“ይች ወፍ አዙራ ነፋች!” ይላል ሀበሻ….

ጋዜጠኛ ይርጋ አበበ 

“ይህ ከዚህ በታች ያለው ልጥፍ፤ ራሱን “የጄኔራል ፍሰሃ ማንጁስ የልብ ወዳጅ” ብሎ የሚገልጸው የቀድሞው የአፋጎ ሊቀመንበርና የአሁኑ የትብብሩ ሊቀመንበር ዘመነ ካሴ መልእክት ነው። ዘመነ “ይድረስ ለእስክንድር ነጋ” የሚል ደብዳቤ ከሩቁ ሆኖ በወንጭፍ ልኳል። (አስረስ ማረ ነው የለጠፈው)

ስለ እስክንድር ነጋ ምንም ማለት አልችልም፤ ለዛሬው ግን ራሱ ዘመነ ካሴ እነዚህን ጥያቄዎች እንዲመልስልኝ በአደባባይ እጠይቃለሁ። ከፈለገም ወንጭፉ ተቀብሎ ያድርስልኝ።

1. እስክንድርን “ከድርጅታዊ ህገ ደንብና መመሪያ ባፈነገጠ መልኩ…” የሚል ክስ አቅርበሃል። ለመሆኑ የድርጅቱ ህገ ደንብ ከየትኛው ማንፌስቶ የተቀዳ ነው? ድርጅቱ ህገ ደንብ አለው ወይ? ህገ ደንብ አለው ከተባለ አንተ ከሜጫ ተነስተህ መቀሌ ስትገባም ሆነ የትብብሩን መግለጫ ከማውጣትህ በፊት፤ ከድርጅታችሁ ለህወሓት የቀረበውን ቅድመ ሁኔታ አንፈልግም ሲሉህ፤ መላው የድርጅታችሁ አባላት ይቅርና የፖሊት ቢሮ አባላቱ ሳያውቀው ስምምነቱን በጓዳ በር ተፈራርመህ ከመግለጫው አንድ ሰዓት በፊት ለፖሊት ቢሮ አባላት ያሳወካቸው በየትኛው ህገ ደንባችሁ ነው?

2. እስክንድርን የኦህዴድ ብልጽግና ጠበቃ እንደሆነ አድርገህ ከሰኸዋል። ለመሆኑ የኦህዴድን ተስፋፊና ወራሪነትም ሆነ ዘር አጥፊነት በአደባባይ በመሞገት እስክንድርን የሚቀድመው ማነው? የብልጽግናው ሊቀመንበር ዐቢይ አህመድ በአደባባይ፤ “ጦር እንማዘዋለን” ብሎ የዛተው በአንተ ላይ ሳይሆን በእስክንድር ነጋ ላይ ነው እኮ። አንተ ያኔ በአማራ ክልል ከብአዴን የተሰጠህን ሹመት እያጣጣምክ እንደነበር ላስታውስህ እፈልጋለሁ። “ቄሮ መሪ ያለው አሸባሪ ድርጅት ነው” ብሎ እስክንድር ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ያቀረበውን ሪፖርትስ ታስታውሰው ይሆን? ባንተ ልክ ለዐቢይ አህመድ መንግሥት ተባባሪና ስትራቴጂካል አጋር ይኖረዋል ብለህ ታስባለህ እንዴ?

3. ሚዲያዎችን በጠላትና በወዳጅነት ፈርጀህ ከሰሃል። ለመሆኑ ለአማራ ሕዝብ ትግልና ለአጠቃላይ ለሕዝቡ ካንተ በላይ ጠላት አለው እንዴ? እውነታው፤ በአንተ ልክ የአማራን ሕዝብ የድል ተስፋ ያጨለመ ሰው የለም። You are the one and only traitor of our struggle. ለዚህ ነው “ይች ወፍ አዙራ ነፋች” ያልኩህ።



LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.