>
10:55 am - Thursday August 18, 2022

ኢትዮጵያና ዓቢይ (ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማሪያም)

ኢትዮጵያና ዓቢይ

 

ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማሪያም

 

የገናና ጥንታዊ ታሪክ ባለቤት፣ ኩራትንና ክብርን የኑሮው መሠረትና መለያው አድርጎ የኖረ ሕዝብ፣ ቃር ቃር በሚል የባዕድ የአገዛዝ ፍልስፍና ለሀምሳ ዓመታት ያህል በውርጋጦች ተገዛ፤ የታላላቅ ሰዎች አገር የድንክዬዎች አገር ሆነ፤ ችጋር፣ ውርደት፣ ውድቀት፣ የሕዝቡ መታወቂያ ሆነ፡፡

እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ሕዝብ ጸሎት ሰማ፤ ዓቢይ አህመድንና ለማ መገርሳን ኮርኩሮ ቀሰቀሰ፤ ቀስቅሶ አሰማራ፤ አሰማርቶ ከውስጥም ከውጭም አቀጣጠለ፤ ትንሣኤ አቆጠቆጠ፤ አረንጓዴ ብቅ አለ፤ የተስፋ ጮራ ፈነጠቀ፤ እሾሁ ጠወለገ፤ ኢትዮጵያ ዓቢይን ይዛ ቦግ አለች፡፡

ጥያቄው፡– ዓለም-አቀፍ ሽልማቱ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ እድገት የሚያስከትል ይሆናል? ወይስ ለዓቢይ ዝና ምንጣፍ ይሆናል?ለማናቸውም ከዓቢይ ጋር በክብር ቆመን ስናጅበው ደስታ ይሰማናል፤ የሚተክዙ የኢትዮጵያ ጠበኞች ናቸው፡፡

ዶር. ዓቢይ ያበርታህ!

Filed in: Amharic