>
5:16 pm - Saturday May 24, 7175

ትዊተር/ስፔስ ላይ ያሉ የአማራ ትግል ውስጥ ሰርገው የገቡ የDOUBLE AGENTS መለያዎች:- 

ትዊተር / ስፔስ ላይ ያሉ የአማራ ትግል ውስጥ ሰርገው የገቡ የ DOUBLE AGENTS መለያዎች :- 

 1)  ከኛ በላይ ብሔርተኛና ለአማራ ተቆርቋሪ የለም ባዮች።
 2)  ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚሉ ሰዎችን ልክ የአማራ ቀንደኛ ጠላት አድርጎ መሳል።
 3)  የአማራን ትኩረት መበታተን።
 4)  በተቆርቋሪነት ሽፋን የልዩነት አጀንዳ ማምጣትና ማጮህ ።
 5)  ራሳቸውን የፋኖ ጠባቂ ና ተቆርቋሪ በማድረግ አንዱን የፋኖ ክፍል በሌላው ለማጥቃት ፕሮፖጋንዳ መንዛት።
 6) አንዳንዶቹ ደሞ ለዘብተኛ መስለው አንተም ተው አንቺም ተይ በሚመስል ሰበብ እነሱ የሚቃወሙት ፍኖ ሲቀጠቀጥ በዝምታ ማየት ና የሚደግፉት ሲነካ. ገላጋይ መስለው መምጣት::
 7) እነሱ በውጭው ብአዴን የተሳሰሯቸው የአማራ ድርጅት ተብዮዎች ጥፋት እንዳይነገር መከላከል ሀሳብን divert ማስደረግ ና ሁላችንም እንደ ዲያስፖራ ጥፋተኞች ነን የሚል ማለባበሻ መንዛት ና ዋናው አጥፊ እንዳይታወቅ ማድረግ።
8) ብአዴንን በአፋቸው ና ፅሁፋቸው እየረገሙ ከዕውነተኛ የአማራ ታጋዮች ጋ ራሳቸውን አመሳስለው በመሰለል በገሃዱ አለም ግን ብአዴኖች እንዳይነኩ መረጃ ማቀበል ና መከላከል::
 9) የእኩዮች ስራ የሚገለጥ ሲመስላቸው መካሪ መስለው መምጣትና እንዴት እየተጨፈጨፍን ይህን ተራ ወሬ እናወራለን በማለት በማሸማቀቅ ዕውነታው ታፍኖ እንዲቀር ማድርግ ባንፃሩ በነሱ መንገድ የሚሄድ አጀንዳ ከሆነ ግን ለምን ስለሚጨፈጨፈው ሕዝብን አንጮህም አይሉም!
10) በጣም ሾካካ ልምጥምጥ ና ለስላሳ ሆነው ስማችሁን እያቆላመጡ ድምፃቸውን አስረቅርቀው ይቀርቧችኋል! በተለይ የአማራ ትግል ላይ significant contribution ያደርጋሉ የሚባሉትን ጓዳኝነት መስርተው እነዛ ሰዎች የነሱን አጀንዳ እንዲያራግቡ ወይም ወሳኝ ነገሮች ሲኖሩ በዝምታ እንዲያልፉት በመቀራረብ በጓደኝነትና በመተዋወቅ ሰበብ ያዘናጋሉ!

 ♦ ንቁ ታጠቁ !…አይናችሁን ክፈቱ!…ትግሉ ከመቼውም በላይ በሴረኞች እጅ የመውደቅ አደጋ ውስጥ ነው! የአማራ ትግል የህልውና እንጂ የ ፖለቲካ አይደለም!

እርጎዬ (Ethiopiawit)
@ethio_forever

#AmharaResistance

Filed in: Amharic