>
5:16 pm - Tuesday May 23, 9020

በመቐለ  ስብሰባ ሳሞራና ስብሀት ስለ ትግራይ ህዝብ ሲባል እንዲግባቡ ይለመናሉ 

ዘውዴ ታደሰ

ሕወሃት ከጥር 3 -11 በመቐለ ሰማዕታት አዳራሽ ስብሰባ ያካሂዳል ። በመጀመርያ ውስጣቸው ያለውን መከፍፈል በይቅርታና ለስልጣን ሲባል ሰላም እንዲያወርድ ይደረጋል(የሳሞራና ስብሀት ስለ ትግራይ ህዝብ ሲባል እንዲግባቡ እየተለመነ እንደሆነ ይሰማል ከዚህ በሀላ የተሰነጠቀ ህውሓት እንዳይኖር ይፈለጋል በአደባባይ እንደ ተከፍፈልን ህዝብ አቆታል ይህ ሊተረም ይገባዋል ብለው እንደ ትልቅ አጀንዳ ይዘውታል ። አዜብም ልትመለስ ትችላለች ። በዚህ ስብሰባ ላይ ከ2500 በላይ የህውሓት አባላት ይገኛሉ ።
ስለ ቤተመንግስቱ የ17 ቀን የኢህኣዲግ ስብሰባ የህውሓት አባላት በዝርዝር ይነገራቸዋል ምን እንዳጡ ምን እዳገኙ ማን እንደ ደገፍቸው ማን የተጋሩን ስልጣን ለመንጠቅ እንዳሰፈሰፈ ከመጀመርያ ቀን ውላቸው እስከ 17ተኛ ቀን የነበረው ሂደት ይተነተንላቸዋል ። እኛ ለህውሓት የስጋ ዘመዶች ስላልሆንን ስለ ዝጉ ስብሰባ እሚነግረንም የለም እንመራችሀለን የሚሉትም ሰወች የተወያዩበትን አጀንዳ ለህዝብ በይፍ ሲያወጡ አይታይም ። ለመጪው 8 ቀናት የ4ኪሎውን ቤተመንግስት ለሀይለማርያም በይደር ሰጥተው አዲስ አበባን ለአሰፍ አብዩ በአደራ አስይዘው የህውሓት መሪዎች ሰሜናዊት ኮከብ ይከትማሉ ።
በመጨረሻም ስለ እስረኛ ፍቺ በደንብ ይወያያሉ እሚፈቱት ታሳሪዎች ከእዛ መልስ ሊሆን ይችላል ተለይተው ሚታወቁት ። የህውሓት አባላት በሽብር የተከሰሱትን እስረኞች ማነው እንድንፈታ ያስገደደን የአለም ባንክ ፕሬዝዳንታ ነች ፣ ወይስ እምትደራደራቸው ፓርቲዎች አልያም ኦህዴድና ብአዴን ብለው በግልፅ ይጠይቃሉ ። ኦህዴድ ይሁን ብአዴን በሀገራዊ ጉዳይ ላይ የመወሰን ስልጣን እንደሌላቸው በተደጋጋሚ የታየ እውነት ሲሆን ህውሓት በዚህ ስብሰባ ላይ ለመጋቢቱ የሀዋሳ ኢህአዴግ ጉባኤ ላይ እሚሳተፍ አባላቱንም ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል ።

Filed in: Amharic