>
6:46 am - Wednesday December 7, 2022

ቅዱስ ፓትርያርኩ ለምን ጥርስ ተነከሰባቸው ?

ከቅዱስ ፓትርያርኩ ላይ እጃችሁን አንሱ!!!
ሀብታሙ አያሌው
• የኦዴፓን የነውር ፖለቲካ አቡክቶ ለመጋገር ቅዱስ ሲኖዶሱን እና ቤተክርስቲያንን ለመከፋፈል መሞከር ከነውሮች በላይ ነውር ነው።
• ቅዱስ ፓትርያርኩ የተገኙበትን ብሔረሰብ “ትግሬነትን” የማጥቂያ መሳሪያ ማድረግ ወደ በርባኖስ የሚወስድ የፖለቲካ ቁልቁለት ነው።
• ቅዱስ ፓትርያርኩ ለምን ጥርስ ተነከሰባቸው ?
* ቅዱስ ፓትርያርኩ በመላው ኦሮሚያ ክልል የኦርቶዶክስ አማኞች ሆን ተብሎ ከመንግስት መዋቅር ጭምር እንዲገለሉ መደረጉን ተቃወሙ፤ አጋለጡ፤
* በቤተክርስቲያን ላይ የሚደርሰውን ቃጠሎ፤ የካህናትን መታረድ፤ የምዕመናንን መሰደድ በፅኑ አወገዙ በአደባባይ መሪር ለቅሶ አለቀሱ መንግስት ኃላፊነት እንዲወስድ ይቅርታ እንዲጠይቅና ካሳ እንዲከፍል አሳሰቡ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሻፈረኝ አለ!
* ቅዱስ ሲኖዶሱ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆኖ እንዲቆም በማድረግ ብሔርተኝነትን ቦታ እንዳይኖረው ማድረግ ቻሉ!
* በቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ ደህንነትና ካድሬዎች እንዳይገኙ የመንግስትን አዛዥ ናዛዥነት እንዲቀር አቋም ይዘው በር ዘጉ!
* ቤተክርስቲያንን በመክፍል ሁለት ሲኖዶስ ለማቋቋም የተደረገውን ሙከራ በፅናት ታግለው አከሸፉ!
በተለይ በቤተክርስቲያን ላይ መንግስት እየደረሰ ባለው ጥቃት የመንግስት እጅ አለበት መንግስት ይቅርታ ይጠይቅ፤ ካሳ ይክፈል ማለታቸው እጅግ ያበሳጨው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ
የሰጠው የንዴት ምላሽ ለቅዱስ ፓትርያርኩ እንደማይተኛላቸው ያስታውቅ ነበር።
ጠቅላይ ሚንስትሩ = “እኔ አልገደልኩም፣ እኔ አላቃጠልኩም ይቅርታ አልጠይቅም”
 ቅ/ፓትርያርኩ =እርስዎ ገደሉ፤ እርስዎ አቃጠሉ አልወጣንም መንግስትን እየመሩ ነው፤ መንግስት በሚያደርሰው ጥፋትና፤ አጥፊዎችን ማስቆም ባለመቻሉ ወይም በመተባበሩ ግን ተጠያቂ ነዎት!
 ጠቅላዩ = ድሮ እንዲህ ብላችሁ አታውቁም አሁን እኔ መሪ ስሆን እንዴት ታያችሁ ?
 ቅ/ፓትርያርኩ = ለድሮው ጥፋትማ እርስዎ መንግስትን ወክለው ይቅርታ ጠየቁ፤ አይደገምም ብለው ፋይሉን በህዝብ ፊት ዘጉ፤ ከዚያ ግን የቤተክርስቲያን መከራ እጅግ ባሰ፤ እንዴት ዝም እንበል ?
ቅዱስ ፓትርያርኩ ጥርስ ተነክሶባቸዋል፤ ቅዱስ ፓትርያርኩ ብቻ ሳይሆኑ ቤተክርስቲያንን ለማዳከም ቅዱስ ሲኖዶሱን ለመከፋፈል ያልተፈነቀለ ድንጋይ የለም፤ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አስተዳደር
በደህንነት ኃላፊው በአቶ በደምመላሽ ወ/ሚካኤል በኩል የኦዴፓን አደገኛ ሴራ ትተን ህወሓት ላይ ብቻ እንድናላዝን በመምሪያ ደረጃ አስተባባሪ መድቦ በርካታ ጥረት እያደረገ ይገኛል። በዚህ ግን የተዘናጋ የለም።
* ወለጋ፣ አርሲ፣ ባሌ ክርስቲያኖች እየታረዱ አብያተክርስቲያናት እየወደሙ ያሉት በግልፅ ኃላፊነት በወሰደው በጃዋር በሚመራው ቄሮ ሆኖ ሳለ፤
* ቅዱስ ሲኖዶሱን ለሁለት ከፍለንየኦሮሞ ኦርቶዶክስ እንመስርት ያለት በይፋ በጃዋር የሚታዘዙት የኦዴፓ ሰዎች መሆናቸው እየታወቀ፤ ቅዱስ ፓትርያርኩ እንደ ወዶ ገብ የፓርቲ አመራሮችና የጥቅም ተስፈኞች ለመንግስት ስላልገበሩ፤ ትግሬነታቸውን እንደ ማጥቂያ በመጠቀም ለማጠልሸት መሞከር በእጅጉ የከፋ ወንጀልም ሐጢያትም ነው።
* * *
ትግሬነት ወንጀል አይደለም !! ትግሬነትን ከህወሓት ጋር እየለጠፉ ማሸማቀቂያ ለማድረግ መሞከር የክፋት ሁሉ ክፋት ነው !! ሐይማኖት ዘር ቀለም የለውም ከቅዱስ ፓትርያርኩም ሆነ ከቤተክርስቲያን ላይ እጃችሁን አንሱ !!
Filed in: Amharic