“..በዓለም ላይ ብቻዬን እንኳን ብቀር እኔ ዘመነ ካሴ በግሌ ለዚህ አላማ ለህወሃት እስከ ፍጻሜ በታማኝነት ጸንቼ እቆማለሁ…” ዘመነ ካሴ በህወሃት የዲያስፖራ ደጋፊዎች ስብሰባ ላይ ተገኝቶ የገባው ቃል ኪዳን
ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ
“..በዓለም ላይ ብቻዬን እንኳን ብቀር እኔ ዘመነ ካሴ በግሌ ለዚህ አላማ ለህወሃት እስከ ፍጻሜ በታማኝነት ጸንቼ እቆማለሁ…” ይህ ንግግር ከአንድ የ TDF አመራር ወይም ከአንድ TPLF አመራር በዲያስፖራ ላሉ ደጋፊዎቻቸው የተነገረ ቃል ኪዳን አይደለም። ይህንን ቃል ኪዳን ለዲያስፖራ ተጋሩዎች ጄ/ል ፍስሀ ማንጁስ ፣ ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ወይም ፈትለወርቅ ወልደጊዮርጊስ (ሞንጆሪኖ) አንደበት የተነገረ ቃል ኪዳን ሳይሆን በአማራ ስም የሚንቀሳቀሰውና በአማራ ፋኖ ስም የተደራጀውን አፋብን በሰብሳቢነት እመራለሁ ባዩ ዘመነ ካሴ አንደበት የተነገረ ቃል ኪዳን ሲሆን የክፍለ ዘመኑ የዚህ ትውልድ ታላቁ ክህደትና ባንዳነት ሆኖ የታየ ተግባር ነው።
“… በእስር ቤት እያለሁ ከበረከት ስምኦን ጋር በመሆን በእኛ እና በህወሃት መካከል መፈጠር ስለሚገባው አንድነት ደጋግሜ ስገልጽ ነበር። በእስር ቤት እያለሁ እኔን ለመጠየቅ ከአክሱም ለመጡ አባት የተናገርኩት ሀቅ ነው። በ2013ቱ ጦርነት ወቅት ይህንን ግንኙነት የፈጠርኩና ምናልባትም ዛሬ ይህንን ድምጼን ከሚሰሙት ውስጥ የህወሃት አመራር የሚያስታውሱት ነው ……. ስለትግሬዎች ጀግንነት ካነበብኩት መጽሀፍ የአማራ ተዋጊዎች ባሉበት ትግሬዎቹ እንደ ተተከለ ድንጋይ ሆነው የሚዋጉ ጀግኖች መሆናቸውን ….. ይህ ታላቅ ጀግንነትም ለሀገረ ኢትዮጲያ የተከፈለ ጀግነት መሆኑን የተረዳሁበት …. እናንት የትግራይ ዲያስፖራዎች ድርጅታችሁን ህወሃትን ከዚህ ቀደም እንደሰጣችሁት ታላቅ ድጋፍ በማድረግ ዛሬም ህወሃትን ከመጥፋት እንድትታደጉ …. የህወሃት መጥፋት ማለት የትግራይን ህዝብ ድርጅትና መሪ አልባ የሚያደገግ መሆኑን ….ወዘተ ወዘተ እንድታውቁ እፈልጋለሁ ” በማለት በጄ/ል ፍስሀ ማንጁስ ዋና አዘጋጅነት TDF/TPLF በዲያስፖራ ካለው ደጋፊያቸው ጋር በዝግ ለመመካከር ባዘጋጁት የዙም ስብሰባ ላይ ሳይጋበዝ በግድ ካልተገኘሁ ሞቼ እገኛለሁ በማለት ፍስሀ ማንጂስን አስቸግሮ በስብሰባው ላይ በመገኘት የተናገረው ዘመነ ካሴ ነው።
ዘመነ ካሴ የአማራን ጀግንነት በትግሬ ጀግንነት ቀይሮ፣ የአማራን ክብር፣ ጥቅም ክዶና አማራውን አራክሶ የትግሬን እና የህወሃትን ጀግንነት፣ አይበገሬነት ወድቆ ተነሺነትን እየገለጸ በሰበከበት ስብስባ ህወሃታዊያኑ በክብር እንግዳነት ጋብዘው ያደረገው ንግግር ሳይሆን እሱ እራሱ ለዲያስፖራ ተጋሩዎች በተናገረው ቃል መሰረት ጄ/ል ፍስሀ ማንጁስን በስብሰባው ላይ ካልተገኘሁ ሞቼ እገኛለሁ በማለት አስገድዶ በግድ የተገኘ ድንኳን ሰባሪ ሆኖ በመገኘት ያደረገው ንግግር ነው።
