>
5:26 pm - Monday September 15, 2594

ለአማራ ምሁራን ምክረ - ሀሳብ

ለአማራ ምሁራን ምክረ-ሀሳብ አለኝ፦

መምህር ፋንታሁን ዋቄ

የአማራ ምሁራን ሚና በአማራ በህልውና ትግል ውስጥ
ማንኛዉም የህልውና ትግል ውጤታማነቱን ማረጋገጥ የሚችለው ዘርፈ ብዙ የህልውና መሠረቶችን ታሳቢ ያደረገ ጉዳዮች ተንትኖና በሁሉም አቅጣጣ ተመጋጋቢ ድሎችን ማስመዝገብ ሲችል ነው። የአማራ የህለውና ተጋድሎም እንደዚሁ አሁን በፋኖ ከሚካሄደው የጥትጥቅ እኩልና ጎን ለጎን፥ ብሎም ከትጥቅ ትግሉ መጠናቀቅ መኃላ በአጭር፥ በመካከለኛ ግዜ (ከአሁን እስከሚቀጥሉት ፭ ዓመታት፥ ከ፮-፲፭ ዐመታት፥ ከ፲፮ እስከ ቢያን ፴ እና ከዚያ በላይ ዓመታት የሚመዘገቡ ድሎች፥ በየድል ምዕራፉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአጠቃላይ ምን የተሻለ ሕይወትና የትውልድ ሰላማዊና ሁለገብ የሰብአዊ ክብር ሁኔታ እንዲሚያረጋግጥ የሚያመለክት የድል ጉዞ ፍኖተ-ካርታን ከወዲፉ በጭናጭልም ቢሆን ማሳየት አለበት።
ይህ ተግባር በአብዛኛው በሜዳ ላይ ውድ ሕይወቱን አስይዞ ለመጀመሪያው ድል፥ ማለትም የአመራን ሕዝብ ከጥፋት የመታደግ ተጋድሎ ላይ ከተሰለፈው ተዋጎ ኃይል የሚጠበቅ አይደለም። ይህ ፍኖተ-ካርታ፥ ፍኖቱ ላይ ለመሄድ የሚያስፈልገው መርህ፥ አቅምና አደረጃጀት፤ አደረጃጀቱ የሚመራበት ፖለቲካዊ፥ አስተዳደራዊና ማኅበራዊ አመራር ምን መሆን እንደሚገባው፥ በወዳጅነትና በጠላትነት የተሰለፉ አካላት በፍኖቱ ላይ በሚደረግ ጉዞ ውስጥ የሚኖራቸው ሚና እንዴት መስተናገድ እንደሚገባው፥ የትጥቅ ትገሉ መጠናቀቂያ መሥፈርቶችና ቀጣይ ተጋድሎዎች አይነትና አመራር ወዘተ ሁሉ በምሁራን ሊታሰብባቸውና ግልጽነት እያገኑ መሄድ የሚገባቸው ናቸው። በአመራ ሕዝብ የህልውና ትግልም ይሁን የትግሉው ውጤቶች ዘለቄታዊ ዋስትና ለማስገኝ በሚደረጉ ተያያዥና ተከታታይ ከትጥቅ ውጭ የሆኑ ተጋድሎዎችን ትርጉም፥ አካሄድ፥ ፍልስፍና፥ አመራርና ዲፕሎማሳዊ ማኅቀፍ ለመንደፍ “ምሁራን” ተብለው በዚህ ሰነድ የሚጠቀሱት፦
♦ አገር-ፈለቅ ዕውቀት ባለቤቶች (በሃይማኖት እስተምህሮ በየቤተ እምነቱ ሊቅ የሰኙ) ወይንም ብሔራውያን ሊቃውንት፤
♦ ዘመኑ ያስገኛቸው የዓለማዊ (ዩኒቭረሲቲ) ትምህርት ሊቃውንት ሆነው ከዚህ ቀደም በጸረ-ነባር- ኢትዮጵያ እሤቶች ጠላትነት ባላቸው የፖለቲካ ርእዮት በሚመሩ አካላእተ ጋር ያልሠሩ፥ እውነትን ለመከላከል ከሐሰተኛ ትርክትና ከስሑት ርእዮቶች ጋር በመጋደል የሚታወቁ፥ ምራባውያንና ምሥራቃውያንን በአጠቀላይ ባእዳንን እንደ መፍትሔ የማይወስዱና በኢትዮጵያ ማኅበረሰቦች የታፈነ እምቅ አቅም የሚያምኑ)፤
