አንበሳው የፈራ ከመሰላት ሞትን የናቀች አይጥ ትደፍረዋለች!
ከፋንታዬ ሠርጸ
(ይህ ጽሁፍ ለአዋዜዎቹ – አለምነህ ዋሴና ኢሳያስ – ምስጋና – ይሁንልኝ)
የዩክሬንና ሩስያ ጦርነት የተጀመረው 23 February 2014 ዓም ሲሆን19 March 2014ዓም ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ሩስያ ክሪሚያን በመጠቅለል (annexation of Crimea) ተጠናቀቀ። በጦርነቱ 6 ሰዎች ሞቱ። ሁለተኛው ወደ ሩስያ መቀላቀል የሚፈልጉ የዶንባስ ተገንጣዮችን (pro-Russian separatis
ጦርነቱ
በጦርነቱ ምክንያት እጅግ በርካታ ዩክሬናውያን አገራቸውን እየለቀቁ አውሮፓ ወደሚገኙት አገሮች ተሰደዋል። ከሁለቱም ወገን፣ ከዩክሬንም ከሩስያም፣ እጅግ በርካታ ወታደሮች መሞታቸው ይታወቃል። ሩስያ እስካሁን ድረስ የያዘቻቸው የዩክሬን ግዛቶች ዶነትስክ (Donetsk)፣ ካርኪቭ (Kharkiv)፣ ኬርሶን (Kherson)፣ ሚኮላዪቭ (Mykolayiv) እና ዛፖሪዥዥያ (Zaporizhzhya) ናቸው። አሁን ላይ ሩስያ የምታካሂደው የፖክሮቭስክ ማጥቃት (Pokrovsk offensive) ስትራቴጅያዊ የሆነችውን የፖክሮቭስክ (Pokrovsk) ከተማ የማያዝ ሙሉ በሙሉ የዶነትስዝን ግዛት የመቆጣጠር ሂደት ነው። ይህ ሲሆን ሩስያ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ብላ የሰየመችውን ውጊያ ታገባድዳለች። ሆኖም ግን የኔቶ (NETO) ኃይል በድብቅ የሚሳተፍበት የሩስያና የዩክሬን ጦርነት ወዴ እንደሚሄድ መተለሙ ከበድ ይላል።
አለምነህ ዋሴና ኢሳያስ አዋዜ በሚለው መገናኛ ብዙሃን የዩክሬንና ሩስያ ጦርነት ከተጀመረበት 24 February 2022 ዓም ጀምረው አሁን ድረስ ጠቃሚ መረጃዎችን አጠናቅረው በማቅረብ ግንዛቤዎችን ሲያስጨብጡ ቆይተዋል። ከዚያ በፊት ካልተጠናቀቀ24 February 2025 ዓም ጦርነቱ ሶስተኛ ዓመቱን ይደፍናል። ሁለቱ ጋዜጠኞች ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ይህን የዓለም ስጋት፣ የሰው ልጆች የልብ ትርታ የሆነውን ጦርነት በዜና፣ በሠበር ዜና እና አስተማሪ በሆነ ውይይት እያቀረቡልን ያስደምጡናል። ኢሳያስ ይጠይቃል “ሩስያ ያስቀመጠችው ቀይ መስመሮች ሁሉ ተጥሰዋል። ምዕራብያውያኑ ርቀት የሚጓዙ ተምዘግዛጊ ሚሳይል (ATACMS – STORM SHADOW) እየሠጧት ነው፣ ኔቶ ኢላማን በማሳለም ይረዳቸዋል፣ ይህ ሩስያን አደጋ ውስጥ አይከታትም?” አለምነህ ብዙ ጊዜ የሚናገራት አረፍተ ነገር አለች። “ባላሙያዎች – ሳይኮሎጂ በሁለቱም በኩል የሚቆርጥ ባለስለታም ቢላዋ ነው ይላሉ“። ጥያቄውም መልሱም መጪውን አሳሳቢ ሁኔታ ከወዲሁ የሚተነብዩ ድርብ ትርጉም (double meaning) ያላቸው የነገው ፖለቲካ አካሄድ ጠቋሚዎች (political aspects) ናቸው። እስኪ ወደ ታሪክ ልግባ።
