>

‹‹ዳይኖሰርስ ከእነ ነፍሱ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ብትል ሰላም ከሌለ ማንም ሊጎበኝ አይመጣም››

‹‹ዳይኖሰርስ ከእነ ነፍሱ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ብትል ሰላም ከሌለ ማንም ሊጎበኝ አይመጣም››

በኢትዮጵያ የጦርነት ኢኮኖሚ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በአመት ኪሳራ ተመዝግቦል!!!

  (ክፍል አንድ)        

 ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

የተባበሩት መንግሥታት (United Nations Human Rights Council)፡- የተባበሩት መንግሥታት በአማራ ክልል ወንጀሎችና ስብዓዊ ቀውስ መጨመር በሰው ዓልባ አውሮፕላን (ድሮውን)ና በነፃ እርምጃ ንፁሃን ዜጎች መጨፍጨፍ በተመለከተ ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን እንዲቆቆምና በፊት የነበረው ኮሚሽን ደግም እንዲሰራ ወንጀለኞቹ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተወስኖል፡፡ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ በየሃገሩ ገለልተኛው አጣሪ ኮሚሽን ሥራውን በአስቸይ እንዲጀምር ድጋፋችሁን ማሰማት ይጠበቅባችኃል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት በአማራ ክልል እየተፈፀመ ያለውን የዘር ጭፍጨፍ (ጀኖሳይድ) በድሮውን ጥቃት 70 ንጹሃን ዜጎች በፍኖተሰላም መፈፀሙን፣ በደብረ ብርሃን ከተማ በከባድ መሣሪያ ንፁሃን ዜጎች መገደልና በተሸሸጉበት ስፍራ ሆስፒታል፣ ቤተክርስቲያነ ፣ ትምህርት ቤት ውስጥ በግፍ መገደል፣ ባህር ዳር ከተማን በተወንጫፊ ከባድ መሳሪያ መደብደብየተነሳ በመቶ የሚቆጠሩ ንጡሃን አማራዎች ተገድለዋል፣በጎንደር የተነሳ ጦርነት ከሃያ ንፁሃን አማራዎች ተገለዋል፣ሁለት መቶ ቆስለዋል፣ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ንጡሃን ዜጎች መታገትና በኃይል መሠወር በተባበሩት መንግሥታት የአማራ ጀኖሳይድ ሪፖርት  ላይ በሰፊው ተገልፆል፡፡ ሙሉውን ከድረገፁ ያንብቡት፡፡ The international community’s swift and resolute action is crucial to addressing the deteriorating Amhara genocide in Amhara Region of Ethiopia: The atrocities being committed against the Amhara people in the Amhara region of Ethiopia are deeply concerning and require immediate attention. The following incidents provide a glimpse into the severity of the ongoing crisis:…(1) 

የኮነሬል አብይ አህመድ  የኦህዴድ ብልፅግና አንባገነን መንግሥት በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያን በጦርነት ኢኮኖሚ ውስጥ ዘፍቆ ሃያ ስምንት ቢሊዮን ዶላር የመሰረተልማት ውድመት ያስከተለና አንድ ሚሊዮን ወጣቶችን ጭዳ ያደረገ ፋሽስታዊ መንግስት በአስቸኮይ ከሥልጣን ካልተወገደ በጦርነት የሰው እልቂትና ርሃብ እጣ ፈንታችን ሆኖ ይቀጥላል:: ኢትዮጵያ የጦርነት ኢኮኖሚ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በአመት ኪሳራ ተመዝግቦል! እንደ ቶፕ ቴን ቪፒኤን መሠረት በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት መዘጋት የተነሳ ሀገሪቱ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ደርሶባታል፡፡