♦በባህልም፥ በሃይማኖትም፥ ነዘመናዊ ዓለመዋዊ ትምህርትም እውቅና ባይሰጣቸውም ወይንም በሁሉም አይነት ውሁድንተ የራሳቸው ዕሳቤ አዳብረው አገርና ማኅበረሰባቸውን ለሰላም፥ ለአገራዊ አንድነት፥ ለሰብአዊነትና ለፍትህ እንዲቆሙ አስተዋጽኦ በማድረግ የሚታወቁ ግለሰቦች የሚያካትት ይሆናል። ይህ ቅይጥ ባለፉት ፶ ዓመታት አገራዊውን ነባር አስተሳሰቦችና በአስተሳሰቦቹ ላይ የተመሠረቱ እምነቶችን፥ ባህሎችን፥ ማኅበራዊ ተቋማትን፥ የፍትሕና የአስተዳደር ሥርዐቶችንና መሪዎቻቸውን በአብዮት ወይንም በትምህርትና ምርምር ስም በመዋጋት አገርን አሁን አደጋ ላይ ከጣሉት ምሁራን መፍትሔ ከመጠበቅ የተላቀቀ ሂደትን ለመምራት ይጠቅማል።
የአገራቸውን ጸጋና ሀብታት የማይት አቅም በማጣት ከባእዳን ጋር እየተባበሩ ለባእዳን ዘርፈ ብዙ ጣላቃ ገብነት መረማመጃ ይሆኑ የነበሩና እየሆኑ የሚገኙትን ምሁራን ከአውዱ በማስወጣት አዲስ ነገር ግን በነባር አገር-ፈለቅ አቅም የሚበየን የችግሮቻችን መፍትሔ ትልምን በማስቀመጥና በመምራት አስተማማኝ ጎዳና ላይ አገራችንን የሚያስቀምጡ ምሁራንን ወደፊት ለማምጣት ይጠቅመናል።
የምሁራን ትኩረትን ለመሰብሰብ ልንግባባበት የሚገቡ የዐሳብ ማኅቀፎች
፩) የአማራ ሕዝብ የሕልውና ተጋድሎ ማድረጉ አማራጭ የለዉም።
፪) አማራ ሙሉ በሙሉ ጠላቶቹንና ሀሳባቸውን አለማሸነፍ መጥፋት ይሆንበታል።
(#ድል ፩)
፫) ከማሸነፍ በኋላ ድሉን ለማዝለቅ የግድ መሟላት ያለባቸውን ሁኔታዎች መፍጠርና የመጠበቅ አቅም ላይ መገኘት ግድ ይለዋል።
(#ድል ፪)
፬) #ድል ፩ እና #ድል ፪ እንዲሳካ የውስጥና የውጭ ተዋንያን አዎንታዊነት እና አሉታዊነት ፤ ፍላጎት፣ አቅምን ያገናዘበ ግኑኝነትና ትግል ተለይቶ በእቅድና በታወቀ ስልት መመራት ይኖርበታል
፭) ምሁራን ድርሻቸው ግለሰብ በመደገፍና በመቃወም የካድሬና የአክቲቢስት ደረጃ ያላቸው #ለድል ፩ እና #ድል ፪ መረጋገጥ ሁለተኛ ደረጃ ወይንም በምንም አይነት አዎንታዊ አስተዋጽኦ በሌላቸው ጉዳይ መገኘት የለባቸውም።
ስለዚህ አንድ ምሁር አፍ ከመክፈታችን እና ለመጻፈፍ ጣት ከመቀሰራችን አስቀድሞ #ለድል ፩ እና ለ#ድል ፪ ምን አስተዋጽኦ ላደረግ ነው? ይበል።
ዕውቀታችንንና ሌሎች ዲፕሎማሳዊና ፖለቲካ ክሂሎቶቻችን አውጥተን ከመጻፍና ከመናገር አስቀድሞ ለድሎቹ ያላቸውን አስተዋጽኦ የመመርመር ባህል አንዲስፋፋ ማድረግ የሚኖርባቸው ለዚህ የአማራ ተጋድሎ አስተዋጽኦ ለማድረግ የሚደክሙ ምሁራን ሁሉ ኃላፊነት ነው እናስፋፋ ፤ ለድሎቹ አስተዋጽኦ የማያደርጉ ተራና አድካሚ መልእክቶችን በአመክንዮአዊ ተጠየቅ በመሞገት ከፖለቲካውና ከሚዲያ አውዱ እንዲወገዱ ማድረግን ታሳቢ ያደረገ ተሳትፎን ከፍ ማድረግ።