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት፣ ተስፋና ስጋት
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዘመን ዓለም እንደነ ፍራንክሊን ሮስቬልት፣. ዊንስተን ቸርቺልና ጆሴፍ ስታሊን የመሳሰሉ ከዓላማቸው ውልፍት የማይሉ ወሳኝ መሪዎች ነበሯት። ሶስቱም መሪዎች የጋራ የፖለቲካ ዓላማ ባይኖራቸውም የሁለተኛውን ዓለም አቀፍ ጦርነት ቋጭቶ፣ የጀርመን ሂትለር ፋሺዝምን አንኩታኩቶ የዓለም ሰላምን በማስፈን ረገድ ላይ ግን ተመሳሳይ ሃሳብ ነበራቸው። ሶስቱ መሪዎች ያልታ (Yalta) በምትባል የሩስያ የጥቁር ባህር ክሬሚያ ዳርቻ (Russia`s Black Sea Crimean Coast) በምትገኝ ትንሽ ከተማ ተሰብስበው ነበር ሂትለርን ለመቋቋም ስምምነት አድርገው ፋሺዝምን የገረሰሱት። ፋሺዝም ሲገረሰስ ዓለም ወደ አዲስ የሽግግር ዘመን ተሸጋገረች። ሆኖም ግን በርዕዮተ ዓለም ልዩነት ምክንያት በኃያላኖቹ (አሜሪካና ሶቭየት ሕብረት) መካከል የቀዝቃዛው ዘመን መልክዓ–ምድራዊ ውጥረት (geo-political tension) ተ
ኃያላን አገሮች እንዳይዋጉ ከሚደረግባቸው ዘዴዎች አንዱ ድምጽን በድምጽ የመሻር – የቬቶ (VETO POWER) መብት ነው። ይህ የፖለቲካ ሥነ–ልቦና (political psychology) ሃሳብ የመነጨው አቶሞክ ወይንም ኒውክለር ቦምብ ከያዙት አምስቱ ኃያል አገር መካከል (ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ሶቭየት ሕብረት ወይንም ሩስያ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካ) አንደኛው ያልተስማማበት ውሳኔ እንዲሻር ለማድረግ ነበር። አንድ ኃያል አገር ብቻውን (unilaterly) ህጉ የሠጠውን መብት በመጠቀም ብሄራዊ ፍላጎቱን ለማስከበር ወይንም ከጦር ስትራተጂክ አኳያ ሊሆን ይችላል (defend national interests or strategic necessity) የብዙሃኑንን ውሳኔ ያመክናል። አሠራሩ ዴሞክራሲያዊ ባይሆንም፣ የፖለቲካ ጠበብት፣ የዓለም ሰላም ለማምጣት በሚከወነው ጥረት (global peace making effort) ውስጥ ጠቃሚ አስተዋጾ ያደርጋል ይላሉ። ብዙ ጊዜ ቬቶ በማድረግ የምትታወቀዋ አገር የቀድሞዋ ሶቭየት ሕብረት የዛሬዋ ሩስያ ነች።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከ 12 March 1947 ዓም እስከ 26 December 1991ዓም ድረስ ለ44 ዓመታትና ዘጠኝ ወራት በሶቭየት ህብረት – ምሥራቅ አጋሮች (Eastern Bloc) እና አሜሪካ – ምዕራብ አጋሮች (Western bloc) መካከል ሠፍኖ የነበረ የቀዝቃዛው ዘመን መልክዓ–ምድራዊ ውጥረት አበቃ። የሶቭየት ህብረት 26 December 1991ዓም ቀን ሲፈርስ ዓለም በአሜሪካና ምዕራብ አጋሮችዋ መመራት ጀመረች።