በኢትዮጵያ የጦርነት ኢኮኖሚ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በአመት ኪሳራ ተመዝግቦል፡፡ በሪፖርቱ መሠረት የኮቪድ 19 እና የትግራይ ጦርነት በጣምራ የኢትዮጵያን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ  የሁለት ቢሊዮን ዶላር ገቢ በአመት ኪሳራ በአለፈው ሁለት አመታት አስከትሎል፡፡ በቀጣይነት በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ጦርነት እና የአስቸይ ጊዜ አዋጂ የተነሳ ብዙ አገሮች ለዜጎቻቸው የጉዞ ማስጠንቀቂያ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይሄዱ በማሳሰባቸው የቱሪስቶች ቁጥር ሲቀንስ የሃገሪቱን ዓለም አቀፍ የቱሪስት መስህብነትና ዝና የነበራትን ስምና ክብር  ሊጠለሽ ችሎል፡፡ Reports estimate that combined, the COVID-19 pandemic and violence in Tigray cost Ethiopia’s tourism industry two billion dollars yearly over the last two years in lost revenue. Following the conflict in the Amhara region and announcement of a state of emergency, several countries issued stern travel warnings advising their citizens not to visit areas affected by violence or unrest. This decline in visitors has damaged Ethiopia’s reputation as a stable tourist destination worldwide, according to Henok…(2) 

በአገልግሎት ዘርፍ ውስጥ የሚካተተው  የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍል ሲሆን ወደ አገር ቤት የገቡ የቱሪስቶች ቁጥር (Number of tourists) ዘርፉ በውጪ ምንዛሬ ያስገኘ ገቢ (Receipts) እንዲሁም  ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) (% of GNP) በመቶኛ  ሲሰላ ያለውን 2017 እስከ 2021እኤአ የቁልቁለት ጉዞን በማስረጃ እንቃኛለን፡፡

  • በ2017እኤአ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ 933,000 (ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ሦስት ሽህ) ቱሪስቶችን  በማስተናገድ  ከፍተኛው ክብረ ወሰን ነበር፣ 2.51 (ሁለት ቢሊዮን ነጥብ ሃምሳ አንድ) ዶላር የውጪ ምንዛሬ ያስገኘ ሲሆን ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) 3.1 % (ሦስት ነጥብ አንድ)በመቶ ሸፍኖ ነበር፡፡
  • በ2018እኤአ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ 849,000 (ስምንት መቶ አርባ ዘጠኝ ሽህ) ቱሪስቶችን  በማስተናገድ፣ 3.55 (ሦስት ቢሊዮን ነጥብ ሃምሳ አምስት) ዶላር የውጪ ምንዛሬ ያስገኘ ሲሆን ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት 4.2 % (አራት ነጥብ ሁለት) በመቶ ሸፍኖ ነበር፡፡
  • በ2019እኤአ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ 812,000 (ስምንት መቶ አስራሁለት ሽህ) ቱሪስቶችን  በማስተናገድ፣ 3.53 (ሦስት ቢሊዮን ነጥብ ሃምሳ ሦስት) ዶላር የውጪ ምንዛሬ ያስገኘ ሲሆን ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት 3.7 % (ሦስት ነጥብ ሰባት) በመቶ ሸፍኖ ነበር፡፡ Ethiopia tourism statistics for 2019 was 3,529,000,000.00, a 0.54% decline from 2018.
  • በ2020እኤአ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ 518,000 (አምስት መቶ አስራስምንት ሽህ) ቱሪስቶችን  በማስተናገድ፣ 2.28 (ሁለት ቢሊዮን ነጥብ ሃያ  ስምንት) ዶላር የውጪ ምንዛሬ ያስገኘ ሲሆን ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት 2.1 % (ሁለት ነጥብ አንድ) በመቶ ሸፍኖ ነበር፡፡ Ethiopia tourism statistics for 2020 was 2,282,000,000.00, a 35.34% decline from 2019.በ2021እኤአ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ 518,000  (አምስት መቶ አስራስምንት ሽህ) ቱሪስቶችን  በማስተናገድ፣ 2.60 (ሁለት ቢሊዮን ነጥብ ስድስት) ዶላር የውጪ ምንዛሬ ያስገኘ ሲሆን ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት 2.3 % (ሁለት ነጥብ ሦስት) በመቶ ሸፍኖ ነበር፡፡
  • በ2022 እና 2023እኤአ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የቱሪስቶች ቁጥር በጣም በመቀነሱ የተነሳ መረጃውን መንግሥት ደብቆል፡፡ በሆቴልና ቱሪዝም የተገኘው የውጪ ምንዛሬ አልተገለፀም  ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት በመቶ የሸፈነው አልተሰላም፡፡
  • በ2024 እኤአ በኢትዮጵያ የሆቴል ገበያ ገቢ 1.14 (አንድ ቢሊዮን ነጥብ አስራ አራት) ዶላር እንደሚገመትና ከ2024 እስከ 2028 እኤአ  እድገቱ 6.01 በመቶ እንደሚሆን ተተንብዬል፡፡ By 2024, the Hotels market in Ethiopia is projected to reach a revenue of US$1.14bn, with an expected annual growth rate (CAGR 2024-2028) of 6.01%. This growth is expected to result in a projected market volume of US$1.44bn by 2028.

