደረሰና ከአለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 88 (የሰማንያ ስምንት) በመቶ  እድገት እንዳሳየ  ዘግበዋል፡፡ Addis Abeba – According to new data on global military spending published on Monday, 24 April, by the Stockholm International Peace Research Institute (SIPRI), Ethiopia spent 1 billion USD on military expenditures in 2022, showing an increase of 88 percent from the previous year.………………..……(7) 

ምንጭ

  1. Ethio Lease

(4)Moha Soft Drinks Industry facing closure : 8,000 employees losing jobs /November 27, 2023

(5)©Ethiopian Economics Association VOLUME XXVIII NUMBER 1 April 2019 Pub: September 2020

(6) Capital flight has cost Ethiopia 44 billion USD over the last ten years/Fidel Post/ April 4, 2023 

(7) global military spending

 

Filed in: Amharic