>
4:28 pm - Friday August 19, 2022

የህወሃትን መግለጫ የሰሙት የኤርትራው ፕሬዝደንት ምላሸሰ ሰጡ! (በትግሉ አስፋው - ካብ አስመራ)

የህወሃትን መግለጫ የሰሙት የኤርትራው ፕሬዝደንት ምላሸሰ ሰጡ!
በትግሉ አስፋው (ካብ አስመራ)
የባህታዊ ቀበሮ መግለጫና ሽምግልና ለኤርትራ ህዝብ ሰሚ እና ተቀባይነት የሌለው የገደል ላይ ጭኾት ነው፡፡ !!!
ክቡር አቶ ኢሳያስ አፈውሪቄ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት የትህነግ መራሹ መንግስት የተለመደውን ከስብሰባ ማዕግስት የሚያውጣው የአስመሳይነት መግለጫ ያደገበት የመሰሪነት
ባህሪው ነው፡፡
ባለፋት ሃያ ዓመት በዚህ የመሰሪነት ተፈጥሮው የአንድ እናት ልጆችን በማለያየት የኢትዮጵያ እና የኤርትራን ህዝብ በመግለጫ በመሽንገል በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ መንግስታዊ የጥፋት ሥራ ሲሰራ መቆይቱ የአለም የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡
በህዝብ ትግል ሀጢያት ከሚሰራበት በትረ ስልጣን የተወገድ ቢሆን ሀገሪቱ ሰላማዊ ሆና ያላትን ተፈጥሮዊ ፀጋ ከራሷ አልፋ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች እንዳትተርፍ በተልዕኮ የተለመደውን የማተራመስ እና ከእኔ በላይ ለአሳር ነው የሚል ግትርነት ከአንድ ዓመት በመያዝ ሲደመር እና ሲቀነስ እንደቆይ ለኤርትራ ህዝብ የተሰውር አይደለም፡፡
እውነታው ይህ ሆኑ እያለ በተደጋጋሚ ከስብሰባ ማዕግስት በተለመደው የመሰሪነት ባህሪ የሚሰጥ መግለጫ ለኤርትራ ህዝብ ሰሚ እና ተቀባይነት የሌለው የገደል ላይ ጭኾት ነው፡፡
“ ድመት መልኮሳ አመሏን አትረሳ ” አለ አማራ እውነቱን እኮ ነው፡፡ መቺም ቢሆን በተለያዩ ሀገሮች አምባሳደራት እና የሀገር መሪዎች የሚደረግ መርህ አልባ ሽምግልና የፓርቲ መግለጫ የባህታዊ ቀበሮ ባህሪ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው ለኤርትራ ህዝብ ውሃ የማይቋጥር ተግባር እና ሀሳብ ነው፡፡
ምክንያቱ
1ኛ./ የእኛ በመርህ ላይ የተመሰረተው ግንኙነታችን ከክልል መንግስት ጋር ሳይሆን ከፌድራል መንግስት ጋር ነው፡፡
2ኛ/ .ምንም እንኳን የትግራይ ህዝብ ከህዝባችን ጋር የቋንቋና የባህል ተመሳሳይነት ቢኖርውም መሪ ድርጅቶ ትህነግ አብሮት ለታገለው ለአማራ ህዝብ ያልሆነ ለኤርትራ ህዝብ ይበጃል ብልን አናምነም፡፡
3ኛ/ባለፈው ሃያ ዓመት በትህነግ መሰሪነት የኤርትራ ህዝብ ከሁለተኛ ሀገሩ በመሰሪው ትህነግ ተንኮል ሀብት ንብረታችውን ጥለው ሲፈናቀሎ ባለማተቡ የአማራ ህዝብ “ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ ” በማለት የህዝባችን ንብረት እና ሀብት መልሷል፡፡
በመሆኑ ትህነግ የአማራን ህዝብ ጠላት በማድረግ በደል ያደረሰበት በመሆኑ ይቅርታ ሳይጠይቅ ከአማራ ጠላት ጋር ህብረት አንመሰረትም፡፡
4ኛ/ ትህነግ ከእኔ በላይ ላሳራ የሚል የማያረጅ ግትርነት ባህሪው ጋር ያለፍቺ የተጋባ በመሆኑ ለጋራ ተጠቃሚነት እና እኩልነት አልርጂ ነው፡፡
ሰለሆነም ለጊዜያው ትዳር ብልን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የጀመረነው አዲስ ህብረት በምንም ታምር አናደናቅፍም፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ እና የኤርትራ ህዝብ አብሮነት በቀበሮ ባህታዊ መግለጫ እና መርህ አልባ የሽምግልና ጋጋታ አይደናቀፍም፡፡
ክቡር አቶ ኢሳያስ አፈውሪቄ የኤርትራ ፕሬዝዳንት
04/02/2012 ዓ.ም
Filed in: Amharic