ከፍተኛ የብአዴን አመራሮች
ለዓለማቀፋዊ ላብአደራዊነት ሲታገሉ የኖሩት ኢህአፓ እና መኢሶን በአመዛኙ በራሳቸው የውስጥ ችግር እንዳልሆነ ከሆኑ በኋላ ነበርበዘመኑ እዚህ ግባ የሚባል ፖለቲካዊ ትኩረት ያልነበረው ህወሃት መለምለም የጀመረው፡፡ በሰዓቱ ‘ህብረ-ብሄራዊ ነኝ’ ይል የነበረውብአዴንም በእናት ፓርቲው ኢህአፓ መቃብር ላይ ነበር ህልውናውን የጀመረው፡፡ በጫካ ቆይታው ህብረ-ብሄራዊው ኢህዴን በብሄርተኮሩ ህወሃት አይዞህ ባይነት ብቻ ሳይሆን ለሎሌነት በተጠጋ ጥገኝነት ስር እንደነበር አቶ ገብሩ አስራት በመፅሃፋቸው በደንብአብራርተውታል፡፡ ህብረ-ብሄራዊ ነኝ ሲል የታላቋን ሃገር ሁሉንም ህዝብ ፖለቲካዊ ህይወት ለማሻሻል እታገላለሁ ባዩ ኢህዴን ለአንድጎሳ እታገላለሁ በሚለው ህወሃት ጉያ ስር ገብቶ ‘አቤት ወዴት’ ማለቱ የአደናጋሪነቱ ጅማሬ ነው፡፡ ከፅንሰት ውልደቱ ጀምሮ ግራአጋቢነቱ እየባሰበት የሄደው ብአዴን አትኩሮት ሰጥቶ ለሚከታተለው ብዙ አስገራሚም አደናጋሪም ማንነቶችን የተሸከመ ፓርቲ ነው፡፡
ከፖለቲካዊ ፍዘት ወደ ጎሰኝት መኮማተር
ኢህዴን በጫካ ትግሉ ዘመን የትግራይ ነፃ አውጭ ነኝ ባዩ ህወሃት ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ሲገሰግስ የእርሱ ህብረ-ብሄራዊነት ከህወሃት ጎሰኝነት ጋር እንዴት መሰናሰል እንዳለበት ግልፅ አላደረገም፡፡የኢትዮጵያን ህዝብ ወክሎ ሲታገል የትግራይ ህዝብምየኢትዮጵያ ህዝብ ነውና ጥያቄው በኢህዴን ትግል ውስጥ ሊመለስ እንደሚችል ግልፅ ነው፡፡ ነገር ግን ኢህዴን ስሙን የሚመጥንወታደራዊም ሆነ ፖለቲካዊ ብርታት አልነበረውምና የህብረ-ብሄራዊነትን ታላቅ ስም ይዞም ለአንድ ጎሳ እታገለላለሁ በሚለው ህወሃትእየተዘወረ በሽፍንፍን አዲስ አበባ ገባ፡፡ ኢህአዴግ የሚለው ማዕቀፍ ከተመሰረተ በኋላም በኢህዴንነቱ ቀጠለ፡፡ ኢህአዴግ የሚለውማዕቀፍም ሆነ በዚህ ስር ገባ የተባለው ኢህዴን ህብረ-ብሄራዊ መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡ በሽግግር መንግስቱ ወቅትም ኢህዴንበፓርላማ የተወከለው ኢህአዴግ በሚለው ስም ነበር፡፡ በህወሃት፣በሻዕብያ እና በኦነግ ሲዘወር በነበረው የሽግግር ወቅት ፖለቲካየኢህዴን ሚና ፈዞ ህወሃት ያለውን ‘አዎ አዎ!’ ማለት ነበር፡፡ኢህዴን ከዚህ ፖለቲካዊ ፍዘት ወደ ባሰው ጎሰኝነት የተኮማተረው በመአድመመስረት ምክንያት ነበር፡፡ በታዋቂው ሃኪም ፕ/ሮ አስራት ወልደየስ ዋናነት የተመሰረተው መአድ የመመስረቱ ዋነኛ ምክንያትበሽግግሩ ወቅት በአማራ ህዝብ ላይ የወረደው መቅሰፍት ነበር፡፡ ጊዜ ካለፈ በኋላ ህወሃት በኦነግ፣ ኦነግ ደግሞ በህወሃት የሚያላክኩትግን ከሁለቱ የማይዘል በአማራ ህዝብ ህልውና ላይ የደረሰው ግፍ አንዳች ሃይል የዚህን ህዝብ ድምፅ ለማሰማት መመስረት እንዳለበትግድ ብሎ ነበር፡፡ ስለሆነም ፕ/ሮ አስራት ግድ ያለ ውድ በአንድ ብሄር ስም ፓርቲ መስርተው የዚህን ህዝብ መከራ ለማቅለል ደፋ ቀናይሉ ያዙ፡፡በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን መአድ ወደ ህብረብሄራዊነት እንደሚያድግ፣እርሳቸውም ኢትዮጵያዊነታቸውን እንደሚያስቀድሙይናገሩ እንደ ነበር መዛግብት ያስረዳሉ፡፡
በመሆኑም የመአድ አባላት አማሮች ብቻ አልነበሩም፡፡ ይልቅስ የሰብዐዊ ፍጡርን እንግልት የማይወድ ሁሉ በመአድ ጥላ ስር ተሰባስቦበየቦታው ለሚገደለው፣ በገደል ለሚወረወረው አማራ ጥብቅና መቆም ጀመረ፡፡ይሄኔ ፕ/ሮ አስራት ጥርስ ውስጥ ገቡ፤ ፓርቲያቸውምሆነ የአባላቶቹ ህልውና አደጋ ውስጥ ገባ፡፡ ይሄኔ የብልጣብልጡ አቶ መለስ ህወሃት መአድን በብአዴን የማጣፋትን ድንቅ ፖለቲካዊ“ጌም” ይዞ ብቅ አለ፡፡ ወትሮም በፖለቲካዊ ፍዘት ውስጥ የነበረው የነታምራት ላይኔ ብአዴን እሳት እንደነካው ላስቲክ ተጨማዶብአዴን ለመሆን አላመነታም፡፡
እዚህ ላይ ልብ መባል ያለበት ነገር ለእያንዳንዱ ብሄረሰብ ቆሜያለው የሚለው የኢህአዴግ አባልም ሆነ አጋር ፓርቲ የህወሃትን ቡራኬካላገኘ ስንዝር መራመድ አለመቻሉ ነው፡፡ የአማራን ህዝብ ፍዳ ለማስቆም ከልብ ተነሳስቶ የተመሰረተው መአድ አባላት ቤተክርስቲያንእንደገባች ውሻ ሲታደኑ የነበረው አመሰራረታቸው የህወሃት አሻራ ስለሌለበት ነው፡፡ ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው የሃገሪቱ የሽግግርዘመን ቻርተርም ሆነ በኋላ ህገ-መንግስቱ ስለመደራጀት መብት የሚያስቀምጡት አንቀፅ ምድር ላይ ነፍስ የሚዘራው ህወሃት ይሁን ብሎእስትንፋስ ሲዘራበት ብቻ መሆኑን ነው፡፡እውነት እንነጋገር ከተባለ የአማራን ህዝብ ቀልብ በመግዛቱ በኩል ከመአድ እና ከብአዴን የቱየተሳካለት ነበር/ነው? በትቂቱ ፖለቲካዊ ስሌት ብንሄድ እንኳን መአድ የከሰመው ብአዴን ደግሞ የአማራን ህዝብ እየተሳደበም ቢሆንሁሌ ተመረጥኩ እያለ የሚያስተዳድረው የአማራን ህዝብ ቀልብ የሚስብ ፖለቲካዊ ማንነት ኖሮት ሳይሆን የባለ ጠብመንጃው ህወሃትየትሮይ ፈረስ ስለሆነ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ብአዴን አንድ የተሳካለት ነገር ቢኖር መአድን አጥፍቶ የህወሃት/ኢህአዴግን ልብ ማረጋጋትመቻሉ ነው፡፡
“ስፊኒክሱ” ፓርቲ
የሃገራችን የብሄር ፖለቲካ ስሪት ከክልሎቹ መጠነ ስፋት ጀምሮ በርካታ አስቂኝ እና ግራ አጋቢ እውነቶች ቢኖሩትም እንደ በአዴንአስቂኝነቱ የሚበረታበት የለም፡፡ ጨቋኝ ሲባል የኖረው አማራ መአድን ለማጥፋት ሲባል ብቻ ከመቅፅበት ተጨቋኝ ሆኖ ብአዴንየሚባል ዲሞክራሲ አማጭ ፓርቲ ተነጎተለት፡፡
Source: ethiothinkthank