>
9:52 am - Sunday November 27, 2022

የጃዋር እቅድ...! (እንግዳ ታደሰ)

የጃዋር እቅድ…!

እንግዳ ታደሰ

David Axelrod በኦባማ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ከፍተኛውን የምርጫ ጎዳና ቀመር ያወጣለት ምርጥ ስትራቴጂስት ነበር ። መንገዱን ቀይሶና አሳልጦ በሰጠው ጎዳና ኦባማ አንተ ጎዳና አንተ መንገድ በሚል ሄዶ አሸነፈ። ዴቪድንም በመንግስቱ አስቦት ልዩ አማካሪው አደረገው።
ብዙዎች ስለ ጃwar ፓስፖርት መመለስና ለምርጫ መድረስ በህግ ዙርያ እየተነታረኩ ነው። ጃዋር ይህች ነገር አትጠፋውም አትሞኙ !! ። ጀዋር በዚህ ምርጫ ሁሉ ነገር ተሟልቶለት እንደማይደርስ ያውቀዋል። ለሱ ዋናው ጉዳይ በጥሩ ስልት ዋና ስትራቴጂስት ሆኖ ከጥብቆ እስከ እጀ ጠባብ እየሰፋ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን ፖለቲካዊ ጥበብን ማልበስ ነው።
ነግሮናል እኮ ! ሾርት ሚሞሪ’ ካላጠቃን ፣ ምርጫ consequence አለው አንድም በጡጫ ፣ አሊያም በምርጫ አይነት ። ጀዋር እቅዱ ከተሳካለት ምእራብ ሸዋን በመረራ ፥ ወለጋን በዳውድ ኢብሳ አርሲን፥ባሌን፣ሀረርን በእርሱና ከማል ገልቹ አስረግጦ እንደሚያመጣ አውቋል።
ጃዋር David Axelrodን ሁኖ እነ-መረራ አብይን’ ከኦሮሚያ ምድር ከጨዋታ ዉጭ ሲያደርጉት የመረራ ከፍተኛ አማካሪነቱን ከመጋረጃ ጀረባ የሚከለክለው የለም ። አምስት አመቱ አልቆ ሌላ ምርጫ ሲደርስ ደግሞ ከዚያ በኋላ መረራም ዳውድ ኢብሳም ከማልም ተከርብተው ከርባቹ የዉህዱ ፓርቲ መሪ ይሆናል። ይህ ነው የጃዋር እቅድ ።
Filed in: Amharic