እውነቱን ለመናገር፥ ሌባ እየቀደመ እና ፖሊስ እየተከተለ እንደሚኖረው አይነት ሁኔታ ጠላት አጀንዳ እየሰጠ፥ ጥቃት እየከፈተ ምላሽ በመስጠት እና ራስን በመከላከል የተጠመደውን የአማራ ፋኖ እና የምሁር ወደ አዲስ የመምራት ደረጃ ለማሸጋገር በሁለቱ አጀንዳዎች ላይ ብቻ አተኩሮ መሄድ ያስፈልጋል። አሁን በአለው ሁኔታ ግን ሌሎች ባመነጩት አስተሳሰቦች ላይ ትችት በማቅረብና ስሜታዊ መልእክቶችን ከማመላለስ በዘለለ ለትግሉ ግልጽ የፍልስፍና፥ የመርህ፥ የግብና ይርዮት ጥራት በማዋለድ ላይ አስተዋጽኦ የሚያደርግ የምሁራን ተሳትፎ አይታይም።
በቅንንት ለትግሉ አስተዋጽኦ ለማድረግ የሚሞክሩ ምሁራንም ቢሆኑ የየግል አስተሳሰባቸውን በመከላከልና በማጉላት ላይ ከማተኮር አልፈው ሁለቱን የድል ወጤቶች አማክለው ያደረጉት ተጨማሪ ዕሴት የለም ማለት ያስደፍራል። አንዳንዶች በእርግጥ ችግሩን ከተረዱ በኋላ በግላቸው መጽሐፍትን፥ የውስጥ ምክረ ሀሳቦችን እያበረከቱ ይገኛሉ። ይሁን አንጂ በተደራጀና በተናበበ መንገድ ለህልውና አደጋ የተጋለጠውን ሕዝብና በጦር ሜዳ የሚፋለመውን ፋኖ አንድ ወጥ የትግል አካሄድ፥ ግብና ሁለቱንም የድል ውጤቶች የሚያስጨብጥ ትምህርትና ሰነድ ከምሁራኑ አልፈለቀም።
“አብዛኛው ምሁር ግን እንዲህ ቢያደርጉት ጥሩ ነበር። እንዲህ አድርገው አበላሹት። እንደ ዚህ ካላደረጉ በስተቀር ለውጥ አይመጣም” በሚል ያልተደራጀና በግልዕይታ ላይ የተመሠረቱ ትችቶችን በመሰንዘር ለዋናው የግብ ውጤቶች መመዝገብ ሁነኛ አስተዋጽኦ ሳኣደርጉ ጉልበታቸውን አባክነው ቀርተዋል፤ በትግል ሜዳው ላይ ወጥ አስተሳሰብና መግባባት እንዳይኖር አሉታዊ ጫና ፈጥረዋል።
ምሁራን ፍሬያማ አስተዋጽኦ ለማድረግ ሊመልሷቸው የሚገቡ ጥያቄዎች
(፩) የአማራ የህልውና በትጥቅ ደረጃ፥ በፖለቲካ ደረጃ፥ በዲፕሎማሲ ደረጃና በሥርዓተ መንግሥት ቅርዕና ይዘት ደረጃ ምን ሲያሳካ ነው ትግሉ አለቀ የሚባለው?
(፪) የአማራ ህልውና ትግል ድል የሚያደርገው ማንን ነው? ምንን ነው? ለምን?
(፫) የአማራ ህልውና ትግል በድል መጠናቀቅ ማንን ይጠቅማል? ማንንስ ይጎዳል? ለምን?
(፬) ትግሉ ሲያልቅ የአማራና ሌሎች ማኅበረሰቦች ግኑኝነት፥ የጥቅም ተጋሮሽ፥ አሁን ሁሉም ከሚገኝበት አጠቃላይ ሁኔታ አንጻ ምን አይነት ለውጥ ይጠበቃል? (
፭) ሁሉን የሚጠቅምና ለህለውና አደጋ የሆነውን ጠላት በዘለቄታዊነት ድል ሆኖ ተጋድሎው አንዲጠናቀቀ ማን አዎንታዊ አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይገባል? ድሉምስ ሊያስተጓጉሉ የሚሠሩ አካላት ፍላጎትና ግብ፥ ወይንም ድሉ ከተሳካ በኋላ እንዲዘልቅ ወይንም እንዳይዘልቅ የሚያደርጉ ተዋንያን እንማናቸው?
