>

የሉባ ገዳ፡  የጨፍጫፊወች ዕድር

የሉባ ገዳ፡  የጨፍጫፊወች ዕድር

መስፍን አረጋ

‹‹አራተኛው ሉባ ቢፎሌ ይባላል፡፡  ደዋሮን ሙሉ በሙሉ አጥፍቶ ፈጠጋርን መውጋት የጀመረው እሱ ነው፡፡  ምርኮኞችን እያጋዘ አገልጋዮች በማድረግ ገርባ አላቸው፡፡››

አባ ባሕርይ፣ ዜናሁ ለጋላ፣ ክፍል 8

መንደርደርያ

የሉባ ገዳ ማለት ማነነታቸውን በውሸት ትርክት ላይ ሙሉ በሙሉ የመሠረቱ የኦሮሞ ፅንፈኞች እንደሚሉት አቃፊ፣ ደጋፊ ሳይሆን ዘራፊ፣ ጨፍጫፊ መሆኑን ከነዚህ ፅንፈኞች ውስጥ ሀቁ እየተገለጠላቸው የመጣው ጥቂቶቹ (እነ ዮናስ ብሩ) በግልፅ መመስከር ጀምረዋል።  መመስከር የጀመሩት እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሎ መላዋን ጦቢያን ለማንቦግቦግ እያስገመገመ ያለው ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል ዓይናቸው ሸፍኖት የነበረውን የኦሮሙማን ሞራ በትንሹም ቢሆን ስለገፈፈላቸው ነው።  በዚህ ጦማር ላይ ደግሞ የሉባ ገዳ ማለት ሌላ ምንም ማለት ሳይሆን የሉባ ጨፍጨፊ ሠራዊት ጭፍጨፋውን ለማሳለጥ የግድ ስለሚያስፈልገው ብቻ የመሠረተው የጨፍጫፊወች ዕድር መሆኑን እንመለከታልለን።  

የጨፍጫፊወች ዕድር

ሌቦች ሲካፍሉ እንጅ ሲሰርቁ አይጣሉም፣ እንደውም በጣም ይዋደዳሉ፣ ካልተዋደዱ ስርቆታቸው አይሳካምና።  ጨፍጫፊወች ደግሞ ድርጊታቸው ከሌቦች እጅግ የከበደ ስለሆነ፣ ጭፍጭፋቸውን ሲያከናውኑ ከሌቦች እጅግ የበለጠ መዋደድ ወዴታቸው ሳይሆን ግዴታቸው ነው።  ዓይናቸውን የሚጥሉት በጭፍጨፋው ቱርፋቶች ላይ እንጅ በጭፍጨፋው ላይ ስላልሆነ፣ ጭፍጨፋውን ለማሳካት ማድረግ /የሚገባቸውን/ ሁሉ በሙሉ ስምምነት፣ ቅንብርና ትብብር ያደርጋሉ፡፡  የጭፍጨፋውን አመራሮች የሚመርጡት ደግሞ የጭፍጨፋውን ቱርፋቶች በተቻላቸው መጠን አመርቂ ለማድረግ በተቻላቸው መጠን ሌት ተቀን ይተጋሉ ብለው ሙሉ በሙሉ የሚያምኑባቸውን ግለሰቦች ብቻና ብቻ ስለሆን፣ አመራረጡ ሙሉ በሙሉ ዲሞክራሲያዊ ነው፡፡  ማናቸውም የጭፍጨፋው አመራር ደግሞ የጭፍጨፋ ሚናውን በሚገባ ካልተወጣ /የሚጎዳው/ እሱ ራሱ በመሆኑ፣ ቦታውን ከሱ ለተሻለ ግለሰብ ለመልቀቅ ሙሉ ደስተኛ ነው፡፡  ማናቸውም የጭፍጨፋው ዐባል ደግሞ ጭፍጨፋውን አመርቂ ለማድረግ ይበጃሉ የሚላቸውን ሐሳቦች የመግለጽ ሙሉ ነጻነት እንዲኖረው ብቻ ሳይሆን፣ እንዲገልጽም በእጅጉ ስለሚበረታታ የጭፍጨፋው አባሎች ነጻነት ገደብ የለውም።  