አሜሪካ ብቸኛዋ የዓለም መሪ ከሆነች በኋላ ትዕዛዝዋን አላከብር ያሏትን አገሮች ዓለም ባንክ ገንዘብ እንዳያበድሯቸው በማድረግ ወይንም በማዕቀብ በመቅጣት ምጣኔ ኃብታቸውን በማንኮታኮትና ወጣቶችዋን በማሰደድ ትጎዳቸው ጀመር። ኢፍትሃዊነት (injustice) ሥር ሰደደ። ቭላድሚር ፑቲን ሩስያን በሶቭየት ዘመን የነበራትን ክብሯን ለማስመለስ ያደረጉት ያላሰለሰ ጥረት ለ30 ዓመታት የዘለቀውን የአሜሪና ብቸኛ ኃያልነት (unilateral power) ስጋት ውስጥ ዳረገው። የሩስያ ዳግም መነሳት ሌላ የሽግግር ዘመን እንዲከሰት ምክንያት ቢሆንም ችግሩ አደገ እንጂ አልቀነሰም።
ዘመናት ሁሉ የሽግግር ዘመናት (ages of transition) ቢሆኑንም አብዛኛዎቹ ዘመናት የራሳቸው ጽንፎች (extremes) አሉዋቸው። ፍልስፍና – የእውነት እና የምክንያታዊ እውቀት ፍለጋ ሲሆን ሃይማኖት ደግሞ ግለሰብን በደግነት ሥራ ላይ እንዲሰማራ እያተጋና ወደ እግዚአብሄር እንዲጠጋ የሚያደርግ ግብረገባዊነት ነው። ይህም ሆኖ ጥቂቱ ግብረገባዊ – ኢ–ግብረገባዊ በሆነ ማህበረሰብ (immoral society) ውስጥ ለመኖር ስለሚገደድ ለፍትህ ከመታገል ይልቅ አስመሳይ ሆኖ መኖርን ይመርጣል። አንዳንድ ቦታ ላይ እየሱስ ክርስቶስ አምላካዊ ስሙ ከመለመዱ የተነሳ ጓደኛ እንጂ ፈጣሪ መሆኑ ተረስቷል። የምዕራቡ ዓለም አጓጊና አስጎምዢ ሥርዓት እምነትን (faith) አቀዝቅዟል። ሃይማኖትም፣ ፍልስፍናም ሆነ ሥልጣኔ አህጉራትን ከጦርነት ካደጋ አይታደጉም።
ታሪክ ዲያሌክቲካው ሂደት ነው። የታሪክ ባለቤት እግዚአብሄር ነው። እርሱ ያለው ይሆናል ያላለው አይሆንም። ዓለም በምስቅልቅልና ጉራማይሌዎች የተሞላች ነች። ፍትህ ስትታፈን የኃብታሞች ኢ–ግብረገባዊነት ፈር ሲለቅ፣ ጎስቋሎች ሲጮሁ አዲስ የሽግግር ዘመን እውን ይሆናል። ማንም የቱንም ያህል ኃያል ይሁኑ የታሪክን ሂደት ሊያስተጓጉል አይችልም። ተፈጥሮ በምክንያት እና ውጤት (Cause and effect) ትንቀሳቀሳለች። ተፈጥሮ ሁለትዮሽ ነች። የዓለም ፖለቲካም ሁለትዮሽ ነው።
የምዕራብያውኑ የደህንነት ክፍል ጠቃሚ መረጃዎችን ይደብቃሉ። በዚህ ምክንያት ሰዎች አስተሳሰባቸውም ሆነ ፍርዳቸው ወደ አንድ ወገን ያዘነበለ ይሆናል። ይሁንና ግን እውነታ (reality) በምክንያት ብቻ አይደለም የምትገለጸው። እውቀትም ቢሆን ከልማድና ተሞክሮን መሠረት ካደረገ ሃቅ (Empricism) ትገኛለች። ባገራችን እድሜ ትምህርት ነው የሚባለው ለዚህ ነው። ሁሉም ፍትህን ይጠማል። በሁለትዮሹ መካከል ባለው ትግል ምክንያት አዲስ የሽግግር ዘመን አይቀሬ ነው። የአውሮፓ ሕዝብ የታሪክን አካሄድና አቅጣጫ ይመረምራል፣ ይወያያል፣ ይወስናል።
አውሮፓውያኑን የርዕዮተ ዓለም ዘመን (age of ideology) እንዳስመነደጋቸው ሁሉ የፍርሃትና የጭንቀት የድብርት ዘመንም (age of anxiety) አሳልፈዋል። አንዳንድ አገሮች የነጻነት ዘመን (age of liberation) ቢኖራቸውም በእጅ አዙር ደግሞ ይገዛሉ። የሉተር ፕሮቴስታንታዊነት በአንድ በኩል ፋሺስታዊነትና ኮሙኒስታዊነት በሌላ በኩል አውሮፓን ያናወጡ አስተሳሰቦች ነበሩ። በዚህ ሁሉ ጉራማይሌና ምስቅልቅሎች ያለፉት ምዕራብያውያን ዛሬም ከጦርነት ስጋት ውስጥ አልወጡም። ሃይማኖቱ፣ ርዕዮተ ዓለሙ፣ ፍልስፍናው፣ ነጻነቱ፣ ብልጽግናው፣ ወዘተ፣ ሰላምን ምሉዕ አላደረጋትም። ያላቸው፣ የደላቸው ሁሉ ዓለምን ዝብርቅርቅ ያደርጓታል። ይህ ሁሉ በተቃርኖዎች አንድነትና ትግል ምክንያት ነው።
የጦርነቱ አባባሽ
ጦርነቱን የሚያባብሰው እልህና ማንአህሎኝነት ነው። ጦርነቱን ያላባባሰው ደግሞ ትዕግስት ነው። የአለምነህ ዋሴና የኢሳያስ ውይይት “ሩስያ ፈተና ሲበዛባት ቀይ መስመር ብላ ያስቀመጠችው ሁኔታ ሲጣስባት አውዳሚ የሆነውን የኒውክለር ጦር መሳርያ ሙሉውን ወይንም ስልታዊውን ለመተኮስ ትገደድ ይሆን? የሚለው ስጋት ላይ ያተኩራል። ዜሌኒስኪ “ሩስያን አትፍሩ፣ ፑቲን ራሱ ለመኖር የሚጓጓ ሰው ነው፣ ኒውክለር አይተኩስም፣ እባካችሁ ከቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን ጀምሮ ከተጠናወናችሁ የሩስያ ፍርሃት (Russo-phobia) ተላቀቁ” የሚሉ አደፋፋሪ ናቸው። የዩክሬይን ሕዝብ ተሰዶ አገሪቱ ባድማ ሆናለች። እርሻ፣ ምርምርም ሆነ እንቅስቃሴ ታቅቧል። መብራት በሌለበት የበረዶ በረሃ ላይ የሚኖሩት ዜሌኒስኪ ብቻቸውን ናቸው። ምንም የሚፈሩት ነገር የሌላቸው ዜሌኒስኪ ሳይማሩ በድፍረት የሥነ–ልቦና ሊቅ ሆነዋል።
የአለምነህ ቃል ልጠቀምና በዜሌንስኪ አተያይ፣ ፑቲን የበጋ መብረቅ፣ የወፍጮ ቤት ድምጽ ናቸው። የዜሌኒስኪ ንግግር የአሜሪካን የላዕላይ መዋቅሩን ባላሥልጣናትና መሳርያ በመሸጥ ብዙ ማትረፍ የሚፈልጉ ነጋዴዎችን ይመስጣል። የአውሮፓ ሶሺያል ዴሞክራሲያዊ ፖለቲካና ከግሪኮቹ ዘመን ጀምሮ ያዳበሩት ፍልስፍና ከዚህ ሃሳብ ጋር አይስማማም። አውሮፓ ግራ ገባት። ዜሌንስኪ በአንድ በኩል በአውሮፓና አሜሪካ ማህል በሌላ በኩል ደግሞ እንደ መንፈስ በኔቶና ሩስያ ማህከል መቆም ይችላሉ። የዘመኑ ሽግግር ሰላማዊ እመርታ እንዳያደርግ በጦርነት ጽንፍ ተወጥሯል። የአሜሪካ ባለሥልጣናትንም ያወዛገበው ከሁለት አቅጣጫ የሚወረወሩ የሃሳቦች ፍላጻ ነው። ግራ ሲገባ እውነታ፣ ግንዛቤና ተሞክሮ ይደበቃሉ።
መደምደምያ
የሩስያና የዩክሬን ጦርነትን በሁለት አቅጣጫ ነው ማየት የምንችለው። አንደኛ – ይህ ጦርነት መልኩን ቀይሮ ምናልባት የሩስያና ኔቶ ጦርነት ይሆናል። ዜለኒስኪ ምዕራቡን ዓለም አሳምነው አገር አቋራጭ ረዥም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳይል (ICBM) እጉያቸው ሊሸጉጡ ይሆን? ፑቲን ይህን ያደረጋችሁ ቀን ውጊያው በሩስያና ኔቶ መካከል ነው ብለዋል። አባባ ተስፋዬ “አንበሳው የፈራ ከመሰላት ሞትን የናቀች አይጥ ትደፍረዋለች” እንዳሉት ነው። ሁለተኛ – የአውሮፓ ሕዝብ ይህን ጦርነት አይፈልገውም። እኔ ወደ ሁለተኛው