(፮) ድሉ ጠቃሚና ዘላቂ እንዲሆን ምን (ፖለቲካዊ፥ ወታደራዊ፥ አስተዳደራዊ፥ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ)ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው? ለምን?
(፯) ትግሉ ለድልድ እንዳይበቃ፥ ከበቃ በኋላ እንዳይ ዘልቅ ምን እንቅፋት ይጠበቃል? እንቅፋቶቹ እንዴትስ ሊወገዱ ይችላሉ?
(፰) ይህ ሕይወትና ሀብት፥ የማኅበራዊ ጸጋዎቻችንና ቤተሰቦቻችንን የምንገብርለት ተጋድሎ ወጋ ለከፈሉት፥ ዳር ቆመው ለተመለከቱት፥ ትግሉን ላዘገዩት ወይንም ላፈጠኑት ግለሰቦች፥ የታወቁ አደረጃጀቶች፥ ማኅበረሰቦች ምን አግባብነት ያለው ጥቅም ይሰጣል ወይንስ ይነሳል? እና የመሳሰሉ ወሳኝ ጥያቄዎችን የመመለስ ክርክር፥ ጽሑም፥ ገለጻ የሚጠበቀው ከምሁራን ነው።
ምሁራን ምክረ ሀሳቡን ወደ ተግባር ለመቀየር ምን ያድርጉ
ሳይንሳዊም ሆነ አገር በቀል እውቀት ያላቸው፥ ለኢትዮጵያዊ የማኅበረሰብ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ፥ መንፈሳዊና ባህላዊ ጸጋዎች በአዎንታዊነት በመቀበል ለዚህ የህልውና ትግል አስተዋፅኦ ማድረግ ካለባቸው፦
፩) ቢያንስ ሚናቸውን ከማወቃቸው ቀድሞ ሁሉም የህልውናው ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ምሁራን ብሐራውያኑን በክብርና በትህትና በማሳተፍ በጋራ የሚነጋገሩበትን መድረክ መፍጠር።
፪) ከላይ በተገለጹ ፪ ድሎች አንጻር የሚወያዩበትን አጀንዳና ግቦችን በግልጽ መቅረጽ
(፫) ከላይ “የምሁራን ሚና” በሚለው ርዕስ ሥር የተጠቀሱትን ፭ ነጥቦች ለማስተግበር የሚያስቸል ሂደትና ተግባር በተክክል መንደፍ/ማቀድ፤
(፬) ተጋድሎውን በወታደራዊ፥ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ደረጃ፥ በሚዲያና በዲፕሎማሲ የሚመሩት ግለሰቦችና ቡድኖች ራሳቸውን የሚፈትሹበት፥ ሲቀበሉ የሚመሩበት፥ ለሕዝብና ለታጋዩ የሚያስተምሩበት የስልጠና ማንዋል በማዘጋጀት ለውይይት ወደሚመለከታው የአመራ ፋኖዎችና በእነርሱ በኩል ወደ ሕዝቡ ማውረድ፤ ከሕዝቡና ከታጋዩ የሚገኘውን ግብረ መልስ እየተቀበሉ በዕውቀትና በመውይይር የሚስተካከለውን እያስተካከሉ መመለስ።
፭) ሂደቱ ተግባራዊ የሚሆንበትን የአፈፃፀም መመሪያ ማዘጋጀት፥ ሂደቱን መምራት፥ መሳተፍ፤
(፮) አፈፃፀሙን የሚገመግሙበት መቸት ግልፍ ማድረግና የእቅድ አካል ማድረግ፤
(፰) የተጠቀሱት ድሎችን ከማግኘት በተጨማሪ ድሉን ለማግኘት የሚከፈለውን ዋጋ ጭምር በመተንተን መስዋዕትነቱ በድሉ ሲመዘን ያለውን ዋጋ/ ብልጫ ያወዳድሩ።የሚከፈለው ዋጋ እንዴት መቀነስ እንደሚቻል ጭምር። የሚመለከታቸው አንዲያውቁት በማድረግ የልብ መከፋፈልና መሰልጨትን ማስቀረት፤
(፯) የትግሉ አካሄድ፥ ውጤቱ፥ ዘለቄታዊነቱ በሁሉም የሐገራችን አካባቢዎች እኩል ተቀባይነት እንዲኖረው ትግሉ በትክክል የህልውና መሆኑን ለማሳየት መሥራት።
Filed in: Amharic