ሌቦች ስርቆታቸውን ከጨረሱ በኋላ በስርቆቱ ክፍፍል እንደሚጣሉ፣ ጭፍጨፊወችም ጭፍጨፋቸውን ከጨረሱ በኋላ በጭፍጨፋው ቱርፋቶች ክፍፍል ይጣላሉ።  በጭፍጨፋው ወቅት የነበረው ከፍትኛ ፍቅር ወደ ከፍትኛ መናቆር ይለወጣል፡፡  በጭፍጨፋው ወቅት የነበረው በሙሉ ስምምነት ላይ የተመሰረት ቅንብርና ትብብርም፣ ተግባሩን ስለፈፀም ጭፍጨፋው እንደቆመ ወዲያውኑ ይከስማል።  

ጭፍጭፋን ላማሳለጥ የግድ ስለሚያስፈልግ ብቻ በጊዜያዊነት የሚያገለግል፣ ጭፍጨፋው ሲቆም የሚከስም፣ ለጨፍጫፊወች ሙሉ ነፃነት የሚሰጥና፣ የጨፍጭፋው አመራሮቸ በሙሉ ነፃነት የሚመረጡበት የጨፍጫፊወች ቅንብርና ትብብር የጨፍጫፊወች ዕድር ይባላል፡፡  የኦሮሞ ጽንፈኞች ገዳ ዲሞክራሲ ነው የሚሉት ለኦሮሞ ጨፍጫፊወች ሙሉ ነፃነት የሚሰጥና የጨፍጭፋው አመራሮቸ በሙሉ ነፃነት የሚመረጡበት የኦሮሞ ጨፍጫፊወች ዕድር ስለነበረ ነበር።  

የሉባ ገዳ

ኦሮሞ ከመነሻው ፈልሶ፣ በጦቢያ ላይ ተስፋፍቶ፣ ግብርና ተምሮ በቋሚነት ከመስፈሩ በፊት አርብቶ አደር የነበረ በመሆኑ፣ ካኗኗሩ ምንነት የመነጨ ነጻነት የሚመስል መረን ለቀቅነት ወይም ልልነት ነበረው፡፡  ዘላን የተባለበትም ምክኒያት ባሻው ጊዜ ወዳሻው ቦታ ስለሚዘል ነው፡፡  የከብት ጭራ የሚከተል አርብቶ አደር፣ በሬ እንደሚጠምድ አርሶ አደር ጥብቅ ሊሆን አይችልም፣ መሆንም የለበትም፡፡  አርብቶ አደራዊ ኑሮ የሚኖሩ ወይም ደግሞ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ይኖሩ የነበሩ ብሔረሰቦች አኗኗራቸው በተወሰነ ደረጃ ልቅ መሆኑን ለመረዳት ያፋሮችን፣ የኢሳወችን፣ የሱማሌወችን፣ የከረዩወችን፣ የቦረናወችን ልቅ አኗኗር ከደገኛው ጦቢያዊ ጥብቅ አኗኗር ጋር ማነጻጸር ይበቃል፡፡  

ሙሐመድ ሐሰንን የመሳሰሉ የኦሮሞ ልሂቆች ግን የኦሮሞን ከዘላንነት የመነጨ መረን ለቀቅነት ከዲሞክራሲ ጋር ሥራየ ብለው ያምታቱታል፡፡  ይህን የሚያደርጉት ደግሞ የኦሮሞ ብሔረሰብ ከሌላው ጦቢያዊ በተለየ መልክ ዲሞክራቲክ ነበር በማለት በብዙ ረገዶች (በስነቃሎች፣ በጽሑፍነክ ትውፊቶች ወዘተ.) የሚሰማቸውን የዝቅተኝነት ስሜት፣ የባዶነት መንፈስ በውሸት ትርክት ለመወጣት ነው፡፡  በዚህ ረገድ ደግሞ ኦሮምኛ የማያውቀው አስመሮም ለገሰ በኦነጋዊ ባልደረቦቹ የተተረጎመለትን የገዳ ትርክት ተሳስቶ (ወይም ደግሞ ሆን ብሎ) ወደ ዲሞክራሲ ትርክት በመቀየር የጻፋቸው ጽሑፎች ያንበሳውን ሚና ተጫውተዋል፡፡ 

