>

በአዲስ አበባ መሬት ጮህች!...የኦህዴድ የቌንቌ፣ የብሔርና የዘር መሬት ዛር!

በአዲስ አበባ መሬት ጮህች!… በኦሮሚያ መሬት ጮህች!

የኦህዴድ የቌንቌ፣የብሔርና የዘር መሬት ዛር!

(ክፍል አንድ)

ሚሊዮን ዘአማኑኤል

(ኢትኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መሬት ጮህች!! የኦህዴድ የቌንቌ፣ የብሔርና የዘር መሬት ዛር!! በአዲስ አበባ መሬት ጮህች!!! መሬት ጮህች!!! እሪ አለች!!! ሰው ዝም ሲል ምን ታድርግ!!!

የኮነሬል አብይ አህመድ፣ ሽመልስ አብዲሳና አዳነች አቤቤ በቢሊዮኖች ብር የምትታለብ ላም፣ የአዲስ አበባ ከተማና የሸገር ከተማ መሬት ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ዋጋ ከ480 ሽህ እስከ 600 ሽህ በሜትር ካሬ በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡የኦሮሞ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ ከተማና በሸገር ከተማ ውስጥ የሚገነባቸው  የተለያዩ ፕሮጀክቶች የንዋሪዎቹን የግል የመሬት ይዞታ ካርታ በመንጠቅ በተለይ የአማራና የሌሎች ብሔሮችን  መሬቶችን  በመውሰድ  ንዋሪውን በማፈናቀል መሬት በመሸጥ የተገኘ ኃብት ትሪሊዮን ብር ይገመታል፡፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዤዳንት ሽመልስ አብዲሳ ‹‹ በኦሮሚያ ነፍጠኛ ይዞት የነበረውን 182,000 (መቶ ሰማንያ ሁለት ሽህ) ሽህ ነፍጠኛ የአማራ ተወላጆች ከኦሮሚያ ክልል ተባረዋል መሬታቸውም ለኦሮሞ ወጣቶች ተከፋፍሎል፡፡ ነፍጠኛ ይዞት የነበረውን ቤቶች በአዲስ አበባ ብሸፍቱ፣ ሞጆ፣አዳማ፣ ሻሸመኔ ከተሞች 213,000 (ሁለት መቶ አስራሦስት ሽህ)  ህገወጥ ቤቶች እንዲፈርሱ ተደርገዋል፡፡›› ብለዋል፡፡ በማንነት ተኮር ላይ የተመሠረተ የቤቶች ፈረሳ በአዲስ አበባ በብሸፍቱ፣ ሞጆ፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ ከተሞች ተጠናክሮ ቀጥሎል፡፡ መሬት ጮህች፣ በክረምቱ ወራት የአማራ ተወላጆች ቤቶች በግፍ በመፍረስ ላይ ይገኛሉ፡፡ በኦሮሚያ በወለጋ መሬት ጮህች የታረዱ ሽማግሌ፣ አሮጊቶችና ህፃናቶች ጩህት ከአጥናፍ አጥናፍ ያስተጋባል!!! የፍርድ ያለህ ይላል፡፡ በቤኒ-ሻንጉል ክልላዊ መንግሥት ፍርድ ቤት በአማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሰው ከሃያ እስከ ሃያ ሁለት አመት ቅጣት የተፈረደባቸው 86 ወንጀለኞች ከእስር ተፈተዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል መቶ ዬነኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኦሮሚያ ክልል ውስጥ መታፈናቸው ታውቆል፡፡ የአማራ ፋኖ ከክልሉ አድማስ ወጥቶ ይሄን ማስቆም አለበት  እንላለን፡፡