በጣም በሚገርም ሁኔታ በዚህ የTDF/TPLF አመራሮችና የዲያስፖራው ደጋፊዎቻቸው መካከል በተካሄደው ዝግ የዙም ስብሰባ ላይ በርካታ የህወሃትና የTDF አመራሮች ለደጋፊዎቻቸው ሰፊ ንግግር፣ ማብራሪያና ጥያቄና ምላሽ የሰጡበት ስብሰባ ቢሆንም ከዚህ ሁሉ ተሳታፊዎች ውስጥ ንግግሩ ተቀድቶ ለሚዲያ ሊክ Lik የተደረገው የዘመነ ካሴ ንግግር ብቻ እና ብቻ ነው።
እነ ጄ/ል ፍስሀ ማንጁስ በእናንተ እና በደጋፊዎቻችሁ መካከል በምታደርጉት ምስጢራዊ ስብሰባ ላይ ባትጋብዙኝም መገኘት አለብኝ ብሎ በአስገዳጅነት የተገኘውን የዘመነ ካሴን ንግግር ብቻ ለይቶና ነጥሎ ሪኮርድ በማድረግ አውዲዮውን ለሚዲያ እንዲሰራጭ ያደረገበትን ምክንያት ስንመለከት
1ኛ- እኛ ሳንጋብዝህ በግል ፈቃድህ ተገኝተህ የተናገርከውን ንግግር ይዘት አወክለዋለሁ የምትለው የአማራ ህዝብ እንዲያውቀው
2ኛ- ይህንን እኛ ዘንድ መጥተህ የሰጠህንን ቃል ኪዳን በታማኝነት ጠብቀህ ትፈጽም ዘንድ ቃል ኪዳኑ በሚስጢር መያዝ ስለለቤት ሕዝብ እንዲያውቀው
3ኛ- የራስህን ወገኖች ክደህ ታማኝነትህን ለእኛ ለተጋሩዎች፣ ህወሃቶች የሰጠህ በመሆኑ ወገኖችህ አውቀው አንተን በመከተል መላው የአማራ ፋኖ እና የአማራ ሕዝብ የህወሃት አዳኝ ሆኖ እንዲሰለፍ የአንተን ንግግር ብቻ ለይተን ለሚዲያ እንዲበቃ አድርገናል ብሎ እነ ፍስሀ ማንጂስ እንደሚናገሩ ነው ማወቅ የምንችለው።
የዘመነ ካሴና ግብረአበሮቹ መንገድ
ዘመነ ካሴና ህወሃት የተገናኙት እሱ እራሱ እንዳለው በ2013 ወይም እስር ቤት በነበረበት ሰዓት በ2014 ሳይሆን ቀደም ብሎ የአለማያ ዩንቨርሲቲ ተማሪ እያለ በጌታቸው አሰፋ በሚመራው ደህንነት ከተመለመለበት ግዜ ጀምሮ ነው ግንኙነቱ የሚጀምረው። ግለሰቡ ከዩንቨርሲቲ ከተመረቀ በኃላ ወደ ስራው አለም የገባው በዚሁ በህወሃት ብአዴን ሰላይነትና ካድሬነት የብአዴን ወጣት ሊግ ሆኖ ህወሃት አስተምራ ባጠመቀቺው የፖለቲካ ዶክትሪኔሽን ፖለቲካዊ ስብእና ተገንብቶለት ወደ ፖለቲካው አለም የገባ ሰው መሆኑን የምንረዳው።
ከዚህ የፖለቲካ Background በመነሳትም ነው የዘመነ ካሴን የፖለቲካ መንገድ ለይተን ማየት የሚቻለን ሲሆን ይህም መንገድ የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል እና የአማራ ፋኖ አደረጃጀት ዋና አላማና ግብ ፍጹም ተጻራሪ ሆኖ የምናገኘው።
የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ማለት ህወሃት ወለድ የሆነ የህልውና አደጋ የፈጠረው ትግል ማለት ሲሆን – አፈጻጸሙ ላይ ስንመጣ በቅደም ተከተል ህወሃት፣ ኦነግ፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና መሰል ድርጅቶች መሆናቸውን እናያለን።