የሉባ የገዳ የሉባን መስፋፋትና መንሰራፋት ለማሳለጥ (make efficient) ብቻና ብቻ የተሰረተ የሉባ የጨፍጫፊወች ዕድር ነበር፡፡  በሌላ አባባል የገዳ ስርዓት በዲሞክራሲ የሚያምን ሕዝብ የሰረተው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ሳይሆን፣ በጭፍጨፋ ለመስፋፋት የግድ ስለሚያስፈልግ ብቻ መስፋፋቱ እስከቀጠለ ድረስ እንዲያገለግል የተሰረተ የሉባ ተስፋፊወች ቅንብርና ትብብር ነበር፡፡  የገዳ ስርዓት የተሰረተው 1522 ዓ.ም ገደማ (ማለትም በ 1515 የተጀመረውን የግራኝ ወረራ ተከትሎ) እንደነበር ራሱ ሙሐመድ ሐሰን ‹‹ኦሮሞና የጦቢያ ክርስቲያናዊ ንጉሥጌ›› (Oromo and the Christian Kingdom of Ethiopia) በተሰኘው በራሱ መጽሐፍ ላይ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡  እዚህ ላይ ደግሞ ትክክል ነው፡፡  የገዳ ስርዓት ከኦሮሞ መስፋፋት በፊትም ሆነ በኋላ አልነበረም፡፡  ስለዚህም የገዳ ስርዓት የኦሮሞን ሕዝብ ዲሞክራሲያዊነት የሚያመለክት ልዩ ክስተት ሳይሆን የሉባ ጨፍጫፊወች ጭፍጨፋቸውን ለማቀላጠፍ ሲሉ ብቻ የሰረቱት የሉባ ጨፍጫፊወች ዕድር ነው፡፡  

የጨፍጨፊወች ዕድር አመራሮች የሚመርጡት የጭፍጨፋውን ቱርፋቶች በተቻላቸው መጠን አመርቂ ለማድረግ በተቻላቸው መጠን ሌት ተቀን ይተጋሉ ተብለው ሙሉ በሙሉ ሲታመንባቸው ብቻና ብቻ ነው፡፡  ስለዚህም ለገዳ ስርዓት አመራርነት የሚታጩት ጭፍጨፋውን በተመለከተ ምንም ዓይነት ቅሬታ፣ ማቅማማት ወይም ማመንታት ይኖራቸዋል ተብለው ሊጠረጠሩ የማይችሉት በሺ የሚቆጠሩ እውነተኛ ኦሮሞወች (ቦረናወች) እንጅ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት የሞጋሳና የጉዲፈቻ ውጤት የሆኑት ገርባወች አይደሉም ማለት ነው፡፡  አባ ባሕርይ በመጽሐፋቸው መግቢያ ላይ እንደገለጹት፣ የኦሮሞ መስፋፋት የተከናወነው ሰውን ለመግደል እንበለ እንቅልፍ ቀን ከሌት በሚተጋ፣ የሆዱ አውሬ (ኮሶው) እንደ እንስሳ በቋንጃው ላይ በሚፍለከለክ፣ የእንስሳነት ባሕርይ በተጠናወተው አረመኔ ሠራዊት ነው፡፡  ተገዶ ገርባ የሆነ ግለሰብ ደግሞ የገዛ ወገኖቹን ለመጨፍጨፍ እስከዚህ ድረስ አይተጋም፡፡   