ዝነኛው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ-መጠይቅ ‹‹አትሌት ኃይሌይህ በጣም ከባድ ነው፡፡ እንደምትሰማው እንዲያውም በአሁኑ ሰዓት ሆቴሎች እየተዘጉ ነው፡፡ ይህ ማለት ቱሪስት ወይም ተጠቃሚ እየጠፋ ነው ማለት ነው፡፡ ተጠቃሚው በአንድ በኩል በቱሪስትነት ነው የሚመጣው ወይም ደግሞ በስብሰባ ነው የሚመጣው፡፡ የፈለገውን ያህል በወርቅ ለብጠን ሆቴል ወይም ሪዞርት ብንሠራ ሰላም ከሌለ ማንም መጥቶ አይጠቀምም፡፡ ሌላው ይቅርና ኢትዮጵያ ውስጥ ዳይኖሰርስ አለ ብትል እንኳ ሰላም ከሌለ ማንም መጥቶ መጎብኘት አይፈልግም፡፡ የዛሬ ስንት ሚሊዮን ዓመት የጠፋው እንስሳ ዳይኖሰርስ ከእነ ነፍሱ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ብትል ሰላም ከሌለ ማንም አይመጣም፡፡ አንድ ቱሪስት መጀመሪያ የሚያስቀምጠው መጀመሪያ ለመቀመጫዬ እንዳለችው እንስሳ ሕይወቱን ነው፣ ይህንን መገንዘብ አለብን፡፡ እንደ ሕዝብም፣ እንደ መንግሥትም ይህንን ካላደረግንና ሰላምን ካላረጋገጥን እንኳን ቱሪስት ለማምጣት ቀርቶ አንተም እኔም ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀስም አንችልም፡፡››…………………………………………….(3) 

የኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት መቶ አስራአንድ ቢሊዮን ዶላር 2021እኤአ እንደነበር የዓለም ባንክ አስታውቆ ነበር፡፡ (Gross domestic product111.3 billion USD (2021) World Bank)

  1. ግብርና ዘርፍ (Agriculture):- የኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) በየዘርፉ ግብርና ዘርፍ (Agriculture: 35.5%) ሠላሳ አምስት ነጥብ አምስት በመቶ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ይሸፍናል፡፡ የግብርናው ዘርፍ የሰው ኃይል አቅርቦቱ (agriculture: 72.7%) ሰባሁለት ነጥብ ሰባት በመቶ የሰው ኃይል ይሸፍናል፡፡
  2. የኢንዱስትሪ ዘርፍ (Industry):-የኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) በየዘርፉ የኢንዱስትሪ ዘርፍ (Industry: 23.11%) ሃያ ሦስት ነጥብ አስራአንድ በመቶ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ይሸፍናል፡፡ የኢንዱስትሪ ዘርፍ የሰው ኃይል አቅርቦቱ (industry: 7.4% ) ሰባት ነጥብአራት በመቶ የሰው ኃይል ይሸፍናል፡፡
  3. የአገልግሎት ዘርፍ (Services):- የኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) በየዘርፉ የአገልግሎት ዘርፍ (Services: 36.81%) ሠላሳ ስድስት ነጥብ ሰማንያ አንድ በመቶ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ይሸፍናል፡፡ የአገልግሎት ዘርፍ የሰው ኃይል አቅርቦቱ (services: 19.9%) አስራ ዘጠኝ  ነጥብ ዘጠኝ በመቶ የሰው ኃይል ይሸፍናል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊሪፓብሊክ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀፅ 42 ‹‹የመዘዋወር ነፃነት›› መሠረት አንደኛ/ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይም በሕጋዊ መንገድሀገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ በመረጠው የሀገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቦታ የመመስረት እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከሀገር የመውጣት ነጻነት አለው፡፡ ሁለተኛ/  ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወደ ሀገሩ የመመለስ መብት አለው፡፡››

