>

የአዲስ አበባ የጥንት ስም “በረራ” ነው!!! (በፕሮፌሰር ሐብታሙ ተገኘ )

የአዲስ አበባ የጥንት ስም “በረራ” ነው!!!
ፕሮፌሰር ሐብታሙ ተገኘ 
የበረራን ታሪክ የፃፍነው ፣ አንዱን ነባር ፣ ሌላውን መጤ እና እንግዳ ለማድረግ አይደለም፡፡ ፅሑፉን ለማዘጋጀት የተፈለገው ፣ ስለ አዲስ አበባ የኋላ ታሪክ ያለውን የታሪክ ክፍተት ፣ በተወሰነ መልኩ ለመድፈን ያግዛል ፣ እንዱሁም ስለቦታው ታሪክ ኢትዮጵያዊያን ትክክለኛ መረጃና እውነት እንዲኖራቸው በማሰብ ነው፡፡ 
 
የአዲስ አበባ የጥንት ስም “በረራ” ነው፡፡በረራም ፣ የነገስታቱ ቀዳማዊ ዋና መቀመጫ ከተማ በመሆን ፣ ከአፄ ዳዊት ቀዳማዊ ዘመን ፣ (ከ1380-1413 ) ድረስ ፣ እንዲሁም በአፄ ልብን ድንግል ስርወ መንግስት ዘመን ፣ማለትም (ከ1408-1480) ፣ በረራ ከመቶ አመት በላይ አገልግላለች፡፡ በረራ ወረብ በሚባል አውራጃ ስር ትተዳደር እንደነበር ፣ የታሪክ መዛግብቶች ያስረዳሉ፡፡ ወረብ ታላላቅ አብያተክርስቲያኖች እና ቤተመንግስቶች የነበሩበት ፣ በጣም ሀብታም አውራጃ ነበር፡፡ በዚሁ ዘመን ፣ የግራኝ አህመድን ጦርነትን ከግራኝ ወታደሮች ጋር እየተዘዋወረ ሲዘግብ ፣ ወረብንና በረራን ያየው ፣ ሻሀብ አደዲን እብዱልቃዲር ፤ “ፉቱህ አል ሃበሽ” በተሰኘው መፀሐፉ ፣ “በረራን የሐበሾች ምድራዊ ገነት” ይላታል፡፡
 የበረራን ታሪክ የፃፍነው ፣ አንዱን ነባር ፣ ሌላውን መጤ እና እንግዳ ለማድረግ አይደለም፡፡ ፅሑፉን ለማዘጋጀት የተፈለገው ፣ ስለ አዲስ አበባ የኋላ ታሪክ ያለውን የታሪክ ክፍተት ፣ በተወሰነ መልኩ ለመድፈን ያግዛል ፣ እንዱሁም ስለቦታው ታሪክ ኢትዮጵያዊያን ትክክለኛ መረጃና እውነት እንዲኖራቸው በማሰብ ነው፡፡ የዚህ ፅሑፍ ይዘት ፣ ያልነበረን ፣ ወይም ያልተነገረን አዲስ ታሪክ ለማስተዋወቅ አይደለም፡፡ ለዚህ ፅሑፍ የተጠቀምናቸው ማስረጃዎችም ፣ ከዚህ በፊት ስለ በረራ ታሪክ መፃፋቸው የታወቁ ምንጮች ናቸው፡፡ ይህ ፅሑፍ ሁለት አላማዎች አሉት፡፡ አንደኛው ፣ የበረራን ወይም የአዲስ አበባን የኋላ ታሪክ ባጭሩም ቢሆን ለመዳሰስ ነው፡፡ ሁለተኛው ስለ በረራ ፣ በኢትዮጵያዊያንም ሆኑ በውጪ አገር ፀሐፊዎች የተፃፉ ታሪኮችን ለአንባቢ ለማስተዋወቅ ነው፡፡ በተለይም ፣ የቦታው ተወላጆች ስለበረራ በሰጡት ምስክርነት ላይ የተፃፉትን ለማካተት ይሞክራል፡፡ የበረራን ታሪክ ያጠኑ ተመራማሪዎች ፤ ኦጂኤስ ክራውፎርድ ፣ ሪቻርድ ፓንክረስት እና ሀርትዌትግ ብሪትሪት ፣ ሳሙኤል ዎከር እና ማርኮ ቪጋኖ ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም ታዋቂው ጣሊያናዊ የካርታ ባለሞያ ፣ ፍራ ማውሮ ፣ በረራንና ባካባቢው ያሉ ከተሞች ፣ ወንዞች ፣ ተራሮች እና ገዳማት ፣ በ1450 አመተ ምህረት ባዘጋጀው የአለም ካርታ ፣ የቦታውን ተወላጆች በመጠየቅ አስፍሯቸዋል፡፡
 የፍራ ማውሮ የአለም ካርታ ፣ በትክክለኛነቱ በአለም የተደነቀ ነው፡፡ ካርታው ፣ አውሮፓውያን ኢትዮጵያን ጨምሮ አለምን ለማሰስ በዘመኑ ባደረጓቸው ጥረቶች ውስጥ ፣ ከፍተኛ ሚና ተጫውቶላቸዋል፡፡ ፍራማውሮ ለሳይንስ እውቀት እድገት ላደረገው አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት ፣ የጨረቃ የተወሰኑ አካላት በስሙ ተሰይመውለታል፡፡ የበረራ ታሪክ ፣ ከአፄ ዳዊት ፣ ማለትም ከ1380-1413 – ቀጥሎም እስከ አፄ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግስት ፣ ከ1508-1540 ፤ ስለ በረራ የመጀመሪያው የታሪክ ማስረጃ ፣ በ1450 የተሳለ የአለም ካርታ ነው፡፡ በዚህ ዘመን የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩት አፄ ዘረ-ያእቆብ ፣ ከ1434-1468 ድረስ የገዙት ናቸው፡፡ ነገር ግን የበረራ ታሪክ ከዚህ ይጀምራል ማለት አይደለም፡፡ ከተማው ተመስርቶ ፣ አድጎ ፣ ለነገስታቱ መቀመጫነት እስኪበቃ ድረስ ፣ ብዙ አመታት መፍጀቱ አይቀርም፡፡ የአፍቃል መረጃ እንደሚያስረዳው ፣ “እንጦጦ ፣ ወይም በረራ” ፣ በዋናነት የአፄ ዳዊት ከተማ እንደነበር ነው፡፡ አፄ ዳዊት የዘረ ያእቆብ አባት ሲሆኑ ፣ የነገሱት ከ1380 አመት ጀምሮ ነበር፡፡ ስለዚህ ከፍራማውሮ የአለም ካርታ መዘጋጀት በፊት ፣ በረራ የአምሳ አመት እድሜ አስቆጥራ ነበር ማለት ነው፡፡ ካርታው በያዘው መረጃ ብዛትና ጥልቀት ፣ በዘመኑ ተወዳዳሪ አልነበረውም፡፡ የፍራማውሮ ካርታ የመጀመሪያው የሚታወቅ ሳይንሳዊ ካርታ ነው፡፡ ሳይንሳዊ የሚያደርገው ፣ በመሬት ላይ ባሉ ተጨባጭ እውነታዎች ላይ እንጂ ካርታው ከሃይማኖታዊ ግብአቶች ይልቅ ፣ በመሬት ላይ ያሉ ነበር እውነታዎች ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ በመሆኑ ነው፡፡ በካርታ ስራውም ብዙ ባለሞያዎች ተሳትፈዋል፡፡ የኢትዮጵያን ካርታ የሚያሳየውን የዚህን ካርታ ክፍል እንደ ማስረጃ ተጠቅመነዋል፡፡
 መረጃውን የሰጡ ሰዎች ፣ በተለይም የአዋሽን ወንዝ ፣ በረራን እና የዝቋላን ገዳም የሚያውቁ መሆን ነበረባቸው፡፡ ካርታው በሚያስደንቅ ሁኔታ መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ ያንፀባርቃል፤ በረራንም በደንብ ያሳያል፡፡ በተጨማሪም የንጉሱ ዋና መቀመጫ መሆኑንም በደንብ ይገልፃል፡፡ በበረራ አካባቢ ያሉ ከተሞችን ፣ ወንዞችንና ፣ አድባራትን ያሳያል፡፡ ከነዚህም ውስጥ የአዋሽ ወንዝ ፣ የዱከም ወንዝ ፣ የዝቋላ ገዳምና የአምባ ነገስት ተራራ ይገኙበታል፡፡ ሁሉም እስከዛሬ ድረስ በትክክለኛ ካርታው ላይ በተገለፁበት አቀማመጥ እንዳሉ ይገኛሉ፡፡ ዱከም ከየረር ተራራ የሚመነጭ አነስተኛ ወንዝ ነው፡፡ በዚህ አካባቢ ያሉ ስሞችን ኦሮሞዎች ከዘመናት በኋላ ስያሜዎቹን ቢቀያይሩትም ፣ “ዝቋላ” በጥንታዊ ስሙ እስካሁንም አለ፡፡