 በቱርክ ነፍጠኞች የተመራው የግራኝ አህመድ ወረራ፣ አማራ የሚባለውን ጀግንነቱ የተመሠከረለትን ታላቅ ሕዝብ ተቋማት ከሞላ ጎደል ሙሉ በሙሉ በማፈራረስ እጅጉን አዳከመው፡፡  የሱማሌን ጅራፍ ይሸሹ የነበሩት የኦሮሞ አርብቶ አድሮች ደግሞ ግራኝ የፈጠረላቸውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ባባ ገዳወቻቸው መሪነት ድንገተኛ አደጋ እየጣሉ፣ በሐይማኖቱ ቀናኢ የነበረውን አማራ ስምንተኛው ሺ ደረሰ እስከሚያስብሉት ድረስ ሴት፣ ወንድ፣ ሕፃን፣ አዛውንት ሳይሉ በሰይጣናዊ ጭካኔ ጨፈጨፉት፡፡  የፈሪ ብትር ሆድ ይቀትር ነውና፣ የነዚህ አንድም ቀን ፊት ለፊት ተዋግተው የማያውቁ ቱርቂወች ብትር ከግራኝ ብትር የከፋበት አማራ፣ ከግራኝ ቁስል እስከሚያገግም ድረስ ምርጫ ስላልነበረው እጅግ ሰፊና ለም ከነበረው ርስቱ እየተፈናቀለ ከኦሮሞ አደጋ ጣዮች ራሱን በቀላሉ ለመከላከል ወደሚችልባቸው ተራሮች በመሸሽ ዝንጀሮቴኔ ኑሮ ለመኖር ተገደደ፡፡  ለዚህ ደግሞ በሸዋ ተራሮች ላይ አማራ ብቻ፣ ሜዳወቹ ላይ ደግሞ ኦሮሞ ብቻ መስፈሩን መታዝብ ብቻ በቂ ነው።   

የሉባ ጨፍጫፊወች ደግሞ አማራውን በመጨፍጨፍ የወረሱትን ያማራውን ምድር በየጎሳቸው በመከፋፈል ወረምንትስ፣ ወረቅብጥርስ እያሉ ሰየሙት፡፡  የአማራ አገር ፈጠጋር (አሩሲ)፣ የአማራ አገር እናርያ (ወለጋ)፣ የሀድያ አገር ዳዋሮ (ጨርጨር)፣ የጃንጀሮ አገር ገሙ (ኢሉባቦር)፣ የአገው አገር አንጎት (ራያ)፣ ያማራ አገሮች መካነ ሠላም (ቃሉ)፣ ሠገነት (ወረሂመኖ)፣ ዋሰል (ወረኢሉ)፣ ቤተሳባ (ወረባቦ)፣ ገነቴ (የጁ)፣ ምድረገኝ (ከሚሴ)፣ ላኮመልዛ (ወሎ)፣ ግራርያ (ሰላሌ)፣ ገንዝ (ጅባትና ሜጫ)፣ ወጂ (ወንጂ)፣ ሸምብራ ቁሬ (ዱከም)፣ በራራ (ፊንፊኔ) እየተባሉ የመስፋፋት ስም ተሰጣቸው፡፡

አማሮች ነፍጥንና አነፋፈጥን ከፖርቱጋሎች ተምረው ግራኝን አሸንፈው ካገገሙ በኋላ ፊታቸውን ወደ ኦሮሞ ተስፋፊወች አዞሩ፡፡  አደጋ መጣል እንጅ መዋጋት የማይችለው የኦሮሞ ተስፋፊ ባራት ማዕዘናዊ የውጊያ ጥበብ (ፊታውራሪ፣ ግራዝማች፣ ቀኛዝማች፣ ደጃዝማች) በተካኑት አማሮች ፊት መቆም አቃተው፡፡  የነፍጥ ድምጽ ሲሰማ ኦቦው ካቦ ሸማኔ ፈጠነ፡፡   የቱርክ ነፍጠኞች በከፈቱለት ሰፊ በር ያለ ምንም ፊት ለፊት ውጊያ ሰተት ብሎ የገባው የኦሮሞ ተስፋፊ፣ ነፍጥና ነፍጠኛ የሚሉትን ቃሎች አምርሮ ጠላቸው፡፡  ሰይጣኑ፣ ጭራቁ በነፍጠኛ ተመሰለ፡፡  ራቡ፣ ጥማቱ፣ ማይምነቱ፣ አረመኔነቱ በነፍጠኞች ተሳበበ፡፡  