ኮነሬል አብይ አህመድ የብልጽግና ሹማምንት የሆኑትን ፓስፖርት በማገት ያለእሳቸው ፍቃድ ማንም ባለስልጣን ከአገር መውጣት እንደማይችል በማሳወቅ የጠቅላይ ሚንስርነትና የኢሚግሬሽን ኃላፊነቱንም ጠቅልለዋል፡፡ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ስዩም መስፍን፣ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ወዘተ ከአገር ኮብልለዋል፡፡

‹‹ከሰሞኑ ዓይተናል ሁላችንም ከአዲስ አበባ ለመውጣት እንኳ እየተሳቀቅን ነው፡፡ እኔ ለምሳሌ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው እዚህ ሶዶ በአውሮፕላን የመጣሁት፡፡ በአውሮፕላን መጥቼ አላውቅም፡፡ መኪናዬን እየነዳሁ ከሶዶ አልፌ አርባ ምንጭ ደርሼ ሥራዬን ሠርቼ እመለሳለሁ፡፡ ሰሞኑን ግን ያሠጋል፡፡ በመኪና መሄድ አትችልም አሉኝ፡፡ እንዴት የማውቀውን መንገድ ትከለክሉኛላችሁ ብልም በፍፁም አይሆንም አሉኝ፡፡ ሐዋሳ በአውሮፕላን ለመሄድ ? ኧረ ባካችሁ ግፍ ነው ነበር ያልኩት፡፡ እንዲህ ባለው አስገዳጅ ሁኔታ ግን በመኪና መሄድ የሚቻሉ ቦታዎችን በአውሮፕላን ለመሄድ ትገደዳለህ፡፡ ይህ ሁኔታ ቱሪስቱን ብቻም ሳይሆን፣ የብዙ ሺሕ ሠራተኛ ኃላፊነት ያለበት እንደ እኔ ያለውን ሰው እንቅስቃሴም ይገድባል። ይህንን ቆም ብለን ሁላችንም ልናስብበት ይገባል፡፡››

(1) የመለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊሪፓብሊክ ሕገመንግሥት፣አንቀፅ 49 መሰረት ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ይጠበቅላታል ባለው መሠረት የአማራ፣ የትግራይ፣ የዶርዜ ሰዎች አዲስ አበባ እንዳይገቡ በማድረግ ልዩ ጥቅምማቸውን ተግባራዊ አድርገዋል፡፡ ህወሓት ለትግራየ ህዝብ በፕሪቶሪያ ስምምነት ያስገኘው ጥቅም ቢኖር ተጋሩ አዲስ አበባ እንዳይገባ ማድረግ ነው፡፡ 

(2) የአማራ ህዝብ ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ከተማ መግባት ተከልክለዋል፡፡ ተላላኪዎቹ ብአዴኖች ከባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ደብረብርሃን ከተሞች መግባትም መውጣትም አልቻሉም፡፡ ብአዴን ብልፅግና አባላት ወደ ውጪ አገራት መሄድ አይችሉም፣ፓስፖርታቸው ኮነሬል አብይ እጅ ነው፡፡