 በዚህ ፅሑፍ ውስጥ ያሉት ፎቶዎች እና አንድ ቪድዮ፣ የአዲስ አበባን ጥንታዊ የፈረሱ ፣ የነገስታት መኖሪያ ቤተመንግስት የሚያሳይ እና በአውሮፓዊያን የአጥኚ ቡድን ፣ እቦታው በመሆን ባደረጉት የቁፋሮ ጥናት የተረጋገጠ ነው፡፡ በተጨማሪም የሳተላይት ካርታው ፣ የምኒሊክ ቤተመንግስት ከተመሰረተበት እንጦጦ ፣ አካባቢ ይህ የቀድሞዋ ጥንታዊ ከተማ በረራ በትክክል የት ከስድስት መቶ አመት በፊት ተመስርታ ታገለግል እንደነበረች የሚያሳይ ማስረጃ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ብቻ ሳይሆን የፍራ-ማውሮ ካርታ እና የፍቱል ሃበሻ የአይን እማኝ ምስክርነቶች እና አያሌ መዛግብት፤ የአሁኗ አዲስ አበባ ፣ የቀድሞዋ ፣ የበረራ ከተማ ለመሆኗ ፣ በከፍተኛ ማስረጃ የተደገፈ ፣ ታሪካዊ ፣ የቀዳማዊ አፄ ዳዊት መናገሻ እንደነበረች ማሳያ ነው፡፡ በንባቡ ይማሩበት ፣ ሌሎቹንም ማስረጃዎች መርምሮ ለማስረዳት ፣ በዚህ ፅሑፍ ውስጥ የተጠቀሱትን ተመራማሪዎች ስራዎች በማየት ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
የአጼ ዳዊት ከተማ አዲስ አበባ(በረራ)ና ሕልማቸው
 ከ500 ዓመት በፊት አጼ ዳዊት ስለ አዲስ አበባ ትንቢት ነበራቸው
Ze Addis
ያሁኗ አዲስ አበባ ላይ ከተማቸውን መስርተው የነበሩት አጼ ዳዊት : ስለ ከተማቸው ትንቢት ተናግረው ነበር:: ይቺ በረራ የተባለችው ከተማቸው በአህዛብ ወረራ ብርቱ ጉዳት እንደሚደርስባትና በኋለኛው ዘመን ግን እንደምትታደስ በሚገርም ሁኔታ ነው ትንቢት የተናገሩት::እንደተነበዩትም ባራራ በግራኝ ብርቱ ጉዳት ደረሰባት:: በኋላ በአጼ ምኒልክ ዘመን ታደሰች::
 አጼ ምኒልክ አዲስ አበባን ድጋሚ አነሷት : አደሷት እንጂ አልቆረቆሯትም:: ብዙ ምስክር መጥቀስ ይቻላል:: የካ ያለውን የድንጋይ ፍልፍል ዋሻ ሚካኤልን ማን ሰራው? አጼ ምኒልክ የተነሱ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ነው:: ዋሻ ሚካኤል ደግሞ የተሰራው በ5ኛ ው ክፍለ ዘመን ነው:(https://washamikael.wordpress.com/)
እንጦጦ ራጉኤል ( የመጀመርያው የድንጋይ ፍልፍሉን) ቤተ ክርስትያን ማን ሰራው? አጼ ምኒልክ ከመነሳታቸው ቢያንስ ከ500 ዓመት በፊት የተሰራ የዋሻ ፍልፍል ቤተ ክርስትያን ነው::