  • በአዲስ አበባ ደሃ ንዋሪዎች መኖሪያ የሆኑ የፈረሱ ቤቶች በጨረታ 99,000,000,000 (ዘጠና ዘጠኝ ቢሊዮን ብር)እንደሚሸጥ የኮነሬል አብይ መንግሥት አስታውቆል፡፡
  • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ አምስት የኮሪደር ልማት ግንባታ 33,000,000,000 (ሠላሳ ሦስት ሚሊዮን ብር) ወጪ እንደወጣ ገልጸዋል፡፡ በስምንት ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባውን አዲሱን ትልቅ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፎቅ ዓይነት አራት የሚያሠራ ወጪ ሲሆን የህዝብ ገንዘብ በግንባታ ስም እየተዘረፈ እንደሆነ ይታመናል፡፡ 
  • በ2016ዓ/ም በጀት አመት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በጀት 75000000000 (ሰባአምስት ቢሊዩን ብር) የተከናወኑ በሽዎች የሚቆጠሩ ፕሮጀክቶች ይመረቃሉ:: በአማራ ክልልስ? ኮነሬል አብይ ትግራይን በሻሻ አደረግናት እንዳለው፣ አማራ በሻሻ ሳያደርጋት በፍጥነት ከሥልጣን መንበሩ መከላት አለበት እንላለን፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኢኮኖሚ ዳሰሳ

{I} የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ Ethiopian Airlines፡- የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ እቅድ መሰረት ከአዲስ አበባ 39 ኪሎ ሜትር እርቀት  በምትገኘው ብሸፍቱ ከተማ ላይ በ35 ስኩየር ኪሎሜትር ቦታ ላይ የአይሮፕላን ማረፍያ በ5000000000 (አምስት ቢሊዮን ዶላር) እንደሚያስገነባ ተገልፆል፡፡ ‹‹Ethiopian Airlines has announced that it will start constructing a new $5 billion airport later this year, its as the rapidly-expanding carrier outgrows capacity at its current base in Addis Ababa. The airport, which will cover an area of 35 square km, will be built in Bishoftu, a town 39 km south east of the capital, and have the capacity to handle 100 million passengers a year.››

{II} ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን Geda Special Economic Zone (GSEZ)በኦሮሚያ ክልል በሞጆና በአዳማ ከተሞች መካከል የተቋቋመው ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን 24 ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ በአራት ምዕራፎች እንደሚለማ፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ 3,114 ሔክታር የሚሆን መሬት ላይ ልማት ለመጀመር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን የዞኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሞቱማ ተመስገን ገልጸዋል፡፡ ‹‹The Geda economic zone lies on 23,656hct of undeveloped land, of which close to 300hct is sourced from the local farmers with a 3.4 million Br compensation fee for a hectare. The 3,114hct is set to be developed in the next five years while 8,000hct is under construction.›› 

ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የአርባ ዓመት ፕሮጀክት ሲሆን አሁን ሦስት መቶ ሠራተኞች ሲኖሩት ወደፊት ለሰባ ሚሊዮን ሠራተኞች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡“It’s a project for the coming 40 years,” said Motuma. The GSEZ will have a free market zone, logistics centre, housing, and industrial flocks, mainly focusing on exporting quality product-producing local and international companies. Over 300 people are currently working in the economic zone, with the prospect of employing 70 million people when it is fully operational, according to the CEO.” ጉድ እኮ ነው የማህይም ነገር  የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የአርባ ዓመት ፕሮጀክት ሲሆን ወደፊት ለሰባ ሚሊዮን ሠራተኞች የሥራ ዕድል ይከፈታል ይሉናል፡፡ ሽመልስ አብዲሳም በሸገር ከተማ ሠላሳ ሚሊዮን የከተማ ንዋሪዎች ይኖራታል ብሎል፡፡

ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን፡- የአዲስ አበባን የመሬት ስፋት ግማሽ የሚያክል ሲሆን የአዳማ ከተማን ስድስት እጥፍ የመሬት ስፋት ያለው ሲሆን ለግንባታ 46,000,000,000 (አርባ ስድስት) ቢሊዮን ብር በጀት የተያዘለት ትልቅ ፕሮጀክት ዋና አላማው ሞጆን ከተማን፣ አዳማንና ሻሸመኔ ከተማዎቹን የሚያገናኝ ፕሮጀክት ነው፡፡‹‹ Special Economic Zone that is half the size of Addis Abeba and six folds Adama town is under construction with over 46 billion Br budget. Oromia Regional State commenced Geda Special Economic Zone (GSEZ) located 65Km east of the capital with the aims of connecting it with Mojo, Adama, and Shashemane towns.››

ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን፡- የሎጂስቲክ፣ የሪል ስቴት፣ የነፃ ንግድ ቀጣና፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያን ጨምሮ የአይሲቲ ፓርክ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አክለውም ለልማት ከተዘጋጀው ውስጥ አምስት ሺሕ ሔክታር የሚሆነው መሬት ለኢንዱስትሪ፣ አምስት ሺሕ ሔክታር ደግሞ ለሪል ስቴት ልማት እንደሚውል ጠቁመዋል፡፡ በአዋጁ ነባር የኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ልዩ ዞን ከማሸጋገር በተጨማሪም፣ በሚቋቋሙት ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የውጭ አገር የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት ማቅረብ እንደሚችሉ የተደነገገ ሲሆን ተቋማቱ የሚመረጡበት መሥፈርት፣ ደረጃና የአሠራርና የፈቃድ አሰጣጥ ሁኔታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣው መመርያ እንደሚወሰን ተመላክቷል፡፡ ብሔራዊ ባንክ የኢኮኖሚ ዞኑን ሳቢነት፣ ተወዳዳሪነትና ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ራሱን የቻለ የፋይናንስና የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሪፎርም እንደሚያካሂድና የአሠራር ሥርዓት እንደሚዘረጋ ተቀምጧል፡፡ በተጨማሪም የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አልሚዎች የሚያገኟቸው ማበረታቻዎች በአዋጁ የተካተቱ ሲሆን፣ ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የሚገቡና ከዞኑ የሚወጡ ዕቃዎች ከቀረጥና ከግብር ክፍያ ነፃ እንዲሆኑ የሚለው ይገኝበታል፡፡ በተመሳሳይ ወደ ዞኑ የሚገቡ የግንባታ ዕቃዎች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ እንዳይከፈልባቸው፣ እንዲሁም የካፒታል ዕቃዎች ከማንኛውም ቀረጥና ታክስ ነፃ የመሆን መብት በአዋጁ ሠፍሯል፡፡

{III} አዲስ አበባ ከተማና የሸገር ከተማ የመሬት ሽያጭ ፕሮጀክት፣

የኮነሬል አብይና ሽመልስ አብዲሳና አዳነች አቤቤ በቢሊዮኖች ብር የምትታለብ ላም፣ ሸገር ከተማ መሬት ሽያጭ ፕሮጀክት፡- የሸገር ከተማ ኩታ ገጠም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ህዝብን ሳያማክር በኦክቶበር 2022 እኤአ የሸገር ከተማ መሠረተ አዲስ የከተማ ማዕከል ስትሆን የአዲስ አበባን ዙሪያ ገባ ተከትላ የተዋቀረች ከተማ ናት፡፡ የሸገር ከተማ ኩታ ገጠም መሬት 1600 (አንድ ሽህ ስድስት መቶ) ስኩየር ኪሎሜትር  ስፍት አላት፡፡ የሸገር ከተማ በስድስት ክፍለ ከተሞች የተመሠረተች ስትሆን እነሱም ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ለገጣፎ፣ለገዳዲ፣ ሱሉልታ፣ ገላን፣ እና መናገሻ ያካትታሉ፡፡ የሸገር ከተማ አዲስ አበባን ዙሪያዎን ከበዋታል፡፡  የአማራ ፋኖ ዕዝ በአስቸአዲስ አበባና የሸገር ከተማ የመሬት ሽያጭ የትሪሊዮን ብር ፕሮጀክት ያስቆመ ጊዜ ብቻ ኮነሬል አብይ አህመድ ከስልጣኑ ይወድቃል፣ አብይ አይ ኤም ኤፍ እንዳለው ‹የኢትዮጵያ  ጂዲፒ 205 ቢሊዮን ዶላር አደገ፣ የኢኮኖሚ እድገታችን 6.5 በመቶ አደገ› እያለ የሚዝናናው ከመሬት ሽያጭ ከሚያገኘው ሃብት መሆኑ ስንቶቻችን እናውቃለን፡፡ አገራችን በጦርነት ኢኮኖሚ ወድማለች፣ የውጭ ንግድ ገቢ መንምኖል፣ የውጭ ብድር ጫና አዘቅት ውስጥ ከቶናል፣ የዋጋ ግሽበት የኑሮ ውድነቱን አባብሶታል፣ መሠረተ-ልማቶች ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ የመብራት የቴሌኮሙኒኬሽን ወዘተ አገልግሎቶች ወድመዉ ኢኮኖሚ አደገ ይሉናል፡፡       

