>
11:18 am - Wednesday December 7, 2022

ህ.ወ.ሀ.ት መድረኮች አረናን አስወጥተው እንዲያስገቧት እየተማጸነች ነው!!! (አብርሀ ደስታ)

ሲያልቅ አያምር፦

ህ.ወ.ሀ.ት መድረኮች አረናን አስወጥተው እንዲያስገቧት እየተማጸነች ነው!!!

አብርሀ ደስታ
ህወሓት ቀልባ ያሳደገቻቸው ድርጅቶች ከከዷትና ከተገለለች በኋላ “ሕገ መንግስቱንና ፌደራላዊ ስርዓቱን ለማዳን” በሚል ሰበብ ሌላ አሻንጉሊት አጋር ፍለጋ “ፌደራሊስት ሐይሎች” ያለቻቸውን ድርጅቶች (እንደነ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር ኦብነግ፣ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኦነግ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ፣ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ሲኣን፣ የዓፋር ነፃነት ግንባር ወዘተ) ጠርታ ለመወዳጀት ብትሞክርም ድርጅቶቹ ከህወሓት ጋር አብሮ መስራት የፖለቲካ ኪሳራ እንዳለው በመገንዘብ ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው አሁን የመጨረሻ አማራጯን ለመጠቀም ወደ መድረክ ለመግባት እየጣረች ነው።
መድረኮች ዓረናን አስወጥተው በዓረና ምትክ ህወሓት እንዲያስገቡ እየወተወተች ነው። ዓረና ከመድረክ ጋር አብሮ በመስራቱ “ከትግራይ ህዝብ ጠላቶች ጋር አብሮ እየሰራ ነው” እያለች በተደጋጋሚ ስትከሰን የነበረችው ህወሓት አሁን ከነዚህ “ጠላቶች” ጋር አብሬ ልስራ እያለች ነው። አሁንስ አሳዘነችኝ! ከጠላት ጋር!? ሆሆ!
Filed in: Amharic