እነዚህ አብያተ ክርስትያናት በሙሉ ( Royal Churches)ናቸው:: የተሰሩት በመካከለኛው ዘመን በነበሩ ነገስታት ናቸው:: ነገስታቱም ያሰሩት መናሃርያቸው ስለነበረ ነው::
ልክ ላሊበላ : ነአኩቶ ለአብ እና ሌሎቹ ነገስታት በሮሃ ላይ የድንጋይ ፍልፍል አብያተ ክርስትያናት እንደሰሩ: የመካከለኛው ዘመን ነገስታትም እንዚህን አብያተ ክርስትያናት አንጸዋል:: የካ ምኒሊክ ከመነሳታቸው 500 ዓመት በፊት ሕዝብ ነበረው:: ድንቅ ቤተ መንግስታዊ ቤተ ክርስትያን ነበረው:: እንጦጦም እንደዛው:: https://uthiopia.com/barara-entoto-barara/
አስደናቂው ፎቶ 
አጼ ቴዎድሮስን ለመውጋት የመጡት እንግሊዞች የዘረረፏቸው መጽሓፍ ላይ ታሪኩ ከነስዕሉ አለ::የአጼ ምኒልክ አማካሪ የነበረው አልፍሬድ ኢልግ የጻፈልን መጽሓፍም ውስጥ ታሪኩን ታገኙታላችሁ::
ለዛሬ ፎቶውን እነሆ! የአጼ ምኒልክ የመጀመርያው ቤተ መንግስት ይሄ ነበር:: በጎን በኩል ተኝቶ ህልም ያየው ንጉስ አጼ ዳዊት ናቸው:: በኋለኛው ግዜ ከተማቸው እንደምትታደስ ያዩትን ህልም እንዲህ ነበር ሰዓሊው ያስቀመጠው::የፈረንሳይ ተመራማሪዎች ከጻፉት የተወሰደ ነው:: ( picture Credit እንዲል ፈረንጅ)
የድሮዋን በህረራ ያሁኗን አዲአ አበባ በተመለከተ የተጻፉ ብዙ ጥናታዊ ጽሁፎች አሉ:: በቃሌ መሰረት ለጠየቃችሁኝ ሁሉ ለመላክ እየሞከርኩ ነው:: አንዳንዶቹን የጥናት ወረቀቶች እዚህ ሊክ ላይ ታገኙታላችሁ::
ዋቢ መጻሕፍትና ሊንኮች
Vigano, M., The Names Lost, the Map Grasped. Central Shoa on the Fra Mauro map,
Academia.edu, 2015.
https://www.academia.edu/…/The_Names_Lost_the_Map_Grasped._…
Fra_Mauro_map
Vigano, M., What of medieval Archaeology in Ethiopia? The quest for Barara, a plan forarchaeological urgencies, Academia.edu, 2010, pp. 14.
https://www.academia.edu/…/What_of_Medieval_Archaeology_in_…
Barara_a_plan_for_archaeological_urgencies
 Vigano, M., Thirty-two historic/archaeo Sites in the Central Shoa-Addis Ababa area are set to prove its medieval, not recent origin, Academia.edu, 2014
https://www.academia.edu/…/Thirty_two_archaeological_sites_…
baba_are_set_to_prove_its_medieval_not_recent_origin
Filed in: Amharic