>

የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት 1504 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ዘግቷል፣ 200 ጋዜጠኞች አስፘል!

የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት 1504 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ዘግቷል፣ 200 ጋዜጠኞች አስፘል!

ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)

Ethiopia: Massive crackdown on civil society organisations /19 Jul 2024 

Ethiopian Authority for Civil Society Organizations (ACSO) has shut down at least 1,504 Civil Society Organisations (CSOs).

ዘ ኦብስርቫቶሪ የስብዓዊ መብቶች ጥበቃና ተከራካሪ ድርጅት፡-Observatory for the Protection of Human Rights Defenders (FIDH-OMCT) የተመሰረተው በዓለም አቀፈ ጸረ-ቶርቸር (ስቃይ) ድርጅት (ኦኤምሲቲ) እና (ኤፍ አይ ዲኤች) ድርጅቶች ነው፡፡ ዘ ኦብስርቫቶሪ ጁላይ 19 ቀን 2024 እኤአ በወጣው ሪፖርት መሠረት  የኢትዮጵያ መንግስት የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች ጥሶል፣ የእራሱን ህገ-መንግሥት ድንጋጌ በመጣስ አንባገነን ስለሆነ የዓለም አቀፍ ህብረተስብ የኮነሬል አብይን መንግሥት እንዲያወግዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዲያፖራዎች በያሉበት ተቃውሞቸውን ማሰማት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ባለሥልጣን 1504 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ዘግል!!! 200 ጋዜጠኞች አስል!!!   

‹‹ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት እንዲሁም ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች የተረጋገጠውን የመደራጀት መብት በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ፤ የመደራጀት መብት በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጡ ሌሎች መብቶችን ለማስከበር ያለውን ፋይዳ በመገንዘብ፤ በሕገ መንግሥቱ እንደተደነገገው፣ የመንግሥት አሠራር በግልጽነት፣በተጠያቂነትና በአሳታፊነት እንዲከናወን ለማድረግ የነቃና በነፃነት የተደራጀ ማኅበረሰብ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን በማመን፤ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአገሪቱ ልማትና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያላቸው ሚና እንዲጎለብት ለማድረግ የተመቻቸ ምህዳር መፍጠር ወሳኝ መሆኑን በመረዳት››…………………………….(1)

​​The recent forced dissolution of numerous civil society organisations highlights an intensification in the restriction of civic space in Ethiopia, and constitutes a major violation of the rights to freedom of association and expression, which has harmful consequences on civil society as a whole. The Observatory for the Protection of Human Rights Defenders (FIDH-OMCT) urges the Ethiopian authorities to put an immediate end to this escalating crackdown on civic space and independent domestic human rights organisations. Paris-Geneva, July 19, 2024 – In recent weeks the Ethiopian Authority for Civil Society Organizations (ACSO) has reportedly shut down at least 1,504 Civil Society Organisations (CSOs) for failing to submit their annual reports. The ACSO, which is responsible for overseeing and ensuring the compliance of CSOs with the law, enacted these dissolutions under the revised Civil Society Organizations Proclamation of 2011. …………………………………….……………..(2) 

የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት የኮነሬል አብይ አንባገነናዊ አገዛዝ 1504 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አገር በቀል፣ ድርጅቶች፣ የውጭ ድርጅት፣ የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ የሙያ ማህበራት ዘግተዋል!!! 200 ጋዜጠኞች አስረዋል!!!   

  • /“የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅትማለት ቢያንስ ሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች በፈቃደኝነት የሚመሠረት፣ የመንግሥት አካል ያልሆነ፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ከማናቸውም የፖለቲካ ድርጅት ያልወገነ እና ሕጋዊ ዓላማን ለማሳካት ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ አካል ሲሆን፣የሙያ ማኅበራትን፤የብዙኀን ማህበራት እና የድርጅቶች ኅብረቶችን ይጨምራል፤
  • /አገር በቀል ድርጅትማለት በኢትዮጵያ ውስጥ ወይም ከኢትዮጵያ ውጭ ሕጋዊ ሥራን ለመሥራት በዚህ ሕግ መሠረት በኢትዮጵያዊያን፣ በኢትዮጵያ ነዋሪ በሆነ የውጭ አገር ዜጎች ወይም በሁለቱ አማካኝነት በጋራ የተቋቋመ ድርጅት ነው፤ 
  • / “የውጭ ድርጅትማለት በውጭ አገር ሕግ መሠረት የተቋቋመና በኢትዮጵያ ውስጥ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፤ 
  • / “የበጎ አድራጎት ድርጅትማለት ለጠቅላላው ህዝብ ወይም ለሶስተኛ ወገን መስራትን አላማ አድርጎ የተቋቋመ ድርጅት ነው፤ 
  • /“የሙያ ማኅበርማለት አንድን ሙያ መሠረት በማድረግ የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን፣ ዓላማውም የአባላቱን መብትና ጥቅም ማስከበር፣ የሙያ ሥነምግባርን ማሳደግ፣ የአባላትን አቅም መገንባት እንዲሁም በሙያቸው ለሕዝብና ለአገር አስተዋጽዖ ማድረግን የሚጨምር ነው፤

