>
5:18 pm - Wednesday June 15, 1312

‘’ብፃይ ስብሃት አሁንም ችግር መቀስቀስህን አቁም...’’ ወ/ሮ አዜብ መስፍን 

‘’ሳራ ከምዘይብላ አድጊ…’’ አቶ ስብሃት ነጋ 

ንስሪ ደኣማት

አፈትልከው ከወጡ መረጃዎች ጥቂቶቹ ለማስታወስ ያክል… ወ/ሮ አዜብና ከአቶ ስብሐት ነጋ በነበራቸው አለመግባባት በካቢኔው ትልቅ ውጥረት ተከሰተ፡፡ ለሁለት እንዲከፈልም ምክንያት ሆነ… በዛች ቅፅበት ነገርየው ወደ መሰዳደብ አመራ፡፡ አቶ በየነ መክሩ ከዶ/ር ደብረፅዮን ሃይለቃል የተቀላቀለበት ንግግር አደረጉ፤ አቶ አለም ገብረዋህድ ከአቶ ሚኪኤለ አብርሃ ከቆየው ጥላቻ በመነሳት ወደ ከፋ የብልግና ንግግሮች ተቀየረ፡፡ ይህ መሰዳደብ ለ4 ሰዓታት ቀጠለ፡፡ አቶ ስብሃት ነጋ ሲጋራቸው ለኮሱ፡፡ አቶ አባይ ወልዱ አንድ ነገር ተናገሩ… ህወሓት በኛ ላይ ያላት አመኔታ እያጣች መሆንዋን ይሰማኛል… እማንችለው ከሆነ መንገዱን ለቀቅ እናድርግላቸው … እንደሚታየኝ ከሆነም እንደዛ ብናደርግ ይሻላል… ወጣቱ ሃይል ልንጠራጠረው አይገባም አሉ…መሰዳደቡ ግን ግዜ ከመግደሉ በስተቀር መሰረታዊ የድርጅታችን መብራት አያጠፋም… ካለፍቸው የትግል ግዝያት አሁንም ድረስ ትምህርት ያልቀሰማችሁ አመራሮች እንዳላችሁ ግን ይታየኛል… በናንተ ላይ ውሳኔ መስጠትም የትግራይ ህልውና ወሳኙ ገድል ይሆናል ብለዋል፡፡ ወ/ሮ አዜብ መስፍን … እንዲክ አሉ ‘’አልገባኝም ውሳኔ ስትል ምን ማለትህ ነው አባይ? ካሉ ቦሃላ አቶ በየነ መክሩና አቶ ብርሃነ እጃቸው አወጡ… አቶ ብርሃነም እንዲክ አሉ ‘’ የአቶ አባይ ሃሳብ ትክክል ነው እስካሁን ካሳለፍናቸው መራራ ግዝያት ትምህርት አልቀሰምንም…ከጀግናው ህዝብ ወጥተን ህዝባችን ረስተናል እናም አሁን ይብቃን በተለይም እኔ እረፍት ያስፈልገኛል እያመምኩኝ ነው መታከም ይሻለኛል በማለት ሃሳባቸው ሰጡ፡፡ አቶ ስብሃት ነጋ አንድ ነገር አሉ…’’ ታመምኩኝ ደከምኩኝ ማለቱ ትክክል አይደለም በቃኝ ከሆነ በቃኝ ነው… መሰረታዊ ችግራችን እናውጣ ብለን ስንል ግምገማችን እስከ ውስጣዊ አጥንታችን ዘልቆ መግባት አለበት… አቅጣጫ ማስቀየሱ ትክክል አይመስለኝም አሉ፡፡ ወ/ሮ አዜብ ‘’ ከተቀመጡበት ብድግ ብለው ተነሱና የኔ ሃሳብ ትክክል ነው ያንተ ስህተት ነው ብሎ ማለት ትክክል አይመስለኝም… አሁንም ቢሆን በስተ-እርጅና የድርጅታችን መሰረታዊ ችግሮች በመደበቅ የግል ጥላቻን መርጨት ትክክል አይደለም፡፡ ብፃይ ስብሃት አሁንም ችግር መቀስቀስህን አቁም… በኔ የሚመራ ኔትዎርክ አለ ያልከው ትክክል አይደለም፡፡ ለኔ የስራ ውጤቴ ምስክር ናቸው፡፡ ኔትዎር ባንተ ላይ ነው ያለው…መጣሁኝ፡፡ በማለት በሩን ገፍትረው ወጡ፡፡ ካቢኔው ፀጥ-ረጭ አለ፡፡ ብዙ ሳይቆዩ ዕረፍት ወጡ… ወ/ሮ አዜብ ለአቶ አባይ ወልዱን ጠጋ ብለው ሹክ አሉ፡፡ ወ/ሮ አዜብ መስፍን አዲስ አበባ ሄዱ፡፡ ካቢኔው ቀጠለ… አቦይ ስብሃት አንዴ ወደ ቀኝ አንዴ ወደ ግራ አንገታቸው አዞሩ…፡፡ ወ/ሮ አዜብ መስፍን በመሃከላቸው የሉም፡፡ ግምገማው ቀጠለ…መሸ ወደ ማረፍያቸው ሄዱ… አቦይ ስብሃት ነጋ ወ/ሮ አዜብ መስፍን መድረክ ረግጠው እንደወጡ ሞባይል መልእክት ላኩ…ወዴት? ወደ 3 ሰዎች አንድ ሚኒስትር እና ሁለት የማህበራዊ-ሚድያ አክቲቪስቶች ፡፡ ይቀጥላል…
Filed in: Amharic