አማሮች ግራኝን ድል ነስተው የሉባን ጭፍጭፋ ሲያስቆሙት፣ ጭፍጨፋውን ለማቀላጠፍ ሲባል ብቻ የተሰረተው የሉባ ገዳ ግልጋሎቱን ስለጨረሰ ወዲያውኑ አከተመ፡፡  በጭፍጨፋው ቱርፋቶች ክፍፍል ላይ እጅጉን የተጠቀሙት የጭፍጨፋው ዕድር ዐባሎች አባ ጅፋር፣ አባ ምንትስ የሚባሉ አምባገነኖች ሆኑ፡፡  በክፍፍሉ የተጎዱት የጭፍጭፋው ዕድር አባሎች በክፍፍሉ በተጠቀሙት ላይ ሲያምፁ ደግሞ ፣ የጎዳችሁ አማራ እንጅ እኛ አይደለንም ተባሉና ፀራማራ ትርክት ተጀመረ።    

በሉባ ጨፍጫፊወች የተጨፈጨፈው ያማራ ሕዝብ ጭፍጨፋውን ስላስቆመና ርስቱን በትንሹም ቢሆን  ስላስመለሰ ብቻ የኦሮሞ ጨቋኝ ተደረጎ ተሳለ፡፡  አማራ ከመስፋፋት ባይገታን ኖሮ፣ አማራ ወደኋላ ባይመልሰን ኖሮ፣ አማራ እንዲህ ወይም እንዲያ ባያደርገን ኖሮ እያሉ ማላዘን ብቸኛ መጽናኛ ሆነ፡፡  ያማራ ጥላቻ ተለኮሰ፡፡  አማራን ካለጠፋነው ያጠፋናል የሚለውን የሮማን ፕሮቻዝካን (Roman Prochazka) ሐሳብ የጦቢያ ፖሊሲያቸው የማዕዘን ዲንጋይ ያደረጉት ምዕራባውያን ደግሞ ሙሐመድ ሐሰንን በመሳሰሉ የኦሮሞ ‹‹ምሁሮች›› አማካኝነት በእሳቱ ላይ ቤንዚን ጨመሩበት፡፡  እሳቱም እንደ ሰደድ ተስፋፋ።  

የሙሐመድ ሐሰን ምሁርነት ሙሉ በሙሉ የተገነባው ኦሮሞን ቤተኛ ሐበሻን መጤ በሚለው ባዱ ትርክቱ ነው፡፡  ይህን ትርክት ግን ብዙም ሐተታ ሳያስፈልግ አጥቂን በቀላሉ ለመከላከል በሚቻልባቸው በኦሮሞ ወቅያኖስ ውስጥ በሚገኙት ዝቋላንና ዝዋይን በመሳሰሉት ደሴቶች የሚኖሩት ጥንታዊ አልኦሮሞወች (ኦሮሞ ያልሆኑ ጦቢያውያን) ከየት መጡ? በሚል አንድ ጥያቄ ብቻ ቆሻሻ ቅርጫት መጣል ይቻል ነበር፡፡ 