የኮነሬል አብይና ሽመልስ አብዲሳና አዳነች አቤቤ በቢሊዮኖች ብር የምትታለብ ላም፣የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ሽያጭ ፕሮጀክት፣ ደሃ ንዋሪዎች መኖሪያ የሆኑ የፈረሱ ቤቶች በጨረታ 99,000,000,000 (ዘጠና ዘጠኝ ቢሊዮን ብር)እንደሚሸጥ የኮነሬል አብይ መንግሥት አስታውቆል፡፡ የኦህዴድ ኦሮሙማ መንግሥት የሸገር ከተማን መሬት በመሸጥ አማራውን ከክለሉ በመንቀል መንግሥት መር የሥነ-ህዝብ ለውጥ (ዴሞግራፊክ ለውጥ) በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ ይህን ድርጊት አሁኑኑ በተግባር ማስቆም ካልተቻለ፣ የኮነሬል አብይ መንግሥት ፕሮጀክቶችን እየተከታተሉ እንዳይሰሩ ማድረግ ካልተቻለ፣ የወደቀው መንግሥት አገግሞ መንቀል ያቅታል እንላለን፡፡   

የኮነሬል አብይ የኦሮሙማ የእጅ አዙር አገዛዝ፣  የአዲስ አበባ ከተማ ላይ ተቆርሷ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት  የተሠጠ የሸገር ከተማ 1600 (አንድ ሽህ ስድስት መቶ) ስኩየር ኪሎሜትር ቦታ  ህገ-መንግሥቱን በጣሰ መንገድ የተካሄደ ዘረፋ ነው፡፡ የኦሮሙማ አገዛዝ ያለአንዳች ማስተር ፕላን ጥናት በኦህዴድ ብልጽግና ዘረኛና ተረኛ የኦሮሙማ ሥርዓት  ህዝብ ያላማከረና 600000 (ስድስት መቶ ሽህ) ሰዎችን በግፍ ያፈናቀለ የከተማ ህዝብ ንቅለ ተከላ የተከናወነበት ዘመን ነው፡፡ ማንነት ተኮር በአማራነታቸው ምክንያት የተፈላቀሉ ነበሩ፣  ኮነሬል አብይና ሽመልስ አብዲሳና አዳነች አቤቤ ለሚቀጥለው ምርጫ የዲሞክራፊ ለውጥ በማድረግ አሸናፊ ለመሆን ያደረጉት የፖለቲካ ሴራን አሁኑኑ ማስቆም ካልተቻለ ህዝባዊው ተግል አደጋ ላይ ይወድቃል እንላለን፡፡ የሸገር ከተማ ምሥረታ ዋና ድብቅ አጀንዳ የአማራ ንዋሪዎችን በመንቀል የኦሮሞ አስተዳደር በመመሥረት  የአዲስ አበባን ከተማ ወደ ኦሮሚያ ለማካተትና ለመሰልቀጥ የተወጠነ መሆኑን በሸገር ከተማ ምስረታ ማግስት ህገወጥ ተብለው የፈረሱት የአማራ ቤቶች በመሆናቸው መረዳት አያዳግትም፡፡  