ይህ ማለት አንድ ለነገደ አማራ ሕዝብ ህልውና እታገላለሁ ብሎ የተነሳ ግለሰብ፣ ቡድን፣ ድርጅትም ሆነ ስም የለሽ ስብስብ ውሃ ከዘይት ጋር እንደማይዋሃድ ሁሉ ከነገደ አማራ ሕዝብ ህልውና አደጋ ምንጭ ከሆኑት ከእነዚህ ኃይሎ ጋር አይደለም በቀጥታ በተዘዋዋሪ መንገድ እንኳን ቢሆን ፈጽሞ ጥምረትም ሆነ አጋርነትን፣ ትብብርም ሆነ ውህደታዊ አንድነትን ከጸረ አማራ ኃይል ከሆኑት ከህወሃት፣ ኦነግ፣ ጉምዝ እና መሰሎቻቸው ጋር ፈጽሞ የማያደርግ ሲሆን በአንጻሩም የአማራን ሕዝብ የህልውናን ትግል አክሽፎ ለመበትን ተልእኮ ይዞ የተነሳ ግለሰብም ሆነ ቡድንና ስብስብ የዚህን ተቃራኒን በመፈጸም ትግሉን ለማፍረስ ሲንቀሳቀስ ማየት ይቻላል።
ዘመነ ካሴ ባውቄ የዚህን የአማራን ሕዝብ የህልውናን ትግል አክሽፎ በመበተን ደረጃ ላይ ፊት አውራሪ ሆኖ የተሰለፈ ግለሰብ ነው። ግለሰቡ ገና ከአላማያ ዩንቨርሲቲ ተማሪ ሆኖ የህወሃት/ብአዴን ተመልማይ ካድሬና ሰላይ ሆኖ ወደ ፖለቲካው ዓለም የገባ ሰው መሆኑን ይዘን በወርሃ መስከረም 2022 ላይ የታሰረበትን እና በወርሃ ግንቦት 28 ቀን 2023 ከሳባታሚት ማረሚያ ቤት በእለተ ሰንበት በብአዴን ታጣቂዎች ታጅቦ ከእስር የተፈታበትን ሁኔታ ስንመለከት ዘመነ ካሴ ማለት የአማራን ሕዝብ የህልውናን ትግል ጠልፎ ለማክሸፍ በአገዛዙ ብአዴን ተልእኮ ተሰጥቶት የተለቀቀ የዚህ ትውልድ ቁጥር አንድ ሰርጎ ገብ የጠላት መጠቀሚያ መሆኑን ነው ነው ማረጋገጥ የምንችለው።
የአማራን ሕዝብ የህልውናን ትግል ችቦ ለኩሶ የጀመረው የአማራ ሕዝባዊ ግንባር ግንቦት 20 ቀን 2023 ህልውናውን ባበሰረ ሳምንት ግንቦት 28 ቀን 2023 በእለተ ሰንበት ከሳባታሚት ማረሚያ ቤት በብአዴን ታጣቂዎች ታጅቦ የተፈታው ዘመነ ካሴ ግራና ቀኝ ሆነው እንዲያግዙት ከተመደቡለት የተመስገን ጥሩነህ አጎት ልጅ አስረስ ማረ ዳምጤ፣ የተመስገን ጥሩነህ እህት ልጅ በሆነው ማርሸት ጸሀዬ፣ ወሎ ላይ አበበ ፈንታው፣ሄኖክ ኪዳኔ፣ጎንደር ላይ ሳሙኤል ባለድል፣ ጌታ አስራደ፣ ሸዋ ላይ ብሩክ ስለሺና መሰል ግለሰቦች ጋር በመሆን የህልውናው ትግል በእውነተኛ አማራ ልጆችና ልጆችና በስርነቀል ለውጥ ታጋይ መሪዎች አመራር ስር እንዳይመራ እጅግ አሰቃቂ የግድያ፣ የአፋና እና የስም ማጥፋት ፍረጃን ስራ በቡድን በመስራትና በማሰራት ትግሉን መሪና ድርጅት አልባ ለማድረግ ጠንክሮ ሰርታል፣ ዛሬም እየሰራ ያለ ግለሰብ ነው።
ልጅ ሆናችሁ ጥፋት በማጥፋት ከእናትና አባታችሁ የሚደርስባችሁን ቅጣት ለመሸሽ ወደ አያቶቻችሁ፣ ታላላቅ እህትና ወንድሞቻችሁ እና ወደ አጎትና አክስቶቻችሁ ሸሽታችሁ ታውቃላችሁ??
የዘመነ የብአዴን ሁለተኛ ትውልድ የሆነው ዘመነ ካሴ ወደ ህወሃት፣ ኦነግና ጉምዝ ታጣቂዎች ጋር ሄዶ መወሸቅ እና የህልውናውን ትግል አሳልፎ መሸጥ በአንድ ቤተሰብ ቅርንጫፍ ውስጥ ላለ የቤተሰብ አካል ወግኖ አማራን ጭዳ ማድረግ መገለጫ ነው እንጂ ለዘመነ ክህደት ሆኖ አይታይም።
ስለሆነም የዘመነ ካሴ እና ግብረአበሮቹ የፖለቲካ መንገድ የአማራን ሕዝብ የህልውናን ትግል ማክሸፊያ መንገድ ለመሆን የቻለው ።አበቃሁ።


