የነ ሙሐመድ ሐሰን ውሸት በእንጭጩ ሳይጋለጥ ቀርቶ ይህን ያህል ገዝፎ፣ ይህን ያህል ሕዝብ ለማሳሳት በመብቃቱ ዋናወቹ ተወቃሾች የጦቢያ የታሪክ ምሁራን የሚባሉት ግለሰቦች ናቸው፡፡  እነዚህ ምሁራን በምእራባውያን ታሪክ በመራቀቅ በሰው ወርቅ ለመድመቅ ሲሞክሩ፣ እነ ሙሐመድ ሐሰን በሰፊው የጦቢያ የታሪክ መስክ ላይ ያለ ምንም ተቀናቃኝ እንደ ልባቸው ፏለሉበት፡፡  

ዋሾና ውሸቱ አይናቁም፡፡  ተጋጣሚው የቀረ ቡድን በፎርፌ ያሸንፋል፡፡  እነ ሙሐመድ ሐሰን ደግሞ የእስካሁን ግጥሚያወቻቸውን ሁሉንም ያሸነፉት በፎርፌ ነው፡፡  ካሁን በኋላ ግን ፎርፌው መቆም አለበት፡፡  መቆም ያለበት ደግሞ ጋጠወጦቹ የኦሮሞ ጎጠኞች ከፈሪነት በሚቆጥሩት፣ አህያ የበቅሎ አባት በሚባልበት ካህንኛ (politically correct) ዘይቤ ሳይሆን፣ አህያ አህያ በሚባልበት መዕምንኛ (politically incorrect) ዘይቤ ነው፡፡  ጥያቄው የህልውና ጥያቄ ስለሆነ፣ እንትን ብንል እንትና ይቀየማል የሚባልበት አይደለም፡፡  ሐቅ የሚያንቀው ጓጉሮ ይሙት፡፡  

እየየም ሲደላ ስለሆነ፣ በሞት ሽረት ትግል ላይ ትህትናና ጨዋነት ይቅሩና ሰብአዊነትና ዲሞክራሲም ቅንጦት ናቸው፡፡  ለዚህ ማስረጃ ደግሞ ሰብአዊነትና ዲሞክራሲ ከኔ ወዲያ ላሳር የሚለው ያሜሪቃ መንግሥት በሁለተኛው ያለም ጦርነት ወቅት የገዛ ራሱን ዜጎች (እንጥፍጣፊ የጃፓን ደም ስላላቸው ብቻ) ከወንጀለኛ ቆጥሮ ሕፃን፣ ሴት፣ ወጣት፣ አዛውንት ሳይል ንብረታቸውን ነጥቆ፣ የዜግነት መብታቸውን ገፍፎ ሰብጉረኖ (concentration camp) ውስጥ ማጎሩን መጥቀስ ብቻ ይበቃል፡፡ 

አጼ ምኒልክን ወራሪ የሚሉ፣ ወራሪው አጼ ምኒልክ ሳይሆኑ በሉባወች የሚመራው የገዳ አረመኔ ሠራዊት እንደሆነ በግልጽ ሊነገራቸው ይገባል፡፡  ፊንፊኔ ኬኛ ሲሉ የቆጡን አወርድ ብለው የብብታቸውን እንዳይጥሉ ማስጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡  ቆንጨራ ሲያነሱ ደግሞ አፈሙዝ ማዞር የግድ ነው፡፡  

