>

ለሻአቢያ ልጆች ኤርትራውያን የተሰጠው መብትስ ለኢትዮጵያውያን የሚፈቀደው መቼ ነው??? (ኤርሚያስ ቶኩማ)

ሕዝቡ በሌላ ፓርቲ መተዳደር ካልቻለ፣ ፓርቲው ሌላ ሕዝብ ያስተዳድራ
የኤርትራውያን ሰልፍ በኢትዮጵያ
ዛፍ አወጣጥ የሚያስተምረን ሰው አወራረድ ያስተምረን ዘንድ እንመኝ፡፡ የወጣ ሁሉ አይቆይም፡፡ የቆየ ሁሉ ደግሞ መውረድ አይቀርለትም። የታደልን እኛ ብቻ ነን ብንል ምፀቱ አይገለንም!! በአናቱ ከሚጨመር ሥርዓት ያድነን!! አንድ ኢትዮጵያዊ ፀሀፊ የሮዛ ሉክሰምቡርግን አስተሳሰብ በመጥቀስ የነቆጠውን፤ ስለ ምርጫ ስናስብ አቅም ይሆነን ዘንድ አሁን እናስበው፡- “ነፃነት፣ ቁጥራቸው የፈለገውን ያህል በርካታ ቢሆን፣ ለመንግሥት ደጋፊዎችና ለፓርቲ አባሎች ብቻ የሚሰጥ መብት አይደለም፡፡ ነፃነት ሁልጊዜም የተለየና ተቃዋሚ ሀሳብ ያለው ወገን መብት ነው፡፡ ይህን የምለው ለፍትህና ለርትዕ፣ ልዩና አምልኮ – ባዕዳዊ ፍቅር አድሮብኝ አይደለም፡፡ የፖለቲካ ነፃነት ህብረተሰብን የሚያድሰው፣ በዚህ ሀቅ ላይ ሲመሰረት ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ ነፃነት የተወሰኑ ምርጥ ወገኖች ልዩ-መብት (ፕሪቪሌጅ) ከሆነ የይስሙላ ነፃነት ነው የሚሆነው፡፡ ከላይ የጠቀስነው ኢትዮጵያዊ ፀሀፊ፤ የምርጫውን አሀዝ ብቻ ሳይሆን የህዝቡን ልብ እንገነዘብ ዘንድ የሚከተለውን እንመርምር ይለናል፡- “ወድቀው ከታሪክ ፊት በሀፍረት ሊሰናበቱ ሳምንት ሲቀራቸው ሁሉ 98 ከመቶ በሆነ ድምፅ ይመረጡ የነበሩት የምስራቅ አውሮፓ “ዲሞክራቶች” ነበሩ፡፡ “ዲሞክራሲያዊ ምርጫ”ን የይስሙላ ያደርገው የነበረውም ይኸው ነው፡፡ 90 በመቶም በላይ ድምፅ እያገኘ በሕዝብ ዘንድ ይጠላ የነበረውን የ (ምስራቅ) ጀርመን ኮሙኒስት ፓርቲ አስመልክቶ “ሕዝቡ ሌላ ፓርቲ መምረጥ ካልቻለ፣ ፓርቲው ሌላ ሕዝብ ይምረጣ እንግዲህ” ብሎ ቀልዶ ነበር ቤርቶልድ ብሬሸት፡፡”
“ለአንድ አገር የፖለቲካ ሥርዓት መጎልበት ለሕዝቦቿም ኑሮ መሻሻል አንድ ጭንቅላት ብቻ አይደለም የሚያስፈልገው። የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት መጥፋት እኮ ለሁሉም ጉዳት እንጂ ጥቅም የለውም፤” “አንዳንዴ የዘንድሮን የምክር ቤት ተወካዮች ስመለከት በአንድ ትልቅ የሃይማኖት አባት ምርቃት ተርከፍክፎላቸው የአሜን ድምፃቸውን አሰምተው እንደሚወጡ ምዕመናን አቆጥራቸዋለሁ፤”
“መደማመጥ በሌለበት አገር ውስጥ መካሪ ከመሆን ሱባዔ መግባት ይሻላል፤” በስንቱ ተስፋ ቆርጠን እንዘልቀው ይሆን??? ለሻአቢያ ልጆች ኤርትራውያን የተሰጠው መብትስ ለኢትዮጵያውያን የሚፈቀደው መቼ ነው???

Filed in: Amharic