>
5:13 pm - Saturday April 20, 3309

«ኦሮሞ ጋላ ነው!» ኦነግ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት ከጻፈው የተወሰደ! (አቻምየለህ ታምሩ)

«ኦሮሞ ጋላ ነው!» ኦነግ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት ከጻፈው የተወሰደ!
አቻምየለህ ታምሩ
* ኦሮሞን ነጻ ለማውጣት ታገልሁ የሚለው ኦነግ  ራሱን «ኦሮሞ ጋላ ነው» እያለ ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሲያስተዋውቅ  ኖሮ ነው እንግዲህ «ጋላ አማራ ያወጣልን ስድብ ነው!» እያለ የጥንብ አንሳ ፖለቲካውን ሲያካሂድ የኖረው!
ከታች የታተመው ታሪካዊ ደብዳቤ ኦነግ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት እ.ኤ.አ. በሰኔ 1981 ዓ.ም. ከጻፈው ባለ 18 ገጽ ደብዳቤ ውስጥ የተወሰደ ነው። ኦነግ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት የጻፈው ደብዳቤ ዋና አላማ ድርጅቱ የኦነግን አገር የመመስረት ትግል እንዲደግፍና ኢትዮጵያ የኦሮሞ ቅኝ ገዢ ስለሆነች ከቅኝ ግዛት ነጻ ወጥተው  የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ያቋቋሙ አገሮች ቅኝ ገዢዋን  ኢትዮጵያን ከድርጅቱ አባሮ ዋና ጽሕፈት ቤቱን ከአዲስ አበባ ወደ ሌላ የአፍሪካ አገር እንዲያዛውር ለመጠየቅ ነው።
የተሰመረበት የኦነግ ደብዳቤ ክፍል እንደሚያሳየው ኦሮሞ ጋላ እንደሚባል ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት ያስታወቀው ኦነግ ራሱ ነው። ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት በጻፈው ደብዳቤ ኦሮሞ ጋላ እንደሚባል፤ኦሮሞ ማለት ጋላ ማለት እንደሆነ ለአፍሪካውያን በደብዳቤ ሲያስታውቅ የኖረው ኦነግ ለኦሮሞ ልጆች ሲሆን ግን «ጋላ አማራ ያወጣልን ስድብ ነው» እያለ ይዋሻቸዋል።
ከዚህ በፊት እንደተናገርሁት ኦነግ አነግ ከመባሉ በፊት «የጋላ ነጻነት ግንባር» ነበር የሚባለው። ከዚህ በተጨማሪ ኦነግ ሞቃድሾ የከፈተውን የድርጅቱን የሬዲዮ ጣቢያ «አፋን ጋላ» የሚል ስም ነበር ያወጣለት።
ኦሮሞን ነጻ ለማውጣት ታገልሁ የሚለው ኦነግ  ራሱን «ኦሮሞ ጋላ ነው» እያለ ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሲያስተዋውቅ  ኖሮ ነው እንግዲህ «ጋላ አማራ ያወጣልን ስድብ ነው!» እያለ የጥንብ አንሳ ፖለቲካውን ሲያካሂድ የኖረው!
Filed in: Amharic