አጼ ምኒልክ ያደረጉት ድርጊት ቢኖር በገዳ ሠራዊት ማንነቱን የተነጠቀውን ገርባ ወደ ቀድሞ ማንነቱ መመለስ ነበር፡፡  አጼ ምኒልክ የሚወቀሱ ከሆነ፣ ሊወቀሱ የሚገባቸው ምልሰቱን ምሉዕ ባለማድረጋቸው ብቻና ብቻ ነው፡፡  በግዴታ የተጫነ የተስፋፊ ቋንቋ ከተጫነበት ምድር ላይ ሙሉ በሙሉ የግድ መክሰም፣ በዚህ ቋንቋ የተሰየሙ ቦታወችና ስሞች ደግሞ ወደ ቀድሞ ስያሜወቻቸው ሙሉ በሙሉ የግድ መለወጥ ነበረባቸው፡፡  ኦነጋውያንን ፊንፊኔ ኬኛ፣ ከሚሴ የኛ እያሉ ለመበሻቀጥ የበቁት አጼ ምኒልክ ምልሰቱን ምሉዕ ባለማድረጋቸው ነው፡፡  የኦሮሞ ስም በግዴታ የተለጠፈበት ገርባ ደግሞ የቦረና ደም ያለበት እየመሰለው ከእውነተኞቹ ቦረኖች በላይ ጽንፈኛ የሆነው በዚሁ ባጼ ምኒልክ ስህተት ነው፡፡  ለማ መገርሳ፣ ሕዝቀኤል ጋቢሳ፣ ጸጋየ አራርሳ፣ በቀለ ገርባ፣ ዮሐንስ (ሌንጮ) ለታ፣ አንዳርጋቸው ጽጌ ቂጢሳ ቦረኔ ሳይሆኑ ቦረኔ ነን የሚሉ ያጼ ምኒልክ ስህተት ውጤቶች ናቸው፡፡ 

ለምሳሌ ያህል “ያማራ ሕዝብ ከየት ወደ የት?” በሚለው መጽሐፉ ያማራ ብሔርተኛ መስሎ የቀረበውና፣ “ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር” በሚለው መጽሐፉ ደግሞ ቀኝኋላ በመዞር የለየለት ፀራማራ ሁኖ የቀረበውን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቂጢሳን እንውሰድ፡፡  አባ ባሕርይ ዜናሁ ለጋላ (ምዕራፍ 12) ላይ እንደገለጹት ሸዋን ሙሉ በሙሉ አጥፍቶ ጎጃምን መውጋት የጀመረው ሮበሌ የሚባለው ወሮበላነቱ ወደር ያልነበረው ሰባተኛው ሉባ ነበር፡፡  ስለዚህም ያቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች ሸዌወች ከሆኑ የሮበሌ ገርባወች እንደነበሩ በሙሉ እርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡  ስለዚህም አጼ ምኒሊክ የሸዋ ገርባወችን በእውነተኛ ስሞቻቸው እንዲሰየሙ አስገድደዋቸው ቢሆን ኖሮ፣ ቂጢሳና ከዚያ በላይ ያሉት የሱ ያልሆኑ የቦረና ስሞች በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ባልተለጠፉበት ነበር፡፡  እሱም ደግሞ ቦረኔ ነኝ በማለት የጊዜውን የፖለቲካ ቁማር ለመጫወት ምክኒያት ባላገኘ ነበር፡፡  አጼ ምኒልክን ደግሞ አምርሮ ከመወቀስ ይልቅ ቢያንስ ቢያንስ እሱና አባቱ በራሳቸው ቋንቋ አንዳርጋቸውና ጽጌ ተብለው እንዲጥሩ ስላስቻሏቸው አብዝቶ ባመሰገናቸው ነበር፡፡            

ኦነጋውያን ክልላችን ነው በሚሉት ልቦለዳዊ ክልል ውስጥ የሚገኙትን ቦታወች ዱከም፣ ቢሸፍቱ፣ አዳማ፣ ውንጂ እያለ ሲጠሩ፣ ያማራ መሠረት በሆነው በምድረ አምሓራ (ወሎ) ውስጥ የሚገኙትን ቦታወች የጁ፣ ራያ፣ ቃሉ፣ ወረኢሉ፣ ወረባቦ እያሉ መጥራት ያማራን ሕዝብ ሆደሰፊነት፣ ትልቅነትና ጨዋነት ቢመሰክርም በሌላ አንጻር ግን እጅግ በጣም ያሳፍራል፡፡  ጨዋ መሆን የሚያስፈልገው ጨዋነትን ለሚያውቅ ብቻ ነው፡፡  ኦነጋውያን ደግሞ ጨዋነት አልተፈጠረባቸውም፡፡  ኦነጋዊው ዐብይ አህመድ የሚያበሻቅጠውን ደብረጽዮንን እያሽሞነሞነ፣ የሚያከብረውን አምባቸውን የረሸነው ጨዋነቱን ከፍራት ስለቆጠረው ብቻ ነበር፡፡  