(3) ህወሓት ኢህአዴግ ከትግራይ ክልል ወደ ሌሎች ክልሎች መንቀሳቀስ አይችሉም፡፡ ህወሓት ኢህአዴግ አባሎች ወደ ውጪ ሀገራትም መጎዝን መንቀሳቀስ አይችሉም፡፡ ተጋሩ ከትግራይ ክልል ወደ ሌሎች ክልሎች መሄድና መምጣት አልቻሉም፡፡ ህወሓት ለታላቁ የትግራየ ህዝብ ያጎናፀፈው መብትና ነጻነት በኦህዴድ ብልጽግና ባርነት ስር ወድቆል፡፡

(4) ዶርዜዎች ከአዲስ አበባ ንዋሪ ነበሩ አስር ሽህ ዶርዜዎች ወደ አርባ ምንጭ በግፍ ተሸኝተዋል፡፡

(5) የኦነግ ሸኔ እገታና ኦህዴድ ብልፅግና የአማራ ዜጎች ላይ ያነጣተረ እገታና የቻይና የህንድ ዜጎች እገታ 

ቱሪስትና የኢንተርኔት ዓለም፡- የኮነሬል አብይ አህመድ  የኦህዴድ ብልፅግና አንባገነን መንግሥት በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ኢንተርኔት የሚከረችም መንግሥት ነው፡፡ ቱሪስቶች ኢንተርኔት አገልግሎት በሌለበት ሀገር ምን ሊሰሩ ይመጣሉ? እንን ቱሪስቶች ሀገር በቀሉ ዲያስፖራ አገር ቤት መምጣት ከአቆመና በሃዋላ የሚልከውን የዶለር ፍሰቱን በማቆም የኮነሬል አብይን መንግሥት በመፋለም ላይ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከአፍሪካ አህጉር ዝቅተኛ ሲሆን ከጠቅላላው ሕዝብ ቁጥር 16.7 (አስራ ስድስት ነጥብ ሰባት) በመቶ በ2021እኤአ እንደነበር የዓለም ባንክ አስታውቆ ነበር፡፡ (Internet users16.7% of the population (2021) World Bank

  • Jan 9, 2024 — እንደ ቶፕ ቴን ቪፒኤን መሠረት በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት መዘጋት የተነሳ ሀገሪቱ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ደርሶባታል፡፡ According to a report by Top10VPN, Ethiopia experienced the second largest economic losses globally as a result of government-mandated internet ..( News: Internet shutdown costs Ethiopia nearly $2 billion in …/Addis Standard/https://addisstandard.com › Business)

  • Jan 12, 2023 —  ኢትዮጵያ በ2020 እኤአ በኢንተርኔት የምታገኘው ገቢ በመቶ ሚሊዮኝ ዶላር ኪሳራ ሲደርስበት  በ2021እኤአ ደግሞ መቶ ስልሳአራት ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ደርሶባታል፡፡A new report by Top10VPN … In 2020, the country lost $100 million to internet outage which rose to $164.5 million in 2021, affecting 21.3 …( Ethiopia lost $146 million due to internet blackouts in 2022//Quartz | Make business better.™️/https://qz.com › ethiopia-lost-146-million-due-to-internet…)
  • Jan 16, 2023 — በኢትዮጵያና ትግራይ የሁለት አመት ጦርነት የኢንተርኔት መዘጋት የተነሳ አራት መቶ አስር ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ  ደርሶባታል፡፡ A war in the Tigray region of Ethiopia has caused a two-year-long internet shutdown, costing the country an estimated $410 million. (Ethiopia has lost $410 million to a war-induced internet … /Ventures Africa/https://venturesafrica.com › ethiopia-has-lost-410-million…)

ምንጭ

  1. (1)Urgent Call to Address Escalating Human Rights Violations and Crisis in Amhara, Ethiopia (https://documents.un.org/doc/undoc/gen/g24/025/69/pdf/g2402569.pdf?)
  2. Tourism faces existential crisis/ByAbraham Tekle/August 19, 2023
  3. ‹‹ዳይኖሰርስ ከእነ ነፍሱ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ብትል ሰላም ከሌለ ማንም ሊጎበኝ አይመጣም›› አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ/ ሪፖርተር ጋዜጣ ዮናስ አማረ/February 11, 2024

  

Filed in: Amharic