>
5:14 pm - Friday April 20, 5212

አንዳርጋቸዉ ጽጌ ላይ ከምመሰክር ብትገሉኝ እመርጣለዉ! (አበበ ወንድምአገኝ)

በህወሃት አፈና ዉስጥ ከገባ 4 አመታትን አስቆጥሯል በማህበራዊ የመገናኛ ዘርፍ ፊት አዉራሪዉ ኢሳት ግንባር ቀደም ተሰላፊ ነበር አበበ ወንድምአገኝ።

ተወልዶ ያደገዉ አዲስ አበባ ቀድሞ ከፍተኛ 13 ቀበሌ 06 ተብሎ በሚጠራዉ ሰፈር ነዉ። አበበ በደቡብ አፍሪካ ይኖር የነበረና ከ10 አመታት በፊት ወደ እንግሊዝ በመሄድ ኑሮዉን የመሰረተ፤ ባለትዳርና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ሲሆን ታታሪና ከሁሉ ጋር ተግባቢ ግለሰብ ነበር።

 አበበ ወንድምአገኝ

ለግዜዉ ስማቸዉን ይፋ ማድረግ ያልተፈለጉ በእንግሊዝ ሐገር የሚኖሩ የቅርብ ሰዎች አበበን በተሳሳተና በሃሰት ዉንጀላ እየሰለሉ ወደ ብሐራዊ መረጃ ወሬ በማቀበል ለአፋኙ ህወሃት አስረከብቡት።

አበበ ደፋርና ነጻ የሆነ ሰዉ ስለነበር ከብዙ አመታት በኃላ ወደ እናት ሐገሩ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቹን ለመጎብኘት ተጓዘ። የእንግሊዞቹ ቃል አቀባዮችም ለህወሃት አፋኝ ቡድን መረጃዉን አቀበሉ።

ልክ አዲስ አበባ እንደ ደረሰ ኤርፖርት ላይ ከሁሉም ሰዉ በተለየ መልኩ ከባድ ፍተሻ ተደረገበት። የግል የሆኑ ንብረቶቹ በሙሉ ተመሰቃቀሉ ሻንጣዉ ተቀዳዶ ሁሉም እንዳልነበር ሆኖ ወጣ። የብሄራዊ መረጃዉ አበበን ኤርፖርት ላይ ማፈኑን አልፈለገዉም ነበር ምክንያቱም መቀናበር የነበረባቸዉ የአፈና ዘዴዎች እቅድ ላይ በመሆናቸዉ ነበር።

 ይህም ማለት የብሄራዊ መረጃዉ ከሽብር ጋር በተያያዘ መልኩ አበበን ማፈን ፈልጎ ነበር አፈናዉ ሆን ተብሎ የተጠናና በሌላኛዉ ወንጭፍ አርበኞች ግንቦት 7ን አሸባሪ ድርጅት ለማድረግ የታቀደም ከመሆኑ ባሻገር ለሌሎች ማስፈራሪያና ትምህርትም ተብሎ የታለመም ነበር።

 በዚህም መሰረት አበበ ደንበል ህንጻ ላይ የፈንጂ ጥቃት ሊያደርስ ከአርበኞች ግንቦት 7 መመሪያ የተሰጠዉ ሰዉ ነዉ የሚል የወንጀል መዝገብ ተከፈቶ ተቀናበረ። ሁሉም መልኩን ከያዘ በኋላ አበበን ቦሌ አካባቢ በቁጥጥር ስር አዋሉት።

የብሄራዊ መረጃዉ ሁሉንም አቀናብሮ ሲያከትም የአንድ ልጅ አባት የሆነዉን ወገናችን የኢሳት ደጋፊ በመሆኑ ብቻ ዘብጥያ ወረወረዉ። አበበን የሐገር ባለዉለታ የሚያደርገዉ ታላቅ ነገር ቢኖር የተከበሩት የአርበኞች ግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ከየመን ታፍነዉ ከተወሰዱ ወዲህ በአንዳርጋቸዉ ጽጌ ላይ መስክርና በነጻ ትለቀቃለህ የሚል ዋስትና ቀረበለት።

አበበ ግን ” በአንዳርጋቸዉ ጽጌ ላይ ከምመሰክር ብትገሉኝ እመርጣለዉ ” በማለት እስሩን በክብር በመቀበል የነጻነትን ቀን እየተጠባበቀ ይገኛል።”

የምትመለከቱት ፎቶ በመንግስት ሚድያዎች የተለቀቀ ሲሆን በተቀነባበረ ሴራ እግሩ ስር ካሉት ፈንጂዎች ጋር ነው ያዝነው የሚሉት።

Filed in: Amharic