ወደ ቅርብ ታሪክ ስንመለስ ደግሞ፣ ኦነግ ስለ ልቦለዳዊው አኖሌ ሲያላዝን በእውነተኛው አርባጉጉ ሊወነጀል ይገባል፡፡  የኦሮሞ ጽንፈኛ ምዕተ ዓመታት ወደ ኋላ ሂዶ ተስፋየ ገብረአብ እና በረከት ስምኦን የተባሉ አማራጠል እኩይ ቧልተኞች (evil comedians) የጻፉለትን ልቦለዳዊ ስቅጠት (fictional trajedy) ቀን ከሌት እያነበነበ፣ ለኻጩን እያዝረበረበ ሲነፋረቅ፣  ያማራ ሕዝብ ግን አሁን ትናንትና የተፈጸሙበትን በምስል የተደገፉ አረመኔያዊ ጭፍጨፋወች ከናካቴው መርሳቱ ይቅር የማይባል ኀጢያት ነው፡፡  ለልቦለዳዊው አኖሌ የቆመው ሐውልት ፈርሶ፣ በፍርስራሹ ላይ ፈጠጋርን (አሩሲን) መሉ በሙሉ ያጠፋት ያራተኛው ሉባ የቢፎሌ ሰለባ የሆኑት ያማራ ሰማዕታት ሐውልት መገንባት ይኖርበታል፡፡  

ለማጠቃለል ያህል የኦሮሞ ሕዝብ ገዳ የሚባል አፍሪቃ በቀል ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሰረተ ዲሞክራሲያዊነትን የተላበሰ ዲሞክራቲክ ሕዝብ ነው የሚባለው ትርክት ምንም መሠረት የሌለው የቱሪናፎች ባዶ ቱልቱላ ነው፡፡ በመጀመርያ ደረጃ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንጅ ዲሞክራሲያዊ ሕዝብ የለም፡፡  በሁለተኛ ደረጃ ገዳ ጭፍጨፋን ለማሳለጥ ሲባል ብቻ የተመሠረተ ጊዜያዊ የጨፍጫፊወች ዕድር እንጅ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት አይደለም።  እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ዓይንና ናጫ የነበሩት የኦሮሞ ፅንፈኞች፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰምና ሙጫ የሆኑት የዘመናችን ግራኝ የነበረው ወያኔ ክፉኛ ያዳከመላቸውን አማራን መጨፍጨፍ ስለጀመሩ ብቻ ነው።  

ግራኝ ሙሐመድ አማራውን እጅጉን በማዳከም ላስራ ስድስተኛው ክፍለዘመን የሉባ ጭፍጫፊወች በር እንደከፈተ፣ የደደቢቱ ወያኔ ደግሞ አማራውን እጅጉን በማዳከም ለዘመናችን የሌንጮ ጭፍጫፊወች በር ከፈተ፡፡  የጭፍጨፋ በር የተከፈተላቸው ነጭ አምላኪ የሆኑት የሌንጮ ጨፍጫፊወች ደግሞ ልክ እንደ ሉባ ጨፍጫፊወች ጭፍጨፋቸውን የሚያሳልጡበት የጨፍጫፊወች ዕድር መሠርቱና ዕድሩን ገዳ ከማለት ይልቅ የሮማን ፕሮቻዝካ (Roman Prochazka) ደቀመዝሙር የነበረው ሚሽነሪው ዮሐንስ ክራፍ (Johann Ludwik Krapf) ባወጣላቸው ትናንት መጤ፣ ዳህራዊ ስም ኦሮሙማ አሉት        

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic