>

ወልቃይት የሚባል አውራጃ እንጂ ወልቃይቴ የሚባል ማንነትም የለም-!!!

አማራው ወደ ትግራይ የሚመልሰው ቅንጣት ስንዝር መሬትም ሆነ አማራዊ ማንነት ፈጽሞ የለም-!!!!

ወልቃይት የሚባል አውራጃ እንጂ ወልቃይቴ የሚባል ማንነትም የለም-!!!

ወልቃይት ወደ ትግራይ መመለስ አለበት የሚሉ የወያኔ የጭን ገረዶች ናቸው-!!!!

 

ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ

 

አብሮነት” የተሰኘው የእነ ልደቱ አያሌው ስብስብ የፋይናንስ ዘርፍ ሀላፊ ብለው የሰየሙት ሙሉጌታ ዘለቀ የሚባለው ግለሰብ ባንድ ወቅት ( በዚህ አመት መግቢያ ላይ ይመስለኛል) የብልጽግና ድምጽ ከሆነው #ቴዎድሮስ_አሰፋ ጋር ባደረገው ቆይታ ” ወልቃይት በአስቸካይ ወደ ትግራይ አስተዳደር መመለስ አለበት። የብልጽግና መንግስት የሚያሽከረክረው የወልቃይት አስተዳደር መወገድ፣ መደምሰስ አለበት “ እያለ ሲፋልል ተደምጦ ነበር።

በዚህ አይነት አቋሙም የእነ ልደቱ አያሌው “አብሮነት” የሚባለው ስብስብ የፋይናንስ ዘርፍ ሃላፊ አድርገው አምጥተውታል። አብሮነት የሚባለው የእነ ልደቱ ስብስብ – ፋሺስታዊውን የብልጽግናን ስርአት በሕዝባዊ እንቢተኝነትና በህዝባዊ አመጽ Which is አማራው ምድር አንቀጥቅጥ አመጽና ሰልፍ አድርጎ ሰሚ ያጣበትን ስልት ማለት ነው- ስርአቱን እንገርስሳለን እያለ የሚማዘዝ የስርአቱን ባህሪይና የሀገራችንንም ተጨባጭ ሁኔታን ገምግሞ መረዳት ያዳገተው ስብስብ ነው።

ፋሺስታዊውን ስርአት በሰላማዊ ትግልና በህዝባዊ እንቢተኝነት ማስወገድ ስለመቻሉ ለአብሮነቶች ትቼ ይህ ሙሉጌታ ዘለቀ የሚባለው ግለሰብ ስለተናገረው የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ግን የምለውን ላስፍር።

፩ኛ- አማራው ከወያኔ ጋር ታርቆ አብሮ ብልጽግናን ለመታገል አሳልፎ የሚሰጠው ቅንጣት ታህል ስንዝር መሬትም ሆነ አማራዊ ማንነት ፈጽሞ የለም።

በአማራ እና በትግራይ (ህወሃት) መካከል እርቅ ለማወረድ ሲባል መፈጸም ያለበት ወሳኝ ተግባር የተበዳዪ – አማራው- ለሶስት ድፍን አስርተ አመታት የታገለለትን አማራዊ ማንነቱንና አማራዊ እርስቶቹን – ወልቃይት ጠገዴና ራያን ለህወሃት አሳልፎ በመስጠት ሳይሆን የነገደ አማራን ሕዝብ ህልውናን አደጋ ላይ የጣለውን ስርአተ መንግስትና ብሎም ጸረ አማራ ትርክቶችን ጸንሶ የወለደው ትህነግ

1- እስከዛሬ ሲተዳደርበት የቆየውንና አማራውን በጠላትነት የፈረጀበትን ማንፌስቶውን ሙሉ በሙሉ ቀዶ አዲስ ማንፌስቶ ማውጣት አለበት

2- ዛሬ አማራውን እና ብሎም የትግራይን ሕዝብ በማንነቱ ተነጥሎ እንዲዘመትበት ያስቻለውን ሕገ መንግስት – በስህተት ያጸደቅኩት ጸረ ኢትዮጲያ፣ ጸረ አማራ ሕገ መንግስት ስለሆነ መቀየር አለበት ብሎ ግልጽ አቋም መያዝና ያንንም አቋሙን ማወጅ ይጠበቅበታል።

3- አማራዊ እርስቶች የሆኑትን በወልቃይት ጠገዴና ራያ ላይ ያለውን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ሰርዞ አማራዊ ርስቶች መሆናቸውን መቀበልና ማወጅ አለበት

4- ህወሃት በስልጣን ዘመኑ ለፈጸማቸው ጸረ አማራ ተግባራቶቹ በይፋ ሃላፊነት ወስዶ ይቅርታ መጠየቅ አለበት

5- የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል እና የአማራን ህዝብ ጥያቄ ሙሉ በሙሉ አምኖ መቀበል ይጠበቅበታል።

ይህንን ከፈጸመ በሃላ አማራ እና ትግራይ እንደ ህዝብ ግንኙነታቸውን ይበልጥ አሽሽለው ወደ ፖለቲካ አጋርነት ደረጃ ማድረስ ይቻላቸዋል እንጂ አማራው ከህወሃት ጋር የፖለቲካ አጋርነትን ለመፍጠር ብሎ የሚመልሰው ቅንጣት ስንዝር መሬትና አማራዊ ማንነት እንደሌለ ማወቅ ይገባል።

፪ኛ- ወልቃይት የሚባል አውራጃ እንጂ ወልቃይቴ የሚባል ማንነት የለም-!!!!

ወልቃይት ጠገዴ በጎንደር ክፍለ ሀገር የሚገኝ አንድ አማራዊ አውራጃ ነው እንጂ ወልቃይቴ የሚባል ማንነት የለም። የወልቃይትን አውራጃ ስያሜን ወደ ማንነታዊ ወልቃይቴ ደረጃ ለማውረድና አውራጃውን የማንነት ስያሜ ለመስጠት የሚዳዳቸው አውራጃውን ከትልቁ የአማራ ግንድ ነጥለው ለጠላት ሲሳይ ለማድረግ የቃመጡ ሰርጎ ገብ ጸረ አማሮችና የፋሺስቱ ብልጽግና ካድሬዎች ናቸው። ወልቃይት የጎንደር አውራጃ ነው። ጎንደር አማራ ነው። በአውራጃ ውስጥ የሚኖሩ ትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች አሉ። በጦርነቱ የተፈናቀሉ አሉ። በጦርነቱ የተፈናቀሉ መመለስ ይችላሉ። አውራጃው ግን ወደ ትግራይ እስተዳደር ፈጽሞ አይመለስም። ይህ ህገ መንግስት እስካለ ድረስ አውራጃው በአማራ አስተዳደር ስር የሚተዳደር ይሆናል።

Filed in: Amharic