>
5:33 am - Friday July 1, 2022

የጃዋር (ከበቡሽ) ሌላኛው ገፅ !!! (ታየ ደንደአ አረዶ)

የጃዋር (ከበቡሽ) ሌላኛው ገፅ !!!

ታየ ደንደአ አረዶ
 የቀና ይጎብጣል – ማስመሰል ይቅር!
ከበቡሽ – የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድን የላቀ ዓለማቀፍ ኒሻን ጥላሸት ለመቀባት ያልፈነቀልከው ድንጋይ፤ ያልቧጠጥከው ተራራ፤ ያልወጣኸው አቀበት እና ያልወረድከው ቁልቁለት አልነበረም።
በመሸና በጠባ ቁጥር ‘ምኒልክ’  ‘ነፍጠኛ’ በማለት በቆሞ ቀር እሳቤ ማላዘኑን ተያያዝከው። በዶክተር ዓቢይ በመታከክ የኢትዮጵያውያንን የወል ድል ለማኮስመን በርካታ ሴራዎችን ጎነጎንክ። እንደተለመደው የወገኖቻችንን ደም በክፋት በማስፈሰስ፤ ዓለም የኖቤል ሽልማቱን እንዲሰርዝ የመጨረሻ ካርታን መዘዝህ። ብሩህ ተስፋ ሰንቀው ወደ ታላቁ መካነ ትምህርት የተቀላቀሉ ተማሪዎችን በብሔረሰብ ለይተህ በማናከስ ደም እንዲፈስ አደረግህ። ከዚሁ ጎን ለጎን የኦሮሞ ተማሪዎችን በአማራ ክልል እንዲገደሉ አደረግህ።
ራሱ በድሎ ራሱ አለቀሰ
በአሉባልታ ፈረስ ሀገር አዳረሰ” እንድትል አስቴር = ጅራፉ ራስህ ገርፈህ ራስህ  ጮኽክ።  ለያዥ ለገራዥ አስቸግረህ ያዙኝ ልቀቁኝ አልክ።
የ86 ንፁሓን ህይወት ተቀጥፎም ቢሆን ዓለም የእናንተን ሸር ስለሚያውቅ እና ለገዘፈው የዓቢይ ልእለ ሰብእነት እውቅና = ክፉዎችን ችላ ብሎህ የሽልማቱ ቀን ሲቃረብ፤ “አዲስ አበባ 13 ክፍለከተሞች ልትሆን ነው = ይህም የኦሮሞን ትግል ለመጉዳት ነው” በማለት የተለመደውን የማይሰለችህን የተካንህበትን  የፈጠራ ወሬ ነዛህ። (ሀቁን የከተማው አስተዳደር ሲገልፅ ቅሌትህ እየታወቀ መጣ።)
ይባስ ብለህ ሚዲያ በመጥራት ራስህን አድራጊ ፈጣሪ ቁልፍ የፖለቲካ መሪ አድርገህ ተኮፈስህ። መንጠራራት!
ይህ ሁሉ ቋጠሮህ ተበጣጥሶ ዶክተር ዓቢይ በኖቤል አደባባይ ሲነግሥ አክሮባቲስቱ (ከበቡሽ ጠወልዋሌ) በተለመደው ተገለባባጭ የዘቀጠ ስብእናህ፦
 “ወንድማችን እንኳን ደስ አለህ”
 ብለህ የማያዋጣ ተውኔትህን ተጫወትክ።
ይህም ንግግርህ ውሎ ሳያድር – ድመት መንኩሳ ዓመሏን አትረሳ‘ እንዲሉ ሌላ እዬዬ ቀጠልክ።
ይህንን ያፈጀ ያረጀ የጃጀ ያረጠ ቆሻሻ ስብእና ይዘህ መቼም በዚህ ህዝብ ደም ላይ ቁማር አያዋጣም። አስቀያሚ ተልእኮህም የትም አይደርስም። በሰው ደም የሚነግድ ህዝብ በየደረጃው ይተፋዋልና እየሆነ ያለው ይህ ነው። መቼም ሀገር የማፍረስ ተልዕኮህ አይሳካልህም!
Filed in: Amharic