ሃሳብ አመዝናለሁ። አውሮፓውያን ፕሮቴስታንታዊ ግብረገባዊ ባህልና ፍልስፍና ታጥቀዋል። ምዕራብ አውሮፓውያን ግብረገባዊ ባህላቸው የተቀዳው ከፕሮቴስታንታዊነት ሲሆን ምሥራቅ አውሮፓዎች የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ናቸው። የአሜሪካ የላዕይ መዋቅሩ ባለሥልጣናትም ሆነ ፊት ለፊት የማይታዩት የታላላቆቹ ከበርቴዎች ግብረገብ ንጣፍ ሃብትን ያቋደሳቸው ኬልቪናዊነት ነው። አሜሪካ በፖለቲካ ካፒታሊስታዊ ስትሆን አውሮፓውያን በአመዛኙ ሶሻል ዴሞክራቶች ናቸው።
የአውሮፓ ሕዝብ አስተዳደሩን ያከብራል፣ ለዴሞክራሲ ተገዢ ነው፣ መብቱ ከተነካበት ደግሞ እንደ አራስ ነብር ነው። አስተዳደሩ ወይንም መንግሥት ከፍላጎቱ ውጭ ምንም ነገር እንዲያደርግ አይፈቅዱላቸዋውም። ሕዝቡ ጦርነት አይፈልግም፣ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ የተጎናጸፈው ልማትና ሥልጣኔም እንዲነካበት አይፈልግም። በአሜሪካም ቢሆን እንኳንስ የኒውክለር ቦምብ ሃሩር ይቅርና ንፋስ እንዳይነካቸው የሚፈልጉ ዝነኞች (celebrities) አሉ። ጦርነቱ ከተከሰተ ማማር፣ ማጌጥና መሸላለም የለምና መጮሃቸው አይቀርም። በአሜሪካ ጦርነት የማይፈልጉ ደጋጎችም አሉ። ጦርነት ጥቂት መሳርያ ሻጭ ቱጃሮችንና ሥልጣን ናፋቂዎችን እንጂ ለደሆች ልጆች ፋይዳ እንደሌለው ያውቃሉና ድምጻቸውን ማሰማታቸው እውን ነው።
ፑቲንና የሩስያ ባለሥልጣናት ከአውሮፓ ሕዝብና ከተጎሳቆለው የአሜሪካ ሕዝብ ጎን ናቸው። የኒውክለር ጦርነት ቢከሰት መጀመርያ የሚጎዳው በኑሮ የዳበረው፣ ባሻው ጊዜ የሚዝናናው፣ ቅንጦቱና አሸሼ ገዳሜው የሚቀርበት፣ በሰላምና በድሎት የሚኖረው የምዕራቡ አገር ነዋሪ መሆኑ ይታወቃል። አገር አቋራጭ ረዥም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳይል ለዩክሬን ማስታጠቅ በአውሮፓ ሕዝብ ኅልውና ላይ መፍረድ ነው። ዜሌኒስኪ ያንጀራጅሯቸዋል እንጂ ይህን ሃቅ ባይደንም ብሊንከንም ያውቁታል። የሩስያ ትዕግስት ከኦርቶዶክሳዊ እምነታቸው የሚቀዳ ነው። ሩስያ ስመ ጥር የጦር ማርሻሎች እንዳሉዋት ሁሉ ደጋግ ሃይማኖተኞችና ምጡቅ ፈላስፎችም ሞልተዋታል። ሁኔታውችን ሚዛን ላይ አስቀምታ መመርመር የምትችለዋ ሩስያ ኃይልም ትዕግስትም ለብሳለች። ሩስያ ዩክሬንን ለማውደም ኒውክለር ወይም ታክቲካል ኒውክለር መጠቀም ላያስፈልጋት ይችላል። ሩስያ የሳይንስ መጋዘን ነች። ልዩ ልዩ ረቂቅ መሳርያዎች አልዋት። ሩስያ የፊዚክስ ሊቅ ነች። ሜዳው፣ ተራራው፣ ጉድጓዱና ሸጡ በጦር ቴክኖሎጂ ምርቶች ተጨናንቀዋል።
አንድ ትልቅ ቁልፍ ጉዳይ አለ። ዓለም በሽግግር ላይ ነች። እመርታውን ገና አላየነውም እንጂ። የዩክሬንና የሩስያ ጦርነት አንድ አዲስ ሁነኛ የሽግግር ዘመን ይዞ ይመጣል። ዓለም አሁን ባለችበት ቁመና አትቀጥልም። የአፍሪካም ልጆች ለጦርነት አይገበሩም።
እግዚአብሄር ዓለምን ይጠብቃል!