>
11:16 am - Wednesday December 7, 2022

የ“ብሄሮች ጠላት ማን ነው? ሞጋሳ ወይስ ምኒሊክ??? (ርዕዮት)

የ“ብሄሮች ጠላት ማን ነው? ሞጋሳ ወይስ ምኒሊክ???
ርዕዮት 
 
በWashington DC ሰአት አቆጣጠር ከ12 PM ጀምሮ፡፡ በኢትዮጵያችን፣ ታሪክ ለፖለቲካ አቋምና ርዕዮት እንዲመች ሲባል እየተቆረጠ መቀጠሉና መሰረት የለሽ የዘውግ ትርክቶች በአመክንዮና በማስረጃ የሚሞግታቸው ጠፍቶ መንሰራፋታቸው አሁን የምንገኝበትን አደገኛና አስቸጋሪ አገራዊ ሁናቴ ፈጥሯል፡፡
በተለይ የግራ ፖለቲካ ልክፍተኛ የሆነው ያ ትውልድ በእያንዳንዱ መንደር የህይወት ክፍያና በሁሉም ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን መስዋእትነት የተሰራችውን ሀገር በ“ብሄሮች” እስር ቤትነትና ይባስ ብሎም በቅኝ ገዢነት መፈረጁ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ ብዙ ጉዳት አምጥቷል፡፡
እድሜያማው የኢትዮጵያ ጥንታዊ ሀገረ መንግስት ባልፈጸመው ማንነት በማጥፋትና በመጨፍለቅ ወንጀል ሲከሰስ፣ ዘር ማሳሳትና ባህል መደምሰስ መገለጫዎቹ የሆኑት የሞጋሳም ሆነ የገዳ ስርአት በዲሞክራሲያዊነት የሚሳሉበት ግራተዋስኦ ሰፍኗል፡፡ እያደር እየጎላ የመጣውና ሰሞኑን እየተስተጋባ ያለው “ወደገዳ ስርአት እንመለስ” የሚል የኦሮሞ ብሄርተኞች ዜማ፣ “የኩሽ ምድርን እንመስርት” የሚል ቅዠት እንዲሁም በቅርቡ “በጉራጌ ዞን ከ158 አመት በፊት ተቋርጦ የነበረው የገዳ ስርአት እንደገና ቀጠለ” ተብሎ በመንግስት መገናኛ ብዙሀን በስፋት የተዘገበው አስገራሚ ተውኔትም ከዚህ የተወናገረ የታሪክ ትርጓሜ የሚመነጭ ነው፡፡
ተጨማሪ አስረጂዎችን ለመጥቀስ ያህል፣
ሀ፦ መሰረት የሌለው የተበዳይነት ትርክትና ይህ የፈጠረው “ህገመንግስት”፣
ለ፦ በአዲስአበባም ሆነ በማናቸውም የኢትዮጵያ መሬት ላይ የሚነሳ የልዩ ጥቅምና የልዩ ባለቤትነት ጥያቄ፣
ሐ፦ በአዲስአበባ ህዝብ ላይም ሆነ “የእኛ አይደለም” በሚሉት የተቀረው ኢትዮጵያዊ ላይ የአቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ ያልተገራ ዛቻ!
መ፦ የአቶ ለማ መገርሳ የህዝብ ስብጥር ለውጥ አፍራሽና አደገኛ እቅድ፣
ሠ፦  የአቶ በቀለ ገርባ ያፈጠጠ ዘረኛና አሳፋሪ አስተያየት!
ረ፦ ልዩ ጥቅምን  አስመልክተ የአብይ አህመድ  በተዋቡ ቃላት ሊሸፈን የተሞከረ ዘረኛና መርዘኛ አቋም!
ሰ፦ የአቶ ሽመልስ አብዲሳ “ትውልዱን በገዳ ስርአት የማነጽ” አድሃሪ መግለጫ፣
ሸ፦ የእነአቶ ብርሃነ መስቀል አበበ ሰኚ አይነቱ የአፓርታይዳዊው ስርአት በተሟላ መንገድ እንዲተገበር የሚካሄድ ጥሪ ወዘተ ከዚህ አንዳችም የታሪክ መሰረት ከሌለው የልዩ ባለቤትነትና የቀዳሚነት ተረት የተወለደ ነው፡፡
የኦሮሚያ የዜግነት አገልግሎት ይሉትንም ኩርማን ሀገር የመስራት ህልማቸውን የሚያመለክት መራርና በታታኝ ሁነት ልብ ይሉአል፡፡
የኦሮሞ ጽንፈኛ ብሄረተኞች ከወገኖቹ ጋር ፍጹም ተዋህዶ ሰጥቶና ተቀብሎ የኖረውን ኦሮሚኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊ በእነርሱ የመለያየት ተረት ሊነጥሉት የሚለፉትም ለዚህ ነው፡፡
እነኚህ ከፋፋይ ዘውገኞች ኢትዮጵያንና ንጉሰነገስት ዳግማዊ ምኒሊክን በቅኝ ገዢነት ሲወነጅሉ፤ በጦርነት የማረካቸውን ማህበረሰቦች በባርነት ያኖር የነበረውንና የኦሮሚኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን መገለጫ ሊሆን የማይችለውን የሞጋሳ ስርአትን ደግሞ የሰለጠነና የቀደመ ዲሞክራሲያዊ ስርዐት አስመስለው ሲተርኩ ቅንጣት  ሀፍረት እንኳ አይስተዋልባቸውም፡፡
አዲስ አበቤነት ይለምልም፤
ኢትዮጵያ ምንጊዜም በክብር ትኑር፡፡
Filed in: Amharic