>
1:02 pm - Thursday December 8, 2022

"ዋቃ ነው ያወጣን! ጃዋር ላይ የታሰበው ጥቃት ደርሶ ቢሆን ኖሮ ሀገር ትፈርስ ነበር!!!" (ቀሲስ በላይ መኮንን

“ዋቃ ነው ያወጣን! ጃዋር ላይ የታሰበው ጥቃት ደርሶ ቢሆን ኖሮ ሀገር ትፈርስ ነበር!!!” ቀሲስ በላይ መኮንን
ብርሀኑ ተክለአረጋይ
ትናንት በጃዋር ቤት እየተሰጠ በነበረው መግለጫ ላይ ቀሲስ በላይ መኮንን የተባሉ “የኦሮሚያቤተክህነት አደራጅ፣የኦሮሚያ ዋና እምባ ጠባቂ፣የሃገር ሽማግሌና የኢሬቻ ኮሚቴ” በመግለጫው ላይ ተገኝተው ነበር።
በመግለጫው ላይ የተገኙ አካላት በሙሉ በጃዋር መሪነት ሀሳባቸውን ገለፁ።የመጨረሻው ተናጋሪ ቀሲስ በላይ እንደሆኑ ተገለፀ ይኼኔ ጌቶች (ኦቦ ጃዋር) ተቆጡ። “በቃ ጨርሰናል የእስካሁኑ ይበቃል እናመሰግናለን” አሉ።ቀሲሱ ሽምቅቅ አሉ መግለጫውም ተበተነ።
መግለጫው ካበቃ ከኋላ ቀሲሱም ካፈርኩ አይመልሰኝ ናቸውና ለomn ለብቻቸው መናገር ጀመሩ። እናም እንዲህ አሉ:-
“-  ዛሬ ከዚህ አዋጅ ታውጇል:: ጃዋርን ለመደገፍ የወጣችሁ ወደቤታችሁ ተመለሱ ተብሏል:: የተዘጋው መንገድ ይከፈት::
– የምናገረው እንደ ኦሮሚያ “ቤተክህነት” አስተባባሪ ነው::
– ወንድማችን ጃዋር ላይ ችግር እንደተፈጠረ እንደሰማን ከሌሎች ጋር ተደዋውለን በፍጥነት ጃዋር ቤት ገስግሰን መጥተን ተመካክረናል::
– ዋቃ ነው ያወጣን:: ጃዋር ላይ የታሰበው ጥቃት ደርሶ ቢሆን ኖሮ ሀገር ትፈርስ ነበር::
– አቶ ሽመልስ አብዲሳ ዘንድ ሄደን “ይህ ለምን ተደረገ ?” ብለን ጠይቀናል:: አቶ ጃዋርን መንካት መንግሥትን ሀገርን ያፈርሳል ብለናል:: አቶ ሽመልስም ስህተት መሆኑን አምነዋል:: እናርማለን ብለዋል::
– ጃዋር ሠላም ፈላጊ መሆኑን ዐውቀናል:: የኦሮሚያ መንግሥትም ሠላም ፈላጊ ነው:: ሁለቱም ዓላማቸው ተመሳሳይ መሆኑን ተረድተናል::
– ኦሮሞዎች ሌሎች ሚዲያዎችን (ከOMN በስተቀር) አትስሙ:: የሚያስተላልፉት ከዚህ ተቃራኒ ነው:: ነካክተው ነካክተው ሊያን
– ሌሎች አጀንዳ እየሰጡን ነው:: ጥፋተኛ ሆነን እንድንታይ ፈልገው ነው:: ረባሽ እና በጥባጭ መስለን እንድንታይ ነው::
– እኛ ሀገር እያስተዳደርን ሀገር እየመራን ነው::  “መንገድ እየዘጉ እንዴት ሀገር ይመራሉ?” ትብለን እንድንወቀስ ነው::
– አንዳንድ ሙስሊሞችም ሳያውቁ ቤተክርስቲያን አካባቢ አጥፍተው ይሆናል:: እነርሱ ጥፋተኞች አይደሉም:: ከሗላ ተደብቀው አጀንዳ የሚሰጡ አሉ።”
እኔ ደሞ እንዲህ አልኩ
አንዳንድ ሰው ክብረ ክህነትን ያህል ስልጣን ይዞ ለሌሎች አሽከርና ሽቁጥቁጥ መሆንን ይመርጣል
እንዲሁ አንዳንዱ ሰው ሃሳቡን የማስፈፀሚያ አቅም ሲያንሰው ክፉ ሀሳብ ባላቸው ግለሰቦች ጀርባ ይፈናጠጣል።
ተከብሮ ከመዋረድ አውጣን ነው የሚባል
(የቀሲሱ ንግግር ትርጉም የዲያቆን ዮሀንስ መኮንን ነው)
Filed in: Amharic