>

የሼኹ እጣ!!! (አርአያ ተስፋማርያም)

የሼኹ እጣ!!!
አርአያ ተስፋማርያም
ሼኽ አላሙዲ ያሉበት ሁኔታ እንደሚያሳዝን ከቅርብ ታማኝ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል። አመት ከአራት ወር ሲታሰሩ ቶርች ከተፈፀማባቸው አንዱ ሼኹ መሆናቸውን የፈረንሳይ አውታር ጭምር ያጋለጠው ጉዳይ ነበር። ሼኽ አላሙዲ ከነበራቸው 10 ቢሊዮን ዶላር ሃብት በሳኡዲው ፋሺስት ውሳኔ 8 ቢሊዮን 800 ሚሊዮን (8.8) ሲወሰድባቸው የቀራቸው 1.2 ቢሊዮን ብቻ መሆኑን ምንጮች አስታውቀዋል።
የሳኡዲ ፍ/ቤት ያቀረበባቸው ክስ “በኢትዮጵያ በሙስና መሬት በመውረር፣ ያለአግባብ ሃብት በመበልፀግ” የሚል ሲሆን፣ ክሱን አስገራሚ የሚያደርገው በኢትዮጵያ ተፈፀመ ስለተባለው “ሙስና” መጠየቅ ካለበት የኢትዮጵያ መንግስትና በአገሪቱ የፍትህ አካል መሆን ሲገባው በአምባገነኑ ልኡል ፍ/ቤት ይህ መቅረቡ አስገራሚ ያደርገዋል ይላሉ ምንጮቹ። አላሙዲ ከእስር ቢወጡም ከሳኡዲ እንዳይወጡ የቁም እስረኛ ተደርገዋል። ሞራላቸው በመነካቱ ያሉበት ሁኔታ አሳዛኝ ነው ብለዋል ምንጮቹ።
ስለባለሃብቱ የሚጠይቅም ሆነ የሚያነሳ ባለመኖሩ ይበልጥ ያሳዝናል የሚሉት እነዚህ ወገኖች ጠ/ሚ/ር አብይ ጀምረውት ለምን ዝም እንዳሉና ይፈታል ብለው ተናግረው ያልተፈቱበት እንቆቅልሹ ምንድነው? ሲሉ ይጠይቃሉ። ሼኽ አልሙዲ ገፅታቸው ጠቁሮ ክፉኛ የመጎሳቆል ሁኔታ ይታይባቸዋል።
Filed in: Amharic