* ላበረከተውን አስተዋጽኦ ወንድሜን በክብር አስበዋለሁ
ከሁሉም እንዲያየው የምፈልገው አሁን አሁን ጋዜጠኝነት ለህለከና ተገዥ ሆነው ካልሰሩት ገንዘብና ዝና ለማግኘት ፣ የገቢ ምንጭ ማግኛ ሲሆን ለመኖር ተብሎ ሲሰራ ያረክሰል የምለውን የእውነት ሚስጥር አብራርቸ ብገገልጽለት ፣ የሀሳን ሙግት ካመጣ ልሞግተው ነፍሴ መሻቷ ያለነገር አይደልም ! …
ጋዜጠኝነት ዘር ፣ ሐይማኖት የማይለይ ሙያ ነው … ጋዜጠኝነት ሚዛናዊ መሆን ብቻ ሳይሆን ከእውነት ጋር ማደር ነው …ጋዜጠኝነት የግለሰብ እስከ ማህበረሰብ ድምጽ የሁሉም እውነት ማስተላለፊያ መግለጫ መሳሪያ ነው … ጋዜጠኝነት ከምንም በላይ ያዩትን እውነት የማስተላለፍ የህሊና ፍርድ መስጫ መሰሪያም ነው…ጋዜጠኝነት የተበዳይ ድምጽ ማስተጋቢያ ብርቱ መሳሪያ ነው …
እናም እየዋሹ ፣ እየቀጠፉና እየፈሩ ጋዜጠኝነት ሙያን ይቆሽሻል … ጋዜጠኝነት የገዥዎች የመጨቆኛ መሳሪያ ፣ ማባበያ እና መጨቆኛ ስውር መሳሪያ ሲሆን ይረክሳል …ጋዜጠኝነት የአንድነት ህብረት ጸር የሆነው የግለኝነት ግነት ማንጸባረቂያ ፣ የዘር ፣ ጎጥ አምላኪዎች መከፋፈያ ሲሆን ሀገር ያጠፋልና ክፉ መሳሪያ ይሆናል …
አቅሙ ለፈቀደ … ጋዜጠኝነትና አድር ባይነት አብረው አይሄዱም ብዬ አምናለሁ ! አድርባይነትን ለመቀበል ለተዘጋጄ ነፍስ ሙያው የስጋ ማደሪያ መሆኑ ብቻ ከመሆን አልፎ የከበደ ጉዳት አለው ! ጋዜጠኝነት የእውነተኛው አለም ፣ የከባቢውና ማህበራዊ ኑሮው ነጸብራቅ መሆን ያለበት ሙያ ነው ፣ ጋዜጠኛው ከራሱ አልፎ የሌላውን ሀሳብ ፣ ስሜት ና ፍለጎት መጻፍና መናገር የሚችል ዜጋ የዜግነት ድርሻን ለመወጣት የሚሰራው ስራ እንጅ የገቢ መጋፈፊያ ባይሆን ሁሌም።እመርጣለሁ! በአንጻሩ አለም የእውነቱን መረጃ የመቀበል እዝነ ክቦና ቢኖረው አለማ ችን በአጭር ጊዜ በቀናች ነበር እላለሁ !
ጋዜጠኝነት የመንፈስ እርካታ ጥግ ማድረሻ ፣ ከህሊና ወቀሳ መዳኛ ፣ የተጎዳ ህመም ማከሚያ የተከበረ ሙያ የሚል እምነቴ ስለመሆኑ ከሟች ወንድም አስተማሪ አባቴ ጋር የመሞገት መንፈሳዊ ፍለጎት አለኝ ፣ ከጋዜጠኛው ወንድሜና አባቴ ጋር ማድረግ የምፈልገው ውይይት በአዕምሮ የመጣው ስለ እወነት አድሮ ለእናት ሀገሩና ለወገኑ ያበረከተውን አስተዋጽኦ በክብር እያስታወስኩ ነበር !
አዎ ፣ የቀደሙ ስራዎቹን በውል ያስቀመጠ ወንድሜን ሰነዶች አደራጅቸ ለህዝብ የማቅረቡ ህልም በውስጤ ቢኖርም የገንዘብ ሳይሆን መረጃው ካለበት ቦታ የመድረስ አቅሙ የለኝምና እነሆ የማስታውሰው በደረቁ ነው 🙁 በጋዜጠኝነት ዘመኑ ያለፈባቸውን አይረሴ የህይዎት መንገድ ለህዘብ ለመቅረብ አቅሙ ያላቸው ወገኖቸ ደግሞ ሶስቱን ጉልቻ ለመጠገን ደፋ ቀና ሲሉ ጊዜ የላቸውም ይመስለኛል ! እኔ ግን ቀጣይ ህልሜ የጋዜጠኛና ደረሲ ወንደሜን ስራዎች ሰበስቤ ለቀሪው ትውልድ የማስተላለፍ ህልሜ አልጠፋም !
ብቻ ሰነዶች መድብል ሆነው ቀረቡ አልቀረቡ መጽሐፈ ሲራክ በምና ውቀው ዘንድ ክብሩ የገነነ ነው ፣ በዚያ ወቅት ኖራችሁ ስራውን በኢትዮ ጵያ ራዲዮና በለገዳዲ ራዲዮ የማለዳውን የእሁድ ጣፋጭ የጉዞ ፕሮ ግራምና መሳጭ ግጥሙን ያልሰማችሁ ፣ በአዲስ ዘመን በዛሬይቱ ኢትዮጵያና በቀሩት የህትመት ውጤቶች መጣጥፉን ላላነበባችሁ ለማ ታውቁ ለማስተዋወቅ እነሆ ዝካሬ መጽሐፈን ትጋበዛላችሁ ! ወንድሜ እንደ ስጋ ወንድምነቱ ሳይሆን እንደ ኩሩ የሀገር ባለውለታ ከዋዜማው እስከ እለተ ቀኑ ይታወሳል …የምወደው ሙያ አውራሽ ወንድሜ በዚህ የወንድሙ መድረክ ስሙ ከፍ ብሎ ስለሰራው ስራ ይመሰገናል ፣ በክብር ይታወሳል !
ክብር ለሚገባው ክብር ስሰጥ ኖሬያለሁና ወንድሜ ህይዎቱን ግብሯልና ክብር ሞገሱ አይቀርበትም ፣ እኔም ወንደሙን አሞካሸ ይሉኛል ብዬ በይሉኝታ ተጠርንፊ አላደላም ! ለሀገርና ለወገኑ በሙያው ሰርቶ ስላለፈው ሁሉ ታላቅ ክብር ይገባዋልና ክብር እሰጠዋለሁ !
ክብር ለሚገባው ክብር እሰጣለሁ !
ነፍስ ይማር ወንድም አለም 🙁
ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 9 ቀን 2009 ዓም