‹‹የኤጀንሲው ዓላማዎች ኤጀንሲው የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡/ በኢ... ሕገመንግሥትና ኢትዮጵያ ፈርማ በተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት የመደራጀት መብት በተሟላ ሁኔታ እንዲረጋገጥ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፤ / ድርጅቶች በተመዘገቡበት ዓላማ መሠረት ሥራቸውን ማከናወናቸውን በመከታተልና በመቆጣጠር የሕብረተሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤ / ድርጅቶች አቅማቸው እንዲጎለብትና ተልዕኮአቸውን በብቃት እንዲወጡ ማስቻል፤ / በኅብረተሰቡ ዘንድ የበጎ አድራጎት እና በጎ ፈቃደኝነት ባሕል እንዲዳብር ማድረግ፤ / ድርጅቶች አሳታፊ የሆነ፣ ግልጽነትና እና ተጠያቂነት የሠፈነበት የውስጥ አስተዳደር እና አሰራር እንዲኖራቸው ማበረታታትና መደገፍ፤ / በድርጅቶችና በመንግሥት መካከል ሊኖር የሚገባውን መልካም የሥራ ግንኙነት ሊያጠናክሩ የሚችሉ አሰራሮችን መዘርጋት፤ / ለድርጅቶች የራስ ቁጥጥርና አስተዳደር ስርዓት ተገቢውን ድጋፍ መስጠት፡፡››

የኢትዮጵያ ባለሥልጣን 1504 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ዘግል!!! 200 ጋዜጠኞች አስል!!!   

በመላ-ኢትዮጵያ የሚገኙ ነባር የብዙኃን ድርጅቶች (Mass Organaizations) የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበር፣ የመምህራን ማህበር፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎች ማህበር፣ የገበሬዎች፣የሴቶች ማህበራት በሙሉ በደርግ ዘመን ጀምሮ፣ በመለስና ኮነሬል አብይ አንባገነኖች የግፍ አገዛዝ ስር ፈርሰዋል፡፡ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ሰባ ሽህ የኢትዮጵያ መምህራን አባላት ይገኛሉ፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ቁጥር አርባ አራት ሽህ ደርሶል፣ የባንክ ሠራተኞች ቁጥር ስልሳ ሽህ ደርሶል፣ የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ዞን ስልሳ ሽህ ሠራተኞች  አሉት፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሁለት መቶ ኃምሳ ሽህ ወታደሮች አሉት፣ ኢትዮቴሌ አርባ ሽህ ሠራተኞች አሉት፣ የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ስልሳ ሁለት ሽህ ሠራተኞች አሎቸው፡፡  የታክሲ ማህበራት አስራአምስት ሽህ ሹፌሮች አባላት ቢኖሩም በማህበር ተደራጁተው መብቶቻቸውን እንዳያስከብሩ ተደርገዋል፡፡ በማህበር ተደራጅቶ መታገል የመሰብሰብ፣ የሠላማዊ ሠልፍ፣ የሥራ ማቆም አድማ ወዘተ ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች በኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት አንባገነናዊ አገዛዝ ዘበት ሆኖል፣ ታዲያ እንዴት የአዲስአበባ ህዝብ  ተደራጅቶ ሊታገል ይችላል? ሃምሳ አራት ጋዜጠኞች በተሰደዱበትና ቀሪዎቹም የኢትዮጵያ ሚዲያ ፕሮፌሽናልሰ ሁለት መቶ ጋዜጠኞች በታሰሩበት አገር፣ በብዙ አስር ሽህዎች የአማራ ምሁራኖች በእስር ቤቶች ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ 107,260 (መቶ ሰባት ሽህ ሁለት መቶ ስልሳ) እስረኞች በአመዛኙ አማራዎች በማንነታቸው ምክንያት በአዲስ አበባ ወህኒ ቤቶች፣ ሸዋ ሮቢት፣ ድሬዳዋ፣ ዝዋይ፣ አዋሽ አርባ፣ ጦላይ   ወዘተ እንደሚገኙ የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ገልፆል፡፡ 

This unprecedented crackdown is part of an ongoing general repression against civic space and human rights defenders. In recent months, prominent human rights organisations in the country have been subjected to an increase of acts of intimidation, harassment, and threats by the authorities, including the ACSO, and several human rights defenders and journalists have been arbitrarily detained. A report from the Ethiopian Press Freedom Defenders, a collective of Ethiopian media professionals, found that around 200 journalists have been arrested by the Ethiopian government since 2019. The arbitrary closure of CSOs is yet another attempt to suppress civil society, as it seems the authorities use this measure as a tool going alongside with other forms of harassment in retaliation for their work. Over the past years several human rights defenders including journalists, academics, CSOs leaders have been forced to live in exile fearing reprisals.

ምንጭ

  1. Proc-No.-1113-2019-Organizations-of-Civil-Societies.pdf
  2. Ethiopia: Massive crackdown on civil society organisations/19 Jul 2024 

 

Filed in: Amharic