  • ሸገር ከተማ ፕሮጀክት፡- የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሸገር ከተማን ከአዲስ አበባ መንገዶች ጋር ለማስተሳሰርና ለማሳለጥ 150 ኪሎ ሜትር  የመንገዶች ግንባታ  4.5 ቢሊዮን ብር ተመድቦ ተጀምሮል፡፡ የክልሉ ፕሬዜዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የመንገድና ሎጂስቲክ ኃላፊ ሄለን ታምሩ እንዲሁም የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሸመ አዱኛ ሥራውን አስጀምረዋል፡፡

 (3) የኦሮሞ ሥነጥበብና ማሠልጠኛ ማዕከል፣ (2) የኦሮሞ ባህላዊ ምግብ ማዕከል፣ (3) ኦሮሚያ ባህላዊ ግብይት ማዕከል፣ (4) ኦሮሚያ ባህላዊ እቃዎች፣ (5) ስንቄ ባንክ፣ (5) ጋዲሳፋ ህንፃ (ጎኖፋ ኦሮሚያ) (6) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የፕሬዜዳንት ቢሮ፣  (7) ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ህንፃ፣ (8) የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህንፃ፣ (9) ኦቢኤን ሚዲያ ኮምፕሌክስ ህንፃ፣ (10) ኢንትሮዳክሽን ኦሮሚያ ህንፃ፣ (11) ልዩ ልዩ መንግሥታዊ ሚዲያና ኢንተርፕራይዝ ህንፃዎች ይገኙበታል፡፡ ከኦቦ ሽመልስ አብዲሳ በይፋ ማህበራዊ ገፃቸው ካሰፈሩት የተወሰደ፡፡ 

መደምደሚያ 

የኮነሬል አብይና ሽመልስ አብዲሳና አዳነች አቤቤ በቢሊዮኖች ብር የምትታለብ ላም፣ የአዲስአበባ ከተማ መሬትና የሸገር ከተማ መሬት ሽያጭ ለደሃው የኦሮሞ ህዝብ ጠብ የሚልለት አንዳች ነገር የለም፡፡ በኦሮሞ ህዝብ ስም የሚዘረፈው ኃብት ለጥቂት የኦዴፓ ብልጽግና፣ ኦህዴድ ካድሬዎች የሚቀራመቱት ኃብት ነው፡፡  

በኮነሬል አብይ አገዛዝ የስድስት አመታት የማያባራ ጦርነት የኦሮሞ ልጆች በየአውደ ውጊያው የሁለት ነጥብ ሰባት ሚሊዮኖች ኦሮሞዎች በጦርነትና በርሃብ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ የኦሮሞ ምሁራን ይሄን በማስረጃ የቀረበ ጥናት መርምረው የኮነሬል አብይ አህመድን አገዛዝ ለመገርሰስ ከአማራ ፋኖ ጋር ግንባር መሥርቶ ሥርዓቱን መቀየር ይኖርባቸዋል፡፡  በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ የኦሮሞ ልጆች በየእስር ቤቶች ውስጥ በመማቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

  • 1984 እኤአ የህዝብ ቁጥር መሠረት የኦሮሞ ህዝብ ቁጥር  29.1%   
  • 1994 እኤአ የህዝብ ቁጥር መሠረት የኦሮሞና ህዝብ ቁጥር 35%   
  • 2007 እኤአ የህዝብ ቁጥር መሠረት የኦሮሞ ህዝብ ቁጥር 36.7%   
  • 2024 እኤአ የህዝብ ቁጥር መሠረት የኦሮሞ  ህዝብ ቁጥር  34%   ……[ Episode-1 ] The Mystery of Millions of Missing Amharas: Where Have They Gone? – YouTube ይህን በኢትዮ ክሮኒክልስ የተዘጋጀ ዩቲዩቡ በማየት የሁለት ነጥብ ሰባት ሚሊዮኖች ኦሮሞዎች መጥፋት እንቆቅልሽ ምስጢር ይገለጽላችኃል፡፡ 

ምንጭ

  1. Ethiopian Airlines Plans To Build New Airport/Articles East Africa  
  2. Ethiopian Airlines Corporate website/ https://corporate.ethiopianairlines.com › details › ethiopi…..
  3. Geda Special Economic Zone Commence Construction (addisfortune.news)
Filed in: Amharic