የህወሃት ብአዴን የትሮዣን ፈረሶች

በአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ውስጥ ሰርገው የገቡ የህወሃት/ብአዴን የትሮዣን ፈረሶች እና እያደረሱት ያለው ታላቅ ጉዳት እና ቀጣይ ሁኔታ ሲፈተሽ…

ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ

 የአፋብን አመራሮች ትግሉን የማፍረስ የመጨረሻ ምእራፍ:-

አዱስ ስታንዳርድ ሚዲያ ‘የትብብር_ለህልዉና እና የአማራ ፋኖ መሪዎች የተመድ ልዩ መልዕክተኛ በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት እንዲያመቻቹ ጠየቁ ..” ሲል ዘመነ ካሴንና አስረስ ማረ ዳምጤን ፎቶ አስደግፎ ዜና ሰርታል። ዜናውን እጅግ ግልብና ጥቅመኛ የሆኑት የጽምዶ ተቀጣሪ ሚዲያዎች እየተቀባበሉ መሪያቸው ዘመነ ካሴ ከተመድ የአፍሪካ ቀንድ ተወካይ ጋር ተነጋገረ እያሉ እንደ ታላቅ የፖለቲካ ድል ሲያስተጋቡት ታይተዋዎ። ሆኖም የዚህ የስልክ ንግግር ዋና ባለቤት የሆኑት ሶስት ኃይሎች የተመድ አፍሪካ ጉዳይ ጽ/ቤት፣ ትብብር ለህልውና እና አፋብን እንደ ድርጅት በዜናው ጉዳይ ላይ ትንፍሽ ያሉት ነገር የለም። በእርግጥ የስልኩ ንግግር መካሄድ አለመካሄዱን እውቅና ሲሰጡም ሆነ ዜናው ሀሰት ነው ብለው ሲገልጹ እስካሁን አልተሰማም። የዝምታ እድምታ አንደኛው ክፍል ከመስማማት የሚመነጭ ስለሆነ ጉዳዩን ተቀብለን ወደ ይዘቱ እናምራ።

እንደ አዲስ ስታንዳርድ ዘገባ “ጥሪው የቀረበው ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም ከተመድ ዋና ጸሐፊ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጓንግ ኮንግ ጋር በተደረገ የስልክ ውይይት ወቅት መሆኑን አዲስ ስታንዳርድ አረጋግጧል።

አዲስ ስታንዳርድ ባገኘው ሰነድ መሠረት፣ ሁለቱ መሪዎች ከውይይቱ በኋላ ሐሳባቸውን በጽሑፍ አቅርበዋል። ጓንግ ኮንግ በበኩላቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ያብራሩ ሲሆን፣ ለተጨማሪ ውይይቶች ዳግም ለመመለስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በውይይቱ ወቅት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ እና ትብብር ለህልዉና ሊቀመንበር ዘመነ ካሴ እና የንቅናቄው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና የሥራ አስፈጻሚ አባል አስረስ ማረ፣ በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ባሉ ግጭቶች ላይ የጥምረታቸውን አቋም ያቀረቡ ሲሆን፣ በተመድ የሚደገፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር ጠይቀዋል…” ሲል በአጭሩ ዘመነ ካሴ እና አስረስ ማረ ዳምጤ ተመድ የመደራደሪያ በር እንዲከፍትላቸው በጽኑ እንደተማጸኑ መረዳት ተችላል።

ጽምዶ የተባለው ትብብር ለህልውና ዋና አሰባሳቢ የሆነቺው ህወሃት አከርካሪዋ ተሰብሮ ከኢትዮጲያ ግዛት ተባርራ ወደ ኤርትራና ሱዳን ግዛት የተራረፉት አመራሮቻ ከተሰደዱ በኃላ ከህወሃት ጋር በስደት ያለው የእነ ዘመነ ካሴ ቡድን የብአዴን ምርጥ ኤጀንት በሆኑት አስረስ ማረ ዳምጤ፣ ማርሸት ጸሀዬ፣ ማስረሻ ሰጤ ጋር በመሆን በተመስገን ጥሩነህ የበላይ መሪነት እና አረጋ ከበደ በዋናነት አጠቃላይ አፋብንን እንደ ድርጅት ይዘው ለመግባት አቅጣጫ እየተቀበሉና እየተነጋገሩ መሆናቸውን ካሰባሰብኩት መረጃ አንጻር መረዳት ችያለሁ።

አሁን ላይ ከፍተኛ ንግግር የሆነው አጀንዳ በተመስገን ጥሩነህና አረጋ ከበደ በኩል ለአስረስ ማረ እና ባልደረቦቹ እንደ ግለሰብ ሳይሆን በአጠቃላይ የህልውናውን ትግል ላንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ ለማክሰም እንደ ድርጅት አፋብንን ይዘው እንዲገቡ በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሲሆን ከጎጃም ባሻገር በጎንደር፣ በሸዋ እና በወሎ ቤተ አምሃራ ውስጥ ያሉትን የብአዴን Sleeper Spy የሆኑትን አባላቱን ብአዴን Activate በማድረግ እና ከአስረስና ግብረአበሮቹ ጋር በቀጥታ እየተገናኙ የየቀጠናቸውን የአፋብን አደረጃጀት እንዲያቀሳቅሱ አቅጣጫ የመስጠት ጉዳይ ላይ ያተኮረ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል።

ተመስገን ጥሩነህና አረጋ የማርሸት ጸሀዬ እጅ መስጠት በኃላ የአስረስ ማረ ዳምጤ፣ ጥላሁን አበጀ፣ መንግስቱ ለማና መሰሎች በጋራ ሆነው ግን በተናጥል እንደ ግለሰብ ወደ ባሕር ዳር ያደረጉትን ጉዞ ያስቆሙት “ተልእኮአችሁ የተሳካ የሚሆነው ድርጅቱን አፋብንን በሙሉ ይዛችሁ ስትመጡ ነው..” በማለት እንደመለሳቸው ነው ማወቅ የቻልነው።

እነ አረጋ ከበደ ይህንን ውሳኔ ከወሰኑና እነ አስረስን ከመለሱ በኃላ ዘመነ ካሴን ያካተተ እንዱሆን በማዘዝ ወደ ብልጽግና የመግባቱን ሂደት እጅግ ሞቅና ደመቅ ባለ ሁኔታና አለም አቀፍ ተቃማት በታዛቢነት በሚሳተፉበት ሁኔታ የአማራን ሕዝብ የህልውናን ትግል ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለማክሰም በዘመነ ካሴ መሪነት አፋብን በሙሉ በእርቅና በድርድር ስም አመራሮቹ ወደ ባህርዳር ገብተው ተዋጊው ፋኖ የሚበትኑበትን እቅድና ፕሮግራም አቅደው ለተፈጻሚነቱ ተመስገን ጥሩነህ፣ አረጋ ከበደ፣ አስረስ ማረ ዳምጤ፣ ማርሸት ጸሀዬ፣ ማስረሻ ሰጤ፣ ኢያሱ አባተ፣ ጥላሁን አበጀ፣ ዘመነ ካሴ ሆነው እየሰሩ ሲሆን በዘመነ በኩል ያለበት ስፍራና ሁኔታ ለዚህ የማያመች መሆንን ተከትሎ ድርድሩ ህወሃትን ያካተተ በጽምዶ ስም መሆን አለበት የሚል አቃም የመያዙ ጉዳይ እንደ ተግዳሮት የተጠቀሰ ሲሆን የክፍለሀገራቱን አፋብን እዝ ሁኔታ የገመገሙት ወሎ ቤተ አምሃራን ምንሊክ እዝን ሙሉ በሙሉ ለህወሃት የገበረ፣ የጎጃም ቴውድሮስ እዝ almost ከሞላ ጎደል የተቆጣጠሩት መሆኑን ይገልጽና በጎንደር እና በሸዋ እዞች ላይ ያላቸውን ግምግማ እስካሁን ለሁለቱም ጎራ – ማለትም ለህወሃትም ሆነ ለብአዴን ኔትወርክ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ያልገቡ ኃይሎች ያሉበት ቀጠና ሲሉ አስቀምጠውታል።

የማርሸት ጸሀዩ እጅ መስጠት እና እያስተጋባ ያለው መረጃ

“…ፋኖ ለአማራ ሕዝብ አደገኛ ነቀርሳና ፀረ-ሰላም ኃይል ነው” በማለት የተናገረው የአፋጎ ቃለ አቀባይ በመሆን የአማራን ሕዝብ የህልውናን አደጋን ታግሎ በማታገል ምትክ የለሽ ብርቅዬ ህይወታቸውን ለመስዋት አቅርበው የሚታገሉትን እውነተኛ የአማራ ልጆች ላይ ጥቃት በመክፈት የሚታወቀው የማርሸት ጸሀዩ ነው በ NBC ላይ ቀርቦ የተናገረው።

እንደ ማርእሸት ገለፃ፣ ፋኖ ግልጽ የሆነ የትግል ዓላማ ሳይኖረው የአማራን አርሶ አደር ለከንቱ መስዋዕትነት እየዳረገ ያለ ፅንፈኛ ኃይል እንደሆነ የገለጸ ሲሆን ሕዝቡን ላልተፈለገ ግጭት እየገፋፋ ነው በማለት ተናግራል።

ባለፉት ዓመታት በወለጋና በመተከል የተፈጸሙ ጥቃቶች በሙሉ ከብሔር ማንነት ጋር በማያያዝ የአማራን ለማነሳሻነት ሲባል የተፈጠሩ ክስተቶች ናቸው በማለት ጭፍጨፋውን የካደ ሲሆን አሁን ደግሞ በአርሲ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ የሃይማኖት ሽፋን በመስጠት እየከሰመባቸው በመጣው የብሔር አጀንዳ ምትክ የኃይማኖት አጀንዳ ለመፍጠር ሊጠቀሙበት እየጣሩ ነው ሲል የነገደ አማራ ሕዝብ በወለጋ፣ በመተከል፣ በአርሲ መጨፍጨፍን በመካድ ሲናገር ሰምተናል።

በዚህ ልጅ እጅ መስጠት ጉዳይ ላይ እስካሁን ድረስ አፋብንም ሆነ የአፋብን ቴውድሮስ እዝ እስካሁን የሰጠው መግለጫ የሌለ ሲሆን ከሁለት ወር በፊት ግለሰቡ እጁን ሰጠ በተባለበት ወቅት ዘመነ ካሴ መግለጫ አውጥቶ በኃላ ላይ በመካድ የዘመነ መግለጫ አይደለም የሚል ማስተባበያ ከወጣበት በስተቀር ስለ ማርሸት እጅ መስጠት እስካሁን ትንፍሽ ያለ የለም።

በተለይ በአፋጎ ውስጥ በአንድ ድርጅት አብረው የነበሩ ከመሆናቸውም በላይ በስጋ የሚዛመደው አስረስ ማረ ዳምጤ እንደ የአፋብን ቃለ አቀባይነቱ በማርሸት እጅ መስጠት ጉዳይ ላይ መግለጫ ማውጣትም ሆነ ሲጠየቅ መልስ መስጠት ሲገባው በድንገት ለቀረበለት ጥያቄ No comment በማለት ሊያልፈው ችላል።

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ በጎንደር ጠቅላይ ግዛትና በወሎ ቤተአምሃራ የተከሰቱ የክህደት ተግባሮችን በብርሃን ፍጥነት የውግዘት ናዳ በማስተጋባት የሚታወቀው የተመስገን ጥሩነህ አጎት ልጅ የሆነው አስረስ ማረ ዳምጤ በሌላኛው የተመስገን ጥሩነህ እህት ልጅ በሆነው ማርሸት ጸሀዬ እጅ መስጠት ጉዳይ ላይ “..የምሰጠው አስተያየት የለም..” ብሎ ጥያቄውን ሲዘጋ የቀረበበትም The so called of Media ተራ ተከፋይ የጽምዶ ፕሮፖጋንዲስት ልፍስፍስ ዘንድ ነው የቀረበው እንጂ እውነተኛ ጋዜጠኛ ጋር ቢቀርብ ኖሮ እንዴት አንተ የአፋብን ቃለ አቀባይ፣ የአፋጎ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ሆነህ ሳለ የአፋጎ ቃለ አቀባይ የነበረው ማርሸት ጸሀዬ እናንተን ክዶ እጁን ለጠላት ሲሰጥ የምሰጠው አስተያየት የለም የምትለው ?? ብሎ ያፋጥጠው ነበር። ሆኖም አስረስ ማረ ዳምጤ እንደ አፋብን ቃለ አቀባይነቱ በማርሸት ጸሀዬ እጅ መስጠት ጉዳይ ማብራሪያ መስጠት ግዴታው ቢሆንም ትንፍሽ እንዳይል ያደረገው ነገር እሱ እራሱ ያለበት ስለሆነ እራሱን ማጋለጥ ስለማይቻለው ነው ።

 በአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ውስጥ ሰርገው የገቡ የህወሃት/ብአዴን የትሮዣን ፈረሶች :-

የአማራን ሕዝብ የህልውናን ትግል ችቦ ለኩሶ ያስጀመረው እና በታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ የተመሰረተው የአማራ ሕዝባዊ ግንባር ግንቦት 20 ቀን 2023 (12-09-15) ህልውናውን በይፋ ባበሰረ Just በሳምንቱ ግንቦት 28 ቀን 2023 ዘመነ ካሴ ከነበረበት ሳባታሚት ማረሚያ ቤት በእለተ ሰንበት በብአዴን ታጣቂ ሚሊሻ ታጅቦ እንዲፈታ ተደረገ።

በታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ ግንቦት 20 ቀን 2023 የተመሰረተው የአማራ ሕዝባዊ ግንባር ” መነሻችን የአማራ ህልውናን ማስጠበቅ ፣ መድረሻችን የኢትዮጲያ አንድነት ” በሚል መሪ መፈክር ለስር ነቀል ለውጥ የተነሳ ኃይል የመሆኑ ጉዳይ እና መላውን የአማራን ሕዝብ በሀገር ውስጥ እና በዲያስፖራ ያለውን በአንድነት ማሰባሰብ፣ማደራጀትና ማንቀሳቀስ የቻለ ለአገዛዙ ታላቅ የስልጣን ስጋት ኃይል የመሆኑ ጉዳይ ብልጽግና በአጭሩ ለመቅጨት በደብረ ኤሊያስ ላይ መጠነ ሰፊ ሰራዊት በማዝመት አረመኔያዊ ጦርነት በመክፈት ሕዝባዊ ግንባሩንና አመራሩን ለመደምሰስ ቢጥርም ጀግኖቹ ግን በአይበገሬነት ተፋልመውና እጅግ ታላቅ መስዋእትነት ከፍለው ዘመቻውን በማክሸፍ በአራቱም ጠቅላይ ግዛት ውስጥ ያለውን የአማራን ፋኖ በአገዛዙ ላይ አፈሙዙን እንዲያዞር የማድረግ ታላቅ ስራ ተጀመረ።

ይህንን የመታገያ በቂ አጀንዳ ያለውንና ለስርነቀል ለውጥ ቆርጦ የተነሳን ሕዝባዊ ግንባሩን ለማስቆም የሚቻለው በፋኖ ስም የሚንቀሳቀስ ብአዴናዊ የሆነ ወሳኝ መሪ ወደ ጫካ መላክ ማስገባት ብቸኛ አማራጭ ሆኖ በመገኘቱ ብአዴን በመስከረም ወር 2022 ባህርዳር ቀበሌ 14 ይዛ ያሰረቺውን ዘመነ ካሴን ከነበረበት ሳባታሚት ማረሚያ ቤት የህልውናውን ትግል ያከሽፍ ዘንድ ቀጥተኛ ተልእኮ ሰጥቶት በእለተ እሁድ ግንቦት 28 ቀን 2023 በብአዴን ታጣቂዎች አጅቦ ከእስር በመፍታት በባህር ዳር ሙሉጌታ ሪል ስቴት በመንግስት ወጪ እንዲያርፍ ተደረገ።

በቀጣይ ከዘመነ ካሴ ጋር ሆነው ተልእኮውን በማሳካት ደረጃ አስረስ ማረ ዳምጤ፣ ማርሸት ጸሀዬ የተመደቡለት ሲሆን በተለይም ማርሸት ከተመስገን ጥሩነህ በኩል በቀጥታ ለዘመነ የተመደበ አገናኝ መስመር ሆኖ በመመደብ:-

1ኛ- የፋኖ አደረጃጀት በስር ነቀል ለውጥ አማኝ አመራሮች እጅ እንዳይገባ….

2ኛ- በአማራ ፋኖ መካከል ድጹማዊ አንድነት እንዳይፈጠር የመበተን ስራን እንዲሰሩ …

3ኛ- መነሻችን የአማራ ህልውና፣ መድረሻችን የኢትዮጲያ አንድነት መሪ አታጋይ መፈክር የህልውና ትግሉ መነሻ እና መድረሻ እንዳይሆንና በምትኩም አባይን የማይሻገር በአማራ ክልል ብቻ ላይ ያተኮረ አታጋይ መፈክርና አይዲኦሎጂ እንዲያሰርጹ

4ኛ- በአማራ ሕዝባዊ ግንባር እና በታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ ላይ ያተኮረ የሌት ተቀን ዘመቻ በማድረግ ከአማራ ፋኖ እና ብሎም ከመላው የአማራ ህዝብ ልብ ውስጥ የመፋቅ ስራን እንዲሰሩ …

5ኛ- በጎጃም ላይ የተነሳውን የፋኖን ኃይል የተመስገን ጥሩነህ፣ የአረጋ ከበደ ቤተሰብ በሆኑት ኤጀንቶች አመራር ስር እንዲሆን ማድረግና በስርነቀል ለውጥ የሚያምኑትን ፋኖዎች በስልት የማስወገድ ስራን እንዲሰሩ ….አቅጣጫ ተቀምጦላቸው፣ በጀት፣ ሎጀስቲክስ፣ መረጃ፣ ጥበቃና ከለላ በመስጠት ብአዴን ሊያሰማራቸው በቃ።

እነዚህ በህልውና ትግሉ ውስጥ ሰርገው የገቡ የህወሃት/ብአዴን ቁጥር አንድ የትሮዣን ፈረሶች:-

1ኛ- ዘመነ ካሴ
2ኛ- ማርሸት ጸሀዪ
3ኛ- አስረስ ማረ ዳምጤ
4ኛ- ማስረሻ ሰጤ
5ኛ- ኢያሱ አባተ
6ኛ – መስፍን ከፈለኝ
7ኛ- አበበ ፈንታው …… እና መሰል ቅድመ ታሪካቸው ከብአዴን ጋር በአባልነት ተሳትፎ ታሪክ ያላቸውን ሰዎች በፋኖ ስም ተልእኮ በመስጠት ሊያሰማራቸው ቻለ።

ከእነዚህ ውስጥ ገሚሶቹ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ( አፋሕድ)ን ይዘው ለመግባት ሞክረው ባይሳካቸውም እራሳቸውን ይዘው ወደ ባሕርዳር በመግባት አፋሕድን በማፍረስ ተልእኮአቸውን በከፊል የፈጸሙ ሲሆን ከዚህ የቀሩት ሁለተኛው ክፍል እነሆ አፋብንን ሙሉ በሙሉ ይዘው ለመግባት በተሰጣቸው አቅጣጫ በመስራት ላይ ይገኛሉ።

ለመሆኑ እነ አረጋ ከበደና ተመስገን ጥሩነህ ዘመነ ካሴ፣ አስረስ ማረ ዳምጤንና መሰል ጫካ ውስጥ የቀሩትን ኤጀንቶቹን በመጠቀም አፋብንን እንደ ድርጅት ሙሉ በሙሉ ወደ ባህርዳር በማስገባት እና ተዋጊ ሰራዊቱን በመበተን የህልውናውን ትግል ለማክሸፍ ይቻላቸዋልን??? የአማራ ፋኖስ ይህንን ሁኔታ አውቆ መለወጥና ማክሸፍ ይቻለዋልን?? እንዴት ? የሚሉትን ነጥቦች በክፍል ሁለት እመለስበታለሁ